የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ መልካም ተሞክሮዎችና ያልተሻገራቸው መሥመሮች
በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ በመማር ማስተማር፣ በምርምር ሥራዎች፣ በማሕበረሰብ አገልግሎትና የሰባ ሰላሳ ቅበላን ተግባራዊ ለማድረግ የመምህራንና ቤተ ሙከራ ቁሶችን ከማሟላት አንጻር ያጋጠሙ ችግሮች እንዲሁም በተወሰዱ መፍትሔዎችና በሌሎችም ጉዳዮች ከፕሬዚዳንቱ ዶክተር ዮሴፍ ማሞ ጋር ያደረግነውን ቃለ ምልልስ በክፍል አንድ ይዘን መቅረባችን ይታወሳል። በዛሬው እትማችን በዩኒቨርሲቲው ሌሎች እንቅስቃሴዎች ዙሪያ ያደረግነውን ቆይታ ይዘን ቀርበናል። አዲስ ዘመን ፦ በዩኒቨርሲቲው ወጣቶችን በተለይም ሴቶችን ከትምህርታቸው የሚያሰናክሉ የተለያዩ ችግሮች እንደሚያጋጥሙ ይነገራል። ይህ ምን ያህል እውነት ነው ? ምን የመፍትሔ እርምጃስ ተወሰደ ? ዶክተር ዮሴፍ፦ የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ በርካታ ተማሪዎችን ያቀፈ ነው። ከእነዚህ ተማሪዎች መካከል እጅግ በጣም ጥቂት በሚባሉ ተማሪዎች የተነሳ የአብዛኛው ስም መነሳት የለበትም። ተቋሙ እነዚህም ቢሆኑ ለተለያዩ ችግሮች መጋለጥ የለባቸውም የሚል አቋም ይዞ እየሰራ ነው። ያለው አመለካከት በጣም የተዛባ ነው። አብዛኛዎቹ ሴት ተማሪዎችም ቢሆኑ እኛ ለመማር ነው የመጣነው፤ አላማ አለን የሚሉ ናቸው። ከዚህ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ሴት ተማሪዎችን ሰብስበን ለማወያየት ስንፈልግ አይመጡም። ምክንያታቸው በተወሰኑ ተማሪዎች የተነሳ ሰብዕናችንን ትነካላችሁ የሚል ነው። ሐዋሳ ትልቅ ከተማ በመሆኑ በወሲብ ሥራ ላይ የተሰማሩ ሴቶች ሳይቀሩ ራሳቸውን ተማሪ በማስመሰል « ሹገር ዳዲ » የሚባሉትን ያጠምዳሉ። የተማሪ መታወቂያ ይዘውም ይገኛሉ። ይህን ችግር ለመፍታት ከከተማው ፖሊስ ጋር በመተባበር እየሰራን ነው። በመምህራን በኩልም ከውጤት ጋር በተያያዘ ከሴት ተማሪዎች ጋር አግባብ ያልሆነ ግንኙነት ለመፍጠር የሞከረ አንድ መምህር እንዲ