ጥቂት ስለ ገዛሄኝ እና እልፍኔሽ የሃዋሳው ባለ ኣምስት ኮከብ ሆቴልና ሪዞርት
ሥራው አልቆ አገልግሎት የጀመረው የሀዋሳው ባለ 5 ኮከብ ሆቴልና ሪዞርት ስለሆነ እሱን ላስቃኛችሁ። ሆቴሉ የተሠራው ከሀዋሳ ከተማ ዳር ነው፡፡ ከሀዋሳ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ፊት ለፊት፣ ወደ ይርጋዓለም፣ ዲላ፣ ሞያሌ፣ … ከተሞች በሚወስደው አውራ ጎዳና ቀኝ ጠርዝ ነው፡፡ ወደ ሆቴሉ ሲታጠፉ የባለቤቶቹ ስም የተጻፈበት እብነበረድ አለ፡፡ ከዚያ ጥቂት ሜትሮች እንደተራመዱ፣ የሆቴሉን ትልቅ ባለ ቅስት መግቢያ ያገኛሉ፡፡ በሩ ሰፊ በመሆኑ፣ ወደ ሆቴሉ የሚገቡና የሚወጡ መኪኖች መተላለፊያቸው የተለያየ ነው፡፡ ግቢው በጣም ሰፊ ሲሆን፣ አረንጓዴ ሳር፣ በየስፍራው የተተከሉ በርከት ያሉ ዛፎችና አበቦች ሲያዩ ሆቴል ሳይሆን ዘመናዊ መናፈሻ ውስጥ የገቡ ይመስልዎታል፡፡ መግቢያውን እንዳለፉ በስተግራ፣ ግራውንድ ቴኒስ መጫወቻ፣ ከዚያ ቀጥሎ ደግሞ እንግዳ መቀበያውን፣ አዳራሽ እንዲሁም ትንሽ ራቅ ብሎ ባርና ሬስቶራንቱን ያገኛሉ፡፡ ከዚያ ፊት ለፊት ራቅ ብሎ የመዋኛ ገንዳው ይታያል፡፡ እስካሁን ክፍሎቹን አላየሁም፡፡ በባርና ሬስቶራንቱ ጐን፣ ሰፊ ስፍራ አለ፡፡ ከዚያ ቀጥሎ የተሠራው የአስተዳደርና ሌሎች አገልግሎት መስጫ ሕንፃ ነው። መኝታ ክፍሎቹን የሚያገኙት ከዚያ ሕንፃ ጀርባና ጐን ነው፡፡ ሕንፃዎቹ ሁሉ የጐጆ ቤት ቅርፅ አላቸው። በመጀመሪያው ምዕራፍ የተሠሩት 32ቱ ክፍሎች ፎቅ የላቸውም፡፡ በሁለተኛው ምዕራፍ የሚሠሩት 75 ክፍሎች ፎቅ ሲኖራቸው፣ ግንባታቸው ተጀምሮ መሠረቱ መውጣቱን ባለሀብቱ ተናግሯል፡፡ ገዛኸኝ፣ በሀዋሳ ከተማ የተሠራው ሆቴልና ሪዞርት፣ ባለ 5 ኮከብ ሆቴል ሊኖረው የሚገባውን ፋሲሊቲ አሟልቶ በኢትዮጵያ የተሠራ የመጀመሪያው ሆቴል እንደሆነ ይናገራል፡፡ ክፍሎቹ በአራት ደረጃ የተከፈሉ ሲሆን ባለ አንድ፣ ባለ ሁለት አልጋ፣ ትዊንና ልዩ የቤተሰብ መቆያ ኤግስኩቲቭ