Posts

ለመሆኑ ያለተፎካካሪ የተደረገው የሲዳማ ምርጫ ውጤት ኣሽናፊዎቹን ጩቤ ያስረግጥ ይሁን?

Image
ደኢህዴን ያለምንም ተፎካካሪ የተወዳደረበት የቀበሌ ምክር ቤት ምርጫ ውጤት ይፋ ሆኗል። የምርጫው ውጤት ምርጫው ከመካሄዱ በፊት ጀምሮ የሚታወቅ ሲሆን ለፎርማሊት ተብሎ ውጤቱ ይፋ ተደርጓል ይለናል የኢዜኣ ዘጋባ። ለመሆኑ ያለተፎካካሪ የተደረገው የሲዳማ ምርጫ ውጤት ኣሽናፊዎቹን ጩቤ ያስረግጥ ይሁን? ለማንኛውም የምርጫ ውጤ ይፋ መደረጉን የተመለከተ ዜና ከታች ያንቡ። አዋሳ ሚያዚያ 14/2005 በደቡብ ክልል ሲዳማ ዞን ትናንት በተካሄደው የቀበሌ ምክር ቤት ምርጫ ለመራጭነት ከተመዘገበው ህዝብ ከ93 በመቶ በላይ መሳተፉን የዞኑ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ገለጸ፡፡ የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ ብርሃኑ ዱካሞ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹ በዞኑ አንድ ሺህ 507 የምርጫ ጣቢያዎች የድምፅ አሰጣጡ ስነስርዓት በሰላም ተጠናቆ ጊዜያዊ ውጤቱ ይፋ ሆኗል፡፡ በዞኑ 19 ወረዳዎችና ሁለት የከተማ አስተዳደር ከተመዘገው አንድ ሚሊዮን 116ሺህ በላይ መራጭ 93 በመቶ ድምፅ ድምፅ መስጠቱን ተናግረዋል፡፡ አንዳንድ የምርጫ ጣቢያ ሃላፊዎች፣ የህዝብ ታዛቢዎችና አስፈፃሚዎች በሰጡት አስተያየት ምርጫው ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ መካሄዱን ገልፀዋል፡፡

Ethiopia refutes US human rights report

Image
US condemns Ethiopia's human rights record. ADDIS ABABA: Ethiopian government officials are speaking out against a recent American State Department report that criticized the East African country’s human rights record, telling Bikyanews.com that the findings are “unwarranted.” “We have been pushing toward a more democratic society and we believe Ethiopia is a leader on human rights issues across Africa,” a foreign ministry official told Bikyanews.com on Saturday on condition of anonymity as he was not authorized to speak to the media. “If we want to condemn human rights violations, how about the US and their continued use of terror tactics, drones against civilians in the world. That is a crime and should be condemned,” the official continued. The US government on Friday commended activists, netizens, and journalists for their courage in advocating for universal human rights and expressed concern over the heightened crackdown on civil liberties, rebuking several countri

ፌዴሬሽኑ ከደቡብ እግር ኳስ አመራር ጋር የደረሰበት ስምምነት አለመግባባት ፈጠረ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከደቡብ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር ግጭት ውስጥ ገብቶ ከቆየ በኋላ፣ ባለፈው ሚያዝያ 1 ቀን 2005 ዓ.ም. ሁለቱ ፌዴሬሽኖች ባካሄዱት የጋራ ስብሰባ ከስምምነት ቢደርሱም፣ ስምምነቱ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈጻሚዎች ውስጥ አለመግባባት መፍጠሩ ተሰማ፡፡ የብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ሥራ አስፈጻሚዎች፣ በፌዴሬሽኑ ልዩ ልዩ ክፍሎች ወሳኝ ድርሻ ያላቸው ሙያተኞችና ሠራተኞች ባለፈው ረቡዕ ባደረጉት ስብሰባ፣ በፌዴሬሽኑ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ እንደተነጋገሩ፣ የፌዴሬሽን ምንጮች በተለይ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ እንደምንጮቹ፣ በዕለቱ በተካሄደው ስብሰባ በፌዴሬሽኑ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በርካታ ነጥቦች ተነስተው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን፣ በአንዳንዶቹ ነጥቦች ላይ የጋራ መግባባት ሲፈጠር፣ በአንዳንዶቹ ግን በተለይም ሥራ አስፈጻሚዎቹን ለሁለት በመክፈል ክፉና ደግ አነጋግሯል፡፡ በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው መካከል አለመግባባት ከፈጠሩት ነጥቦች፣ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንና በደቡብ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ተከትሎ፣ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ሳህሉ ገብረወልድ ያለ ሥራ አስፈጻሚው ይሁንታ ወደ ሐዋሳ በማምራት ከደቡብ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር ልዩነቱን ለማጥበብ የደረሱበት ስምምነት እንደሆነ ምንጮቹ ያስረዳሉ፡፡  በብሔራዊ ፌዴሬሽኑና በደቡብ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መካከል ተደረሰበት የተባለው ስምምነት ‹‹የደቡብ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መጋቢት 21 ቀን 2005 ዓ.ም. በሐዋሳ ጠርቶት የነበረው ስብሰባ ከመነሻው ሁለት ተልዕኮዎች እንደነበሩት፣ አንዱና የመጀመርያው በክልሉ ያለውን የስፖርት ልማት እንቅስቃሴ ለተጋባዥ የክልል ፌዴሬሽኖችና ከተማ አስተዳደሮች በማስጐብኘት ልምድ ልውውጥ ማድረግ፣ በሌ

የሲዳማ ኣርነት ንቅናቄ ኣባላት ለምርጫው ሲያደርጉ በነበረው ዝግጅት በምርጫው ቀን የምርጫውን ነጻ እና ገለልተኛነት ላይ በነበራቸው ጥርጣሬ የተነሳ የምርጫው ህደት እስክጠናቀቅ ድረስ የምርጫውን ስነስርኣት በትጋት ለመከታተል እንደምፈልጉ መግለጻቸውን ተከትሎ የምርጫ ባርድ ለሲኣን በጻፈው ደብዳቤ የሲኣን ኣባላት የምርጫ ድምጻቸውን ከሰጡ በኃላ በምርጫ ጣቢያው ኣከባቢ እንዳይቆዩ እና ወደየቤታቸውን እንዲሄዱ ኣዞ ነበር፤ ደብዳቤውን ከታች ያንቡት።

Image
የሲዳማ ኣርነት ንቅናቄ ኣባላት ለምርጫው ሲያደርጉ በነበረው ዝግጅት በምርጫው ቀን የምርጫውን ነጻ እና ገለልተኛነት ላይ በነበራቸው ጥርጣሬ የተነሳ የምርጫው ህደት እስክጠናቀቅ ድረስ የምርጫውን ስነስርኣት በትጋት ለመከታተል እንደምፈልጉ መግለጻቸውን ተከትሎ የምርጫ ባርድ ለሲኣን በጻፈው ደብዳቤ የሲኣን ኣባላት የምርጫ ድምጻቸውን ከሰጡ በኃላ በምርጫ ጣቢያው ኣከባቢ እንዳይቆዩ እና ወደየቤታቸውን እንዲሄዱ ኣዞ ነበር፤ ደብዳቤውን ከታች ያንቡት። 

የአውሮፓ ህብረት ባለስልጣናት በኢትዮጵያ የህዝቡ ነጻነት እንዲከበር ጠየቁ

ሚያዚያ  ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአውሮፓ ህብረት የፓርላማ መሪ ማርቲን ሹልትዝ ፣ የኮሚሺኑ ፕሬዚዳንት ሚስተር ጆሴ ማኑኤል  የጎበኙት ጠ/ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ባሮሶ እና የካውንስሉ ፕሬዚዳንት ሚ/ር ቫን ሩምፒ፣ ኢትዮጵያ በእሰር ላይ የሚገኙትን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋንና ርእዮት አለሙን ጨምሮ ሌሎች የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ፣ በአገሪቱ ውስጥ የሀዝቡ ነጻነት እንዲከበር፣ የጸረ ሽብር ህጉ እንዲሻሻል፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ለመቆጣጠር የወጣው ህግ እንዲከለስ ለጠ/ሚ ሀይለማርያም ደሳለኝ ጥያቄ አቅርበዋል። ባለስልጣናቱ ጥያቄውን ያቀረቡት አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ የአውሮፓን ህብረት በጎበኙበት ወቅት ነው። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ሰላም ለማስከበርና ሽብረተኝነትን ለመዋጋት እንዲሁም ድህነትን ለመቅረፍ ለማታደርገው ጥረት እውቅና እንደሚሰጡ የገለጡት ባለስልጣናቱ፣ ይሁን እንጅ  ትክክለኛ ልማት የሰው ልጆች ነጻነት ሳይከበር የሚመጣ ባለመሆኑ ፣ መንግስት የዜጎቹን ነጻነት እንዲያከበር ጠይቀዋል። የኮሚሺኑ ፕሬዚዳንት ሚ/ር ባሮሶ የሰብአዊ መብቶች ሁሉም የሰው ልጆች ሊያገኙዋቸው የሚገቡ አለማቀፍ መብቶች መሆናቸውን ለአቶ ሀይለማርያም ገልጸውላቸዋል። የካውንስሉ ፐሬዛድንት በበኩላቸው “ የማህበራዊ ልማት ስኬት የሚለካው በጠንካራና ግልጽ በሆነ ማህበረሰብ እንዲሁም መሰረታዊ የሆኑ የሰው ልጆች መብቶች ሲከበሩ ነው በማለት ተናግረዋል፡ አቶ ሀይለማርያም በኢትዮጵያ ውስጥ ዲሞክራሲያዊ ስርአት እንዲሰፍን፣ የዜጎች መብቶች አንዲከበሩና የሲቪክ ማህበረሰቡ ሚና አንዲጎለብት ጥረት እንደሚያደርጉ ተናግረዋል። ሶስቱም የ አውሮፓ ህብረት ባለስልጣናት በኢትዮጵያ የዲሞክራሲና የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ችግሮች ላይ ተመሳሳይ አቋም መያዛቸ