ለፍትሕ፣ ለዴሞክራሲ፣ ለልማት፣ ለአገርና ለሕዝብ በሀቅ፣ ከልብ፣ በእምነት፣ በትጋትና በተግባር እየሠራን ነው የምትሉ ባለሥልጣናት እጃችሁን አውጡ
አገራችን ኢትዮጵያ ከድህነት የተላቀቀች፣ ያደገችና የበለፀገች፣ ፍትሕና ዴሞክራሲ የነገሠባት አገር ሆና ለማየት የማይፈልግ ሀቀኛ ኢትዮጵያዊ የለም፡፡ ሁሉም ዜጋ ትፈልጋለህ ወይ ቢባል አዎን ይላል፡፡ ማልልኝ ቢባልም ‹‹ሙት!›› ይላል፡፡ በተለይ ባለሥልጣናት ይፈልጋሉ ወይ? እነሱም ይምላሉ ወይ? ቢባል አዎን ይፈልጋሉ አዎን ይምላሉ ተብሎ ብቻ የሚመለስ ሳይሆን፣ በፓርላማ ሕዝብ ፊት በአደባባይ አዎን ብለው ቃል ገብተዋል፤ ምለዋል፡፡ ጥያቄው የቃልና የመሀላ ብቻ ሳይሆን የተግባር ነው፡፡ በቃልማ ሕገ መንግሥቱም ያስገድዳል፡፡ እስቲ ለፍትሕ፣ ለሰብዓዊ መብት፣ ለዴሞክራሲ፣ ለልማት፣ ለአገር፣ ለሕዝብ በሀቅ፣ ከልብ፣ በእምነት፣ በትጋትና በተግባር እየሠራን ነን የምትሉ ባለሥልጣናት እጃችሁን አውጡ፡፡ በአንድ በኩል የአገር ሀብት የሚዳብርበት፣ አገር የሚለማበትና ድህነት የሚጠፋበት ሁኔታ ቢያጋጥም፣ በሌላ በኩል ደግሞ ጉቦ፣ የቪላና የተሽከርካሪ ጥቅማ ጥቅም የምታገኙበት ሁኔታ ቢኖርና ለመምረጥ መስቀለኛ መንገድ ቢያጋጥማችሁ የትኛውን ትመርጣላችሁ? የአገርና የሕዝብ ልማትን ወደ ጎን ገፍቶ የግል ጥቅምን ማካበት? ወይስ የግል ጥቅምን በመግፋት የአገርንና የሕዝብ ጥቅም ማስቀደም? እስቲ ከልብ የአገርና የሕዝብ ልማት የምታስቀድሙ እጃችሁን አውጡ፡፡ በተግባር ነው እያልን ያለነው፡፡ ሕዝብ ፍትሕ እያጣ መሆኑን ብታውቁና ማስረጃ ቢቀርብላችሁ፣ ሕግ የሚጣሰውና ፍትሕ እየታጣ ያለው ኔትወርክ በዘረጉ ወንጀለኞችና በባለገንዘቦች መሆኑን ብታውቁ ለፍትሕና ለዴሞክራሲ ብላችሁ ከሕዝብና ጎን ትቆማላችሁ? ወይስ ከአደገኞች፣ ከወንጀለኞች፣ ከባለገንዘቦችና ከባለኔትወርኮች ጋር ከምንጣላና ከምንጠቃ ብላችሁ ፍትሕና ዴሞክራሲን ትረግጣላችሁ? እስቲ እጃችሁን አውጡ፡፡ ይህንን አጀንዳ ያነሳነው