በሲዳማ ዞን ከ186ሺህ በላይ ወጣቶች የሚሳተፉበት የክረምት የበጎ ፈቃድ ፕሮግራም በይፋ ተጀመረ፡፡
photo http://www.flickr.com/photos/espsol/sets/72157632677473483/ አዋሳ ሐምሌ 11/2005 በደቡብ ክልል ሲዳማ ዞን ከ186ሺህ በላይ ወጣቶች የሚሳተፉበት የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ፕሮግራም ትናንት ተጀመረ ። የወጣቶችን የስራ ተነሳሽነትና ቁርጠኝነት እንዲጠናከር ሁሉም ባለድርሻ አካላት የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ የክልሉ ሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ጥሪ አቀረቡ፡፡ የፕሮግራሙ መጀመር ምክንያት በማድረግ በሲዳማ ዞን ቦርቻ ወረዳ ትናንት በተዘጋጀው መድረክ ላይ የዞኑ ሴቶች፣ ወጣቶችና ህፃናት ጉዳይ መምሪያ ኃለፊ ውይዜሮ ሻሎ ሮርሳ እንደገለጹት የዞኑ ወጣቶች ባለፉት አራት ዓመታት በበጎ ፈቃድ አገልግሎት በተደራጀ መንገድ በመሰማራት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ያደረጉ ተግባሮችን ሲያከናዉኑ ቆይተዋል ። የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶችን ወጣቶቹ ጉልበታቸውን፣ እውቀታቸውን ለአካባቢው ልማት በማዋል መልካም ተግባሮችን ከማከናወናቸዉም ሌላ ከማህበረሰቡ የተለያዩ እሴቶችን የቀስሙበት እንደነበር አስታዉቀዋል ። በዘንድሮም ክረምት ከዞኑ የተለያዩ ባለድርሻ አካላትና ከወጣት አደረጃጀቶች ጋር በመተባበር እራሳቸውንና ህብረተሰቡን ጠቅመው የዞኑን ልማት በሚያፋጥኑ የልማት ተግባሮች ለመሰማራት እንቅስቃሴ መጀመራቸውን ወይዜሮ ሻሎ አብራርቷል፡፡ የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ደኢህዴን/ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አክልሉ አዱሎ በበኩላቸው የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራ በከተማው ከተጀመረ ወዲህ ወጣቶች ለልማት ያላቸዉ ተነሳሽነትና ፍላጎት እየጨመረ መጥቷል ብለዋል፡፡ ወጣቶቹ በቆይታቸዉ የማጠናከሪያ ትምህርት በመስጠት ፣ የአካባቢ ጥበቃ፣ የጤና፣ የአካባቢ ፅዳትና ውበት፣ የትራፊክ ደህንነት፣ አረጋውያንና