የኣለምኣቀፉ ማህበረሰብ የኢትዮጵያ መንግስት የሲዳማን ህዝብ ህገ መንግስታዊ መብቶች እንድያከብር እና ለክልላዊ መንግስት ጥያቄ ምላሽ እንድሰጥ ግፊት እንዲያደርግ ከኣንድ ኣመት በፊት የቀረበ ጥሪ ኣጥጋብ ምላሽ ኣላገኘም
የሲዳማ ዳይስፖራ ማህበረሰብ ተወካይ የሆኑት ካላ ቤታና ሆጤሳ ለኣለም ኣቀፉ ማህበረሰብ በተለይም ለተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሃፊ ካላ ባንኪሙ፤ ለኣውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ካላ ጆሴ ኣማኑኤል ባሮሶ፤ ለኣፍሪካ ህብረት ዋና ጸሃፊ ዲኮ ኢንኮሳዛና ዲላሚን ዙማ እና ለኣሜሪካን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኮ ሂላሪ ሮዲሃም ክልንተን ደብዳቤ ጽፈዋል። በጻፉትም ደብዳቤ ላይ በሲዳማ ህዝብ ላይ በገዥው መንግስት በመፈጸም ላይ ያሉ የሰብኣዊ መብት ጥስት እንዲቆም፤ የሲዳማ እስረኞች እንድፈቱ እና የሲዳማ ህዝብ ህገ መንግስታዊ ጥያዊ የሆነው የክልል ጥያቄ በኣግባቡ እንዲመለስ ጥሪ ኣቅርበው ነበር። ብዙዎቹ ሲዳማውያን እንደሚያምኑት ከሆነ ጥሪውን ተከትሎ የተገኘው ውጤት የተጠበቀውን ያህል ኣይደለም። ጥሪውን ተከትለው የሲዳማ እስረኞች መካከል ኣንዳንዶቹ ያለ ምንም ምክንያት ከታሰሩበት የተፈቱ ቢሆንም የክልል ጥያቄውን የመሳሰሉ ትላልቅ ህዝባዊ ጥያቄዎች እስከ ኣሁን ድረሰ ምላሻ ተነፍጎበት ይገኛል። ይባስ ብሎም ሰሞኑን የሃዋሳን ከተማ በፌደራል መንግስት እንዲተዳደር ሁኔታን የሚያመቻች የከተሞች መሬት ኣስተዳደር ኣዋጅ ጸድቋል። የዛሬ ኣመት የተጻፈውን የድጋፍ ጥር ደብዳቤ ከታች ያንቡ፦ Appeal to:- Mr. Ban Ki -Moon, United Nation’s Secretary General, United Nations, 760 United Nations Plaza Manhattan, NY 10017, USA Mr. José Manuel Barroso President of the European Commission 1049 Brussels, Belgium Mrs. Inkosazana Dlamini Zuma, African Union’s Secretary Gene