Posts

ቁጥሩ እጅግ ከፍተኛ በሆነ ህዝብ በሃዋሳ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች በደማቅ ሁኔታ የተከበረውን የሲዳማ ኣዲስ ኣመት የፊቼን በኣል በተመለከተ ከክልሉ ሚዲያ ውጭ ያሉት ኢቲቪን ጨምሮ የኣገሪቱ ትላልቅ የሚዲያ ኣውታሮች ሽፋን ኣለመስጠታቸው ኣነጋጋሪ ሆኗል

Image
የወራንቻ ኔዎርክ የኣገሪቱን ትላልቅ ጋዜጦችን እና የሚዲያ ኣውታሮች ዌይብ ሳይቶች ላይ ባደረገው ቅኝት መረዳት እንደተቻለው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን፤ ሬዲዮ ፋና፤ ዋልታ፤ እና የኢትዮጵያ ዜና ኣገልግሎት የፊቼ በኣልን በተመለከተ በእለቱ ምንም ዘገባ ኣለማቅረባቸው ታውቋል። የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ኣካል የሆነው ኣዲስ ዘመን ጋዜጣ ግን የጫንባላላን ኣከባበር በተመለከተ በፎቶ የተደገፈ ዜና እለቱ ይዞ ወጥቷል። ለሲዳማ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ለመላው የክልሉ ህዝብ ትልቅ ባህላዊ እሴት የሆነውን የፊቼን በኣል በተመለከተ ስለ በኣሉ ኣከባበር የምገልጹ እና በኣሉን የምያስተዋውቁ ዜናዎችን ብሎም ፕሮግራሞችን እነዚህ ትላልቅ የኣገሪቱ የዜና ኣውታሮች ኣለማቅረባቸው፤ የፊቼን በኣል በዩኔስኮ በኣለም ቅርስነት ለማስመዝገብ የምደረገውን ጥረት የዜና ኣውታሮቹ እየደገፉ ኣለመሆናቸውን ያሳያል ተብሏል። የፊቼን በኣል በኣለም ቅርስነት ለማስመዝጋብ የሲዳማ ዞን ኣስተዳደር እንድሁም የክልሉ መንግስት ከኢትዮጵያ ባህል እና ቱርዝም ሚኒስቴር ጋር በመሆን የምያደርገውን ጥረት የተሳካ ለማድረግ የኣገሪቱ የሚዲያ ኣውታሮች ባህሉን ለኣለም ህዝብ በማስተዋዎች የበኩላቸውን ልወጡ ይገባል።

የሲዳማ ህዝብ ለባህሉ ታላቅ ፍቅር ያለው ህዝብ መሆኑን ኣንድ ህንዳዊ መምህር ተናገሩ ፤ዩነስኮ ይህንን ታላቅ ባህል በኣለም ቅርስነት መመዝገብ ኣለበትም ብሏል

Image
ከ 50 ደቂቃ ጀምሮ ያለውን ይከታተሉ http://www.allcomtv.com/etv-vod?etvod=2013080716

የሲዳማ ብሄር የዘመን መለወጫ የፊቼ ጫምባላላ በኣል ከግማሽ ሚሊዮን በምበልጥ ህዝብ በታላቅ ድምቀት በሃዋሳ ከተማ ተከበረ

Image
የሲዳማ ብሄር የዘመን መለወጫ የፊቼ ጫምባላላ በኣል ከግማሽ ሚሊዮን በምበልጥ ህዝብ በታላቅ ድምቀት በሃዋሳ ከተማ ተከበረ   ለተጨማሪ http://www.allcomtv.com/etv-vod?etvod=2013080716    

‹‹መንግሥት የሃይማኖት ብዝኃነትን ሲጠብቅ ነፃነትን እንዳይጋፋ መጠንቀቅ አለበት›› ተሰናባቹ የአሜሪካ አምባሳደር ዶናልድ ቡዝ

Image
በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ሆነው ላለፉት ሦስት ዓመታት በአዲስ አበባ የቆዩት አምባሳደር ዶናልድ ቡዝ በእስልምና ተከታዮችና በመንግሥት መካከል ስላለው አለመግባባት፣ በዓባይ ወንዝና በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ስላለው ፖለቲካዊ ትኩሳትና ሌሎች ጉዳዮች የመንግሥታቸውን አቋምና የራሳቸውን ግንዛቤ ለሪፖርተር ጋዜጣና ሌሎች ሁለት ሚዲያዎች ባለፈው ሰኞ አካፍለዋል፡፡ አምባሳደሩ የሦስት ዓመታት የአዲስ አበባ ተልኳቸውን አጠናቀው ወደ አገራቸው መመለሳቸውን አስመልክቶ ከጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ቆይታ ከተነሱ ጉዳዮች መካከል በእስልምና ተከታዮችና በመንግሥት መካከል የሚስተዋለው አለመግባባትና ግጭት አንዱ ነው፡፡ ‹‹ኢትዮጵያ የተለያዩ ብሔሮችና ሃይማኖቶች የሚኖሩባት አገር ነች፡፡ ይህ ስብጥር እንደረጋ እንዲቆይ የአገሪቱ ሕገ መንግሥት የእምነት ነፃነትና እኩልነትን አረጋግጧል፤›› በማለት አስተያየታቸውን የጀመሩት አምባሳደር ቡዝ፣ መንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ እንዲሁም ሃይማኖቶች በመንግሥት ላይ ጣልቃ እንዳይገቡ በግልጽ በሕገ መንግሥቱ መቀመጡ መሠረታዊ ነው ይላሉ፡፡ ይህ መሆኑ የትኛውም ሃይማኖት ነፃነት እንዲኖረውና ለተከታዮቹም የመረጡትን ሃይማኖት የመከተል መብት ይሰጣል ብለዋል፡፡ ‹‹አሁን ካለው ሁኔታ የምንረዳው ግን አንዳንድ ሰዎች ይህንን የመቀየርና የራሳቸውን እምነት በሌሎች ላይ በግድ የመጫን ፍላጎትና አመለካከት መኖሩን ነው፤›› ብለዋል፡፡ ‹‹ይህ ሃይማኖታዊ ፅንፈኝነት ወይም አክራሪነት ሊባል ይችላል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት እየጣረ ያለውም ይህንን እንቅስቃሴ ለመቀልበስ ነው፡፡ ምክንያቱም በሕገ መንግሥቱ ላይ ያለውን የመንግሥትና የሃይማኖት ግንኙነት ፅንሰ ሐሳብ የሚጎዳና በአገሪቱ የቆየውን የሃይማኖት ብዝኃነት የሚያደፈርስ በመሆኑ ነው፤›› በማለት ይገልጻ

በሲዳማ ባህላዊ፤ ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም ፖለቲካ ጉዳዮች ላይ በመላው ኣለም ላይ ከምገኙት የሲዳማ ተወላጆች እና ከሲዳማ ወዳጆች ጋር ለመምከር የሚያስችል ፓልቶክ ሩም ተከፈተ

Image
በመላው ኣለም የምትገኙ ሲዳማዎች እና የሲዳማ ወዳጆች በፓልቶኩ ሩም በመገኘት እንድትወያዩ እና ሃሳብ እንድትለዋወጡ በኣዘጋጆቹ ተጋብዛችሃል። ወደ ፓልቶክ ሩም ለመግባት በመጀመሪያ ወደ ኢትዮጵያ ይግቡ ቀጥለውም Sidama cultural Heritage ላይ ክሊክ ያድርጉ