በሲዳማ ብሔር ላይ እየደረሱ ያሉ ጭካኔ የተሞላባቸው አረሜናዊና ኢ-ሰብአዊ ድርጊቶች እንዲቆሙ የአለም-አቀፉ ማህበረሰብ ድጋፊ እንዲያደግርልን እንማፀናለን!!
ከማህበራዊ መረብ ላይ የተገኝ ጽሁፍ በ Sidaamaho Maganu No በሲዳማ ብሔር ላይ እየደረሱ ያሉ ጭካኔ የተሞላባቸው አረሜናዊና ኢ-ሰብአዊ ድርጊቶች እንዲቆሙ የአለም-አቀፉ ማህበረሰብ ድጋፊ እንዲያደግርልን እንማፀናለን!! በኢትዮጲያ ውስጥ የሕወኃት/ኢህአደግ ግፈኛና ቅኝ አገዛዝ ከተጀመረበት ከወረሐ ግንቦት 1983ዓ.ም እስከ ሚያዚያ 2005 ዓ.ም ድረስ ምርጫ ሳይሆን በየአምሰት አመት አንዴ ብዛት ያለው ወረቀት በአዲስ አበባ በሕወኃት ንግድ ድርጅቶች ታትሞ በካርቶኖች ታሽጎ በየክልሎች ከተከፋፈለ በኋላ የእለት ጉርስ ተሰፈሮላቸው ካድሬዎች ባቀረቡትና ማታ ላይ ይዘው በሚሸሹት ቦርሳ ውስጥ የሚከቱ ተቀጥሬው ምርጫ ቦርድ ወደሚባለው እሳት የላሱ የታጠቅ ካድሬዎች በየደረጃው በተሰገሰጉ መንጋ እየተላከ አራት ዙሪ ምርጫ መሳይ የእቃ እቃ ጨዋታ ሲጫወቱ አሳለፉ፡፡ በሦስተኛው ዙሪ ታፍኖ በብሶት ውስጥ ሆዱ እያረሬ የኖረው የኢትዮጲያ ሕዝብ ከዳር እስከ ዳር ተነቃንቆ አይቀጡ ቅጣት ሲቀጣው እራሱን ስዩሜ-እግዚአብሔር አድርጎ ሲንቀባረር የከረመው ዘረኛና ከፋፋይ የሕወኃት ባንዳ ቡድን ከረፈደ ባነነና በባዶ ጥላቻ በመነሳሳት በአዲስ አበባና በክልሎች ከትምህርት ቤት የሚመለሱ ጨቅላ ህጻናትን ጨምሮ ቁጥር ስፊር የሌላቸውን ህዝብ ህይወት አልባ አደረገ፡፡ "ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮሃል " እንዲሉ ሕዝብ የመረጣቸውን ተወካዮቹንና የህዝብ አይንና ጆሮ የሆኑ ጋዜጠኞችን ህገ-ወጥ በሆነ አካሄድ አስሮ አሰቃያቸው፤ ከሚወዱት ቤተሰባቸውና ህዝባቸው ለያቸው፤ የብዙዎቹን ቤተሰብ ለጎዳና ሕይወት ዳረጋቸው፤ የድራማ ድርሰት ተጻፈና የሀገር ሽማሌዎች የሚባሉ ገጸ-ባህሪያት በፕሮፌሰር ይስሃቅ ዋና ገጸ-ባህርነት ድራማው ለህዝብ ታዬና ብዙዎቹ አናዶ፤ ብዙዎቹ