ከሞጆ ሀዋሳ ለሚገነባው መንገድ የአፍሪካ ልማት ባንክ የ2.4 ቢልዮን ብር ሰጠ
ከሞጆ ሀዋሳ ለሚገነባው አውራ መንገድ ከአፍሪካ ልማት ባንክ 2.4 ቢልዮን ብር በላይ ብድርና እርዳታ መገኘቱን የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ገለፀ፡፡ ከሞጆ ሀዋሳ ለሚገነባው አውራ መንገድ የ2.4 ቢልዮን ብር በላይ ብድርና ስጦታ ስምምነ ቱ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚንስትር አቶ ሶፊያን አህመድ ና የአፍሪካ ልማት ባንክ ተጠሪ ሚስ ጆሰፊን ንጉር ጋር ዛሬ ህዳር 27/2006 ተፈራርመዋል፡፡ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚንስትር አቶ ሶፊያን አህመድ እንዳሉት ከአፍሪካ ልማት ባንክ ጋር የተፈረመው ስምምነት ኢትዮጵያ ለጀመረችው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ጉዞ አካል ለሆነው የመንገድ ልማት የሚውል ነው፡፡ አቶ ሶፍያን እንዳሉት በኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ባለቤትነት የሚገነባው የሀዋሳ ሞጆ መንገድ ወጭው ከአፍሪካ ልማት ባንክና ከኮሪያው ኤግዚም ባንክ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍና በመንግስት የሚሸፈን ይሆናል፡፡ የመንገድ ፕሮጀክት ስራው ሲጠናቀቅ ወደ ደቡባዊ የሀገሪ ቱ ክፍል የሚደረገው የንግድና ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ የሚደግፍ ይሆናል ም ብለዋል፡፡ የአፍሪካ ልማት ባንክም ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን አጋርነት አጠናክሮ እንደሚቀጥል እምነታቸው መሆኑንም ሚንስትሩ ገልፀዋል፡፡ የአፍሪካ ልማት ባንክ ተጠሪ ሚስ ጆሰፊን ንጉር በበኩላቸው ከአፍሪካ ልማት ባንክ ተጠቃሚ የአፍሪካ ሀገራት ኢትዮጵያ ግንባር ቀደ ም መሆኗን አስታውሰው በቀጣይም ባንኩ የኢትዮጵያን የልማት ጉዞ እንደሚደግፍ አረጋግጠዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ዛይድ ወ/ገብርኤል ስምምነቱ በሁለት ክፍሎች ለሚገነባው 201 ኪሎ ሜትሮችን ለሚሸፍነውና በአንድ ጊዜ 6 መኪኖችን ማሳለፍ የሚችለው ዘመናዊ የሞጆ ሞያሌ አውራ መንገድ አ