በሀዋሳ ከተማ ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሀብቶች ፈቃድ ተሰጠ
አዋሳ ሐምሌ 10/2005 በሀዋሳ ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት ከ523 ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ 56 ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወስደው ወደ ስራ ለመግባት እየተዘጋጁ መሆናቸውን የከተማው ንግድና ኢንዱስትሪ መምሪያ ገለጸ፡፡ በከተማው የዘንድሮን ሳይጨምር 5 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር ካፒታል ያላቸው ሌሎች ባለሀብቶች በፈጠሯቸው የስራ እድሎች ከ28ሺህ 600 ለሚበልጡ ዜጎች ተጠቃሚ ማድረጋቸውም ተገልጿል፡፡ በመምሪያው የኢንቨስትመንት ፍቃድ መስጠት ፐርፎርመርና የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ወግደረስ ወንድሙ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በተጠናቀቀው የበጀት አመት ከ523 ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል በማስመዝገብ ፍቃድ የወሰዱት 56 ባለሀብቶች በኢንዱስትሪ ፣ በኮንስትራከሽን ፣በሆቴልና ሌሎች ማህበራዊ አገልገሎቶች ለመሰማራት ነው፡፡ ባለሀብቶቹ በግላቸው ባላቸውና በጊዜዊነት በተሰጣቸው ቦታዎች በአሁኑ ወቅት ወደ ስራ ለመግባት በዝግጅት ላይ መሆናቸውና ስራ የጀመሩ እንዳሉ አመልክተው በሙሉ አቅማቸው ሲንቀሳቀሱ 2ሺህ ሰዎች የስራ እድል ተጠቃሚ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል ብለዋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ለኢንቨስትመንት ልማት የሚውል 420 ሄክታር የሚጠጋ መሬት ዘንድሮ በጥናት ተለይቶ ለአልሚ ባለሀብቶች መዘጋጀቱንና ከዚሀም ውስጥ 270 ሄክታር በሀገር አቅፍ ደረጃ በማዕከላዊ መንግስት ለአንዱስትሪ ልማት የሚፈለግ ነው ብለዋል፡፡ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለኢንዱስትሪ ልማት ከተመረጡ አምስት ከተሞች መካከል ሀዋሳ አንዷ በመሆኗ ማዕከላዊ መንግስት ከውጪና ከሀገር ውስጥ ለሚጋብዛቸው አልሚ ባለሃብቶች እንዲውል ያዘጋጁት መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ቀሪው 150 ሄክታር መሬት በኢንዱስትሪ፣ በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣በሪል ስቴትና በአገልግሎት ዘርፍ ለሚሰማሩ ባለሀብ