ዩኒቨርስቲው 26 አዳዲስ ፕሮግራሞችን ለመክፈት እየሰራ ነው
ሃዋሳ ሐምሌ 8/2005 በድህረና ቅድመ ምረቃ መርሃ ግብር ለ26 አዲስ ፕሮግራሞች ስርዓተ ትምህርት ቀርጾ ተግባራዊ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን የሃዋሳ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ገለጹ፡፡ በዩኒቨርስቲው የሀዋሳ ግብርና፣ ህከምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በተለያየ ሙያ በመጀመሪያ፣ በሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ መርሀ ግብር ያሰለጠኗቸውን ከ900 የሚበልጡ ተማሪዎች ትናንት አስመርቀዋል፡፡ የዩኒቨርሰቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ዮሴፍ ማሞ እንደገለጹት በተጠናቀቀው የትምሀርት ዘመን ለ18 አዳዲስ የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች ስርዓተ ትምህርት ቀረጻ ተጠናቆ አንዳንዶቹ ተማሪዎችን ተቀብለው ለማስተማር እንቅስቃሴ ጀምረዋል፡፡ ከፕሮግራሞቹ መካከል አግሪ ቢዝነስና ቫሊዩ ቼን ማኔጅመንት፣ በባዮቴክኖሎጂ ፣በአግሮ ኢኮሎጂና ሰስቴነብል አግሪካልቸር ይገኙበታል፡፡ በህክምና ትምህርት ቤት ደግሞ በውሰጥ ደዌ፣ በሀጻናት ህክምና፣ በቀዶ ጥገና ፣ በማህጸን ጽንስ ስፔሻሊቲ የስልጠና ፕሮግራም ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ለመክፈት ዝግጅት መደረጉ ተመልክቷል፡፡ በቅድመ ምረቃ በቅርቡ ከተከፈተው የሲዳምኛ ቋንቋ በተጨማሪ ለ7 ፕሮግራሞች ስርዓተ ትምህርት ተቀርጾ በአንዳንዶቹ ተማሪዎችን ለመቀበል መዘጋጀታቸውን ዶክተር ዮሴፍ ጠቁመዋል፡፡ ይህም ዩኒቨርስቲው የቅበላ አቅሙን በመደበኛ ፕሮግራም ብቻ አሁን ያሉትን 17 ሺህ 080 ተማሪዎችን ቁጥር በ2007 ወደ 26 ሺህ ለማድረስ የተያዘው ፕሮግራም አንዱ አካል በመሆኑ ለዚህ ስኬት ከማስፋፊያ ግንባታዎች ባሸገር ቀልጣፋና ዘመናዊ አሰራር መዘርጋታቸውን ገልጠዋል፡፡ የመምህራንን አቅም በማጎልበት ረገድ በሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ ከ400 በላይ መምህራን በሀገር ውስጥና በውጪ የከፍተኛ ትምህርታቸውን እየተማሩ ይገኛል ብለዋል፡፡ በመንግስት የተጀመረው የልማት እንቅስቃሴ በጥናትና ምር