አወዛጋቢው የይዞታ ረቂቅ መመርያ አስተያየት እንዲሰጥበት ለከተማ ልማት ሚኒስቴር ተላከ
ሕ ገወጥ ባለይዞታዎችን ሕጋዊ የሚያደርገው አወዛጋቢው ረቂቅ መመርያ አስተያየት እንዲሰጥበት ለከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ተላከ፡፡ የ62 ሺሕ ባለይዞታዎች ቀጣይ ዕጣ ፈንታን የሚወስነው ይህ መመርያ በርካታ ውይይቶች ተካሂደውበት ለውሳኔ ቢቀርብም፣ በከፍተኛ ባለሥልጣናት መካከል መግባባት ላይ ባለመደረሱ ሲንከባለል ቆይቷል፡፡ በሕገወጥ ባለይዞታነት ከሚፈረጁት መካከል 44 ሺሕ የሚሆኑት መንግሥት ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች በሰነድ ክፍያ የሚፈጽሙ ሲሆኑ፣ 18 ሺሕ የሚሆኑት ደግሞ ምንም ዓይነት ሰነድ የሌላቸው ናቸው ተብሏል፡፡ የሊዝ አዋጁን እንዲያስፈጽም በወጣው ደንብ ሕገወጥ ባለይዞታዎች በአራት ዓመት ጊዜ ውስጥ ሕጋዊ የሚሆኑበትና ከተሞች እንደነባራዊ ሁኔታቸው ሕጋዊ የማድረጉ ተግባር እንደሚከናወን ተደንግጓል፡፡ ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ የአዲስ አበባ አስተዳደር ከ1988 ዓ.ም. እስከ ኅዳር 2004 ዓ.ም. ድረስ በሕገወጥ መንገድ የተያዙ ይዞታዎችን ሕጋዊ ለማድረግ ረቂቅ መመርያ አዘጋጅቷል፡፡ ነገር ግን እስከ ኅዳር 2004 ዓ.ም. ድረስ የተገነቡ ቤቶችን ሕጋዊ ማድረግ በባለሥልጣናት መካከል አለመግባባት መፍጠሩን ምንጮች ይገልጻሉ፡፡ በሌላ በኩል በግንቦት 1997 ዓ.ም. ከተካሄደው ምርጫ በኋላ የከተማው አስተዳደር የሥልጣን ሽግግር በሚያካሂድበት ወቅት ከፍተኛ የመሬት መቀራመት እንደነበር አይዘነጋም፡፡ በወቅቱ የነበረው የከተማው ባለአደራ አስተዳደር ከዚያ በኋላም ሥልጣኑን የተረከበው የከተማው አስተዳደር ግብረ ኃይል በማቋቋም ሕገወጥ ያሏቸውን ግንባታዎች አፍርሰዋል፡፡ ባለሙያዎች እንደሚሉት ዕርምጃ በሚወሰድበት ወቅት ዕርምጃ ሊወሰድባቸው የሚገቡ፣ ነገር ግን በተለያዩ ምክንያቶች የተዘለሉ በርካታ ይዞታዎች በአዲሱ መመርያ ሕጋዊ