መለስ ሀዋሳን ክልል ለማድረግ ቃል ገብተው ነበር
መለስ ሀዋሳን ክልል ለማድረግ ቃል ገብተው ነበር የሲዳማ አገር ሽማግሌዎች አቶ መለስ እድሜያቸው አጭር እንደሚሆንና እንደሚቀሰፉ ነግረዋቸው እንደነበር ተሰማ። በክልሉ የአገር ሽማግሌ ከሚባሉት መካከል አንዱን በማነጋገር በተለይ ለጎልጉል የተላከው መረጃ እንደጠቀሰው መለስ እድሜያቸው ሊያጥርና በድንገት ሊቀሰፉ የሚችሉት የሲዳማን ባህላዊ ልብስ ለብሰው ከዋሹ ነበር። እንደመረጃው መለስ በ1997 ዓ ም ምርጫ ውጥረት ውስጥ በነበሩበት ወቅት አራት ተከታታይ ቀናት ሃዋሳ የብሄር ብሄረሰቦች አዳራሽ ውስጥ የብሄረሰቡን ተወላጆች ሰብስበው አነጋግረው ነበር። “አዲስ አበባ ያለው ድንኳናችን ፈርሷል። እዚህም ከፈረሰ በቃን ማለት ነው” በማለት የአገር ሽማግሌዎችን በተማጸኑበት ንግግራቸው መለስ አስቀድሞ ተቃውሞ ገጥሟቸው ነበር። ስብሰባው አዳራሽ ውስጥ ሙሉ ልብስ ለብሰው መድረክ ላይ ተቀምጠው የነበሩትን መለስ “ማን እዛ ላይ አወጣህ? አውርደንሃል” በማለት ሽማግሌዎች ሲናገሩ በወቅቱ የጸጥታ ሃይሎችና የአቶ መለስ ጠባቂዎች ተደናግረው ነበር። ሽማግሌዎቹ አቶ መለስን ከመድረክ አውርደው “አስቀድመህ ያገራችንን የባህል ልብስ ለብሰህ ነው መድረክ ላይ የምትወጣው” በማለት ከመድረክ አውርደው ጓዳ በማስገባት “ሴማ” የሚባለውን የባህል ቡሉኮ አለበሱዋቸው። “ይህንን የሚለብስ እውነት የሚናገር ብቻ ነው” በማለት አቶ መለስ መዋሸት እንደማይገባቸው ሽማግሌዎቹ አሳስበው እንደነበር የጠቆመው መረጃ፣ “ይህንን የሚለብስ መሪ የሆነ፣ እውነት የሚናገር ብቻ ነው። የሚዋሽ ይሞታል። እድሜው ያጥራል። ይቀሰፋል” በማለት በሲዳምኛ ደጋግመው መናገራቸውንና አቶ መለስም የተባሉትን ለማድረግ ተስማምተው እንደነበር አመልክቷል። በዚሁ መሰረት አቶ መለስ በ1997 ምርጫ ተከትሎ ካጋጠማቸው ቀው