Posts

በሀዋሳ ሀይቅ በጉማሬ ጥቃት የደረሰበት የ15 አመቱ ታዳጊ ለህልፈት ተዳረገ

Image
አዲስ አበባ ፣ሀምሌ 25 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ)  በሐዋሳ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ዳጋ ቀበሌ ውስጥ የ15 አመት እድሜ ያለው የ9ኛ ክፍል ተማሪ ከትናንት በስቲያ 3 ከ30 ላይ ሃዋሳ ሃይቅ ውስጥ ሞቶ ተገኝቷል። ሟች ሃይቅ ውስጥ በመዋኘት ላይ እያለ አጠገቡ የነበረች አንድ ጉማሬ ግራ እግሩን በመንከስ እና አንስታ በመወርወር ህይዎቱ    እንዲያልፍ አድርጋዋለች። ከሃይቁ ውጭ ሆነው ሁኔታውን ሲከታተሉ የነበሩ ጓደኞቹ ለፖሊስ በመናገራቸው ፖሊስ ደርሶ ጉዳዩን እንዲመለከት አድርገዋል። ኢንስፔክተር ሳሙኤል ኩማ እንዳሉት    ፥ በአዲስ ከተማ አካባቢ ጉማሬዎች ይበዛሉ ፤ ይሁን እንጅ የጉማሬዎቹ ባህሪ ስለማይታወቅ ሰዎች ባይነኳቸው ይመረጣልም ነው ያሉት። በሀይቁ ላይ ጉማሬ መሰል አደጋ ሲያደርስ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን የጠቀሱት ኢንስፔክተር ሳሙኤል ፥ ጉማሬዎቹ በሃዋሳ ሃይቅ ላይ ብቅ የሚሉበት የራሳቸው የሆነ ጊዜ እንዳላቸው እና    በተለይ ጤዛ የመላስ ባህሪ ስላላቸው እና ቁስለት ሲኖርባቸውም ውጭ ስለሚያገግሙ ሰዎች ባይቀርቧቸው የተሻለ ነው በማለት መክረዋል ።

ለፍትሕ፣ ለዴሞክራሲ፣ ለልማት፣ ለአገርና ለሕዝብ በሀቅ፣ ከልብ፣ በእምነት፣ በትጋትና በተግባር እየሠራን ነው የምትሉ ባለሥልጣናት እጃችሁን አውጡ

Image
አገራችን ኢትዮጵያ ከድህነት የተላቀቀች፣ ያደገችና የበለፀገች፣ ፍትሕና ዴሞክራሲ የነገሠባት አገር ሆና ለማየት የማይፈልግ ሀቀኛ ኢትዮጵያዊ የለም፡፡ ሁሉም ዜጋ ትፈልጋለህ ወይ ቢባል አዎን ይላል፡፡ ማልልኝ ቢባልም ‹‹ሙት!›› ይላል፡፡ በተለይ ባለሥልጣናት ይፈልጋሉ ወይ? እነሱም ይምላሉ ወይ? ቢባል አዎን ይፈልጋሉ አዎን ይምላሉ ተብሎ ብቻ የሚመለስ ሳይሆን፣ በፓርላማ ሕዝብ ፊት በአደባባይ አዎን ብለው ቃል ገብተዋል፤ ምለዋል፡፡ ጥያቄው የቃልና የመሀላ ብቻ ሳይሆን የተግባር ነው፡፡ በቃልማ ሕገ መንግሥቱም ያስገድዳል፡፡ እስቲ ለፍትሕ፣ ለሰብዓዊ መብት፣ ለዴሞክራሲ፣ ለልማት፣ ለአገር፣ ለሕዝብ በሀቅ፣ ከልብ፣ በእምነት፣ በትጋትና በተግባር እየሠራን ነን የምትሉ ባለሥልጣናት እጃችሁን አውጡ፡፡ በአንድ በኩል የአገር ሀብት የሚዳብርበት፣ አገር የሚለማበትና ድህነት የሚጠፋበት ሁኔታ ቢያጋጥም፣ በሌላ በኩል ደግሞ ጉቦ፣ የቪላና የተሽከርካሪ ጥቅማ ጥቅም የምታገኙበት ሁኔታ ቢኖርና ለመምረጥ መስቀለኛ መንገድ ቢያጋጥማችሁ የትኛውን ትመርጣላችሁ? የአገርና የሕዝብ ልማትን ወደ ጎን ገፍቶ የግል ጥቅምን ማካበት? ወይስ የግል ጥቅምን በመግፋት የአገርንና የሕዝብ ጥቅም ማስቀደም? እስቲ ከልብ የአገርና የሕዝብ ልማት የምታስቀድሙ እጃችሁን አውጡ፡፡ በተግባር ነው እያልን ያለነው፡፡ ሕዝብ ፍትሕ እያጣ መሆኑን ብታውቁና ማስረጃ ቢቀርብላችሁ፣ ሕግ የሚጣሰውና ፍትሕ እየታጣ ያለው ኔትወርክ በዘረጉ ወንጀለኞችና በባለገንዘቦች መሆኑን ብታውቁ ለፍትሕና ለዴሞክራሲ ብላችሁ ከሕዝብና ጎን ትቆማላችሁ? ወይስ ከአደገኞች፣ ከወንጀለኞች፣ ከባለገንዘቦችና ከባለኔትወርኮች ጋር ከምንጣላና ከምንጠቃ ብላችሁ ፍትሕና ዴሞክራሲን ትረግጣላችሁ? እስቲ እጃችሁን አውጡ፡፡ ይህንን አጀንዳ ያነሳነው

CALL FOR SIDAMA ON LINE PRESENTATION.

Image
EGENSHIIIISHSHA  SIDAAMU ILAMA BAALA IKKITINOONIR GOBBANO GIDDONO HEEDHIOONIRIRA BAALAHO SIDAAMU DIRRU SOORO AYAANA PAALTALKETE YINANNNI XAADOOSHSH TEKNOLOGE HORONSINNE AYIIRINSAMORA QIXXAANBANNI HEENOOMOTA QUMMI ASSINANNI: 1)SIDAAMA HEEDHINE TENNE QIXXAWORA ANIIMA ADHTINOONIRINA INSA AFFINOONNIRI  GOBBA HEEDHINE SIDAAMU BUDE ALAMETE DEERRINNI EGENAMRA HEDONNA HALCHO NOONNERI A) SID DAMU FICHHE AANA EGENO NOONERI WOSSINCHIMATE KOYIINSANNERA HASSIDHINANNIRI SIDAAMU SIRBA , DHAGGE, WOLLE EGENO NO FIICHE LAINOHUNNI SHIQSHINARA HASSIDHNANNIRI BAALAHO 4/8/13 geeshsha ane Ledo xaande Hassanbeena Dirru Soorro tenne Miteenni ALAMETE DEERRINI Ayyrinso!!! CALL FOR SIDAMA ON LINE PRESENTATION. In Order to celebrate SIDAMA NEW YEAR FICHEE Celebration ON LINE . WE are organizing pall talk commiunication technology on line. Therefore: 1)Those who are in charge of Coordination of FICHEE Celebration Committee in sidaama or those of you who know their contact numbers and address you are invited

ሲዳማን ጨምሮ በደቡብ ክልል ተፋሰስ አካባቢ አንድ ቢሊዮን ችግኝ ይተከላል

Image
አዋሳ ሐምሌ 25/2005 በደቡብ ክልል በበጋ ወቅት በተፋሰስ በለማ ቦታ ላይ እስካሁን ግማሽ ቢሊዮን ሀገር በቀል ችግኝ መተከሉን የክልሉ ተፈጥሮ ሀብት ልማትና አካባቢ ባለስልጣን ገለጸ። የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅና የተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ የስራ ሂደት ባለቤት አቶ መሀመድኑር ፋሪስ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በክልሉ 14 ዞኖችና 4 ልዩ ወረዳ በበጋ ወቅት በህብረተሰብ ተሳትፎ በተከናወነ ተፋሰስ ላይ ችግኞች እየተተከሉ ነው። ለተከላ ከተዘጋጀው አንድ ቢሊዮን ዋንዛ ፣ጥቁር እንጨት ፣ቀረሮ ፣ዝግባና ሌሎች ሀገር በቀል ዝርያ ያላቸው ችግኞች መካከል ካለፈው ሰኔ ወር ጀምሮ እስካለፈው ሳምንት ግማሽ ቢሊዮን የሚሆን ችግኝ ተተክሏል ብለዋል። የመለስ ዜናዊን መታሰቢያ አንደኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ከሐምሌ 27 ጀምሮ በሚከናወን ዘመቻ ቀሪው ግማሽ ቢሊዮን ችግኝ የሚተከል መሆኑን ገልጸው በክልሉ ከ3 ሺህ በላይ ቀበሌዎች ለመታሰቢያ የሚሆን ፓርክ እንደሚቋቋም ተናግረዋል። በዘመቻው ከ3 ሚሊዮን በላይ አርሶ አደሮችና በጎ ፈቃደኞች የሚሳተፉ መሆኑን የጠቆሙት አቶ መሀመድ ኑር በክልሉ በለፉት ሁለት ዓመታት በዘመቻ ከተተከሉት ችግኞች መካከል ከ70 በመቶ የሚበልጠው መጽደቁን አስታውቀዋል። http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=10363&K=1

የሀዋሳ ከተማን የቄራ አገልገሎት የማሻሻል ፕሮጀክት በመጠናቀቅ ላይ ነው

Image
አዋሳ ሐምሌ 19/2005 የሀዋሳ ከተማን የቄራ አገልግሎት ለማሻሻል ከ25 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የሚካሄደው ፕሮጀክት ግንባታ የመጀመሪያው ምዕራፍ በመጠናቀቅ ላይ መሆኑን የከተማው ማዘጋጃ ቤት ገለጸ፡፡ በማዘጋጃ ቤቱ የመሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ መብራቴ መለሰ ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በአለም ባንክ ፣ በክልሉ መንግስትና በከተማው አስተዳደር ወጪ የሚካሄደው የቄራ አገልግሎት ግንባታ የተጀመረው በ2003 መጨረሻ ላይ ነው፡፡ በእቅዱ መሰረት የግንባታው የመጀመሪያው ምዕራፍ 90 በመቶ መጠናቀቁን አመልክተው ቀሪውና ቀጠዩ የውስጥ ድርጅት የማሟላት ስራ በሂደት ላይ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ ለስጋ ፍጆታ የሚውሉ በግና ፍየልን ጨምሮ በቀን ከ400 በላይ የእርድ እንስሳትን የማሰተናገድ አቅም ያለው አዲሱ የቄራ ፕሮጀክት ለሁለቱም ሀይማኖቶች የሚያገለግል መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የቀድሞው ቄራ ከበሬ በስተቀር የፍየልና የበግ እርድ ያልነበረው ፣ ከከተማው ፈጣን ዕደገትና ከተጠቃሚው አንጻር የማስተናገድ አቅም በቂ ባለመሆኑ ይህንን ለማሻሻል አዲስ ፕሮጀክት ተቀርጾ ወደ ተግባር መገባቱን ተናግረዋል፡፡ በህብረተሰቡ ጥያቄ መሰረት መንግስት በሰጠው ትኩረት የሚካሄደው ፕሮጀክቱ ከነባሩ የተሻለና የጥራት ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎቱን ለማቀላጠፍና ተደራሽ ለማድረግ እንዲሁም የከተማውን ዕደገትና የተጠቃሚውን ፍላጎት የሚያሟላ ነው ብለዋል፡፡ የፕሮጀክቱ ግንባታ ቀሪ ስራ የህንጻና ኤሌክቶሮ ሜካኒካል ስራን አካቶ በመጪው መስከረም 2006 መሉ በሙሉ ተጠናቆ ለአገልገሎት ሲበቃ ጥራትና ቅልጥፍናን ያሻሽላል፡፡ ህገወጥ እርድን በመቆጣጠር ከጤና ጋር ተያይዞ የሚመጡ ችግሮችን ለማስቀረት የሚያስችል ፕሮጀክት መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ የቀድሞው ቄራ እንዳለ ሆ