Posts

የአካባቢ ምርጫ በኢትዮጵያ

የአዲስ አበባ ምክር ቤቶችና የአካባቢ ምርጫ መራጮች ዛሬ ድምፅ ሲሰጡ ዉለዋል። ዛሪ የጀመረዉ የኢትዮጵያ አራተኛ ዙር የአካባቢ የአዲስ አበባ እና የድሪደዋ ከተሞች አስተዳደር ምክር ቤቶች ምርጫ በቀጣይ ማጠቃለያ ልክ የዛሪ ሳምንት የሚከናወን መሆኑ ተነግሮአል። በዛሪዉ የመጀመርያ ፈረቃ ምርጫ በአዲስ አበባ የነበረዉን ሂደት የተከታተለዉ ወኪላችን ዮሃንስ ገብረ እግዚአብሄር፤ እንዲሁም የሱሉልታን አካባቢ የምርጫ ሂደት የተከታተለዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ሃ/ጊዮርጊስ ዘገባ አድርሰዉልናል። በሌላ በኩል ዛሪ በተካሄደዉ የክፍለ ከተማና የከተማ አስተዳደር ምርጫ ከሰላሳ አንድ ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ድምፅን ለመስጠት መመዝገቡን የሀገሪቱ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ማስታወቁ የሚታወስ ነዉ። ዛሪ ከቀትር በኃላ ዘጠኝ ሰዓት ግድም ላይ የምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ነጋ ዱፊን በስልክ አግኝተን ስለምርጫዉ አጠቃላይ ሂደት ጠይቀናቸዉ ነበር። አዜብ ታደሰ መስፍን መኮንን የአካባቢ ምርጫ አዲስ አበባ የአካባቢ ምርጫ ሱሉልታ የምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት ሃላፊ አስተያየት

የሲአን አቤቱታና የምርጫ ቦርድ ውሣኔ

Image
የሲዳማ አርነት ንቅናቄ - ሲአን “በአባሎቼ ላይ የሚፈፀመው በደል ከ2005ቱ ምርጫ እራሴን እንዳገልል አስገድዶኛል” ብሏል፡፡ የሲዳማ አርነት ንቅናቄ - ሲአን “በአባሎቼ ላይ የሚፈፀመው በደል ከ2005ቱ ምርጫ እራሴን እንዳገልል አስገድዶኛል” ብሏል፡፡ ለወረዳ ምርጫ ዕጩ የሆኑ አንድ ግለሰብ እንደተገደሉበትና ድብደባና ወከባ ያልተፈፀመበት አንድም ወረዳ እንደሌለ ድርጅቱ በመግለጫው ጠቅሷል፡፡ የምርጫ ቦርድ በበኩሉ ድርጅቱ ቀደም ሲልም ከምርጫው ሂደት ለመውጣት ዝግጅት ያደርግ እንደነበረ ገልጿል፡፡ ዝርዝሩን ከተያያዘው የመለስካቸው አምሃ ዘገባ ያዳምጡ ዝርዝሩን ከተያያዘው የመለስካቸው አምሃ ዘገባ ያዳምጡ

የምርጫ ዝግጅትና ተቃዉሞዉ በኢትዮጵያ፤ የሲዳማ አርነት ንቅናቄም በምርጫዉ እንደማይታፍ አስታዉቋል።

Image
ኢትዮጵያ ዉስጥ የመፊታችን ዕሁድ እና በሳምንቱ ዕሁድ በሚደረገዉ አካባቢ ምርጫ ከሠላሳ-አንድ ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ድምፁን ለመስጠት መመዝገቡን የሐገሪቱ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። የኢትዮጵያ መንግሥትን የሚቃወሙት ሠላሳ ሰወስት የፖለቲካ ፓርቲዎችን ግን በመጪዉ ዕሁድ በሚጀምረዉ አካባቢያዊ ምርጫ ላለመሳተፍ ወስነዋል። ኢትዮጵያ ዉስጥ የመፊታችን ዕሁድ እና በሳምንቱ ዕሁድ በሚደረገዉ አካባቢ ምርጫ ከሠላሳ-አንድ ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ድምፁን ለመስጠት መመዝገቡን የሐገሪቱ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። የቦርዱ ምክትል የሕዝብ ግንኙነት ሐላፊ አቶ ይስማ ጅሩ እንደገለጡት በሁለት በተከፈለዉ ምርጫ ሃያ-አራት የፖለቲካ ፓርቲዎችን የወከሉ ከስድስት ሚሊዮን በላይ እጩዎች ይወዳደራሉ። የአዲስ አበባዉ ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር አቶ ይስማ ጅሩን አነጋግሯቸዋል።የኢትዮጵያ መንግሥትን የሚቃወሙት ሠላሳ ሰወስት የፖለቲካ ፓርቲዎችን ግን በመጪዉ ዕሁድ በሚጀምረዉ አካባቢያዊ ምርጫ ላለመሳተፍ ወስነዋል። ፓርቲዎቹ እራሳቸዉን ከምርጫዉ ያገለሉበትን ምክንያት ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ማስረዳታቸዉን አስታወቀዋል። የጋራ ትብብር የመሠረቱት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያቀረቡት ቅድመ-ሁኔታ ካልተሟላ በምርጫዉ እንደማይሳተፉ በተደጋጋሚ አስታዉቀዉ ነበር። የጋራዉ ትብብር መሪዎች እንዳሉት ይሕን ምክንያታቸዉን ሠሞኑን ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች ገልፀዋል። በተመሳሳይ ዜና የሲዳማ አርነት ንቅናቄም በምርጫዉ እንደማይታፍ አስታዉቋል። የንቅናቄዉ ባለሥልጣናት እንደሚሉት አባላቶቻቸዉና ደጋፊዎቻቸዉ ይታሰራሉ፥ ይሸማቀቃሉም። ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዝር ዝር ዘገባ አለዉ። የምርጫ ዝግጅት የተቃዋሚዎች ውሳኔ

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መለስ ዋንጫ ሀዋሳ ከነማ መሪነቱን ያዘ

ሚያዝያ 3/2005 በአዲስ አባባ ስታዲየም ከኢትዮጵያ መድህን ያካሄደው ሐዋሳ ከነማ መሪነቱን ከደደቢት ተረክቧል። በሌላ ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከአዳማ ከነማ ባካሄዱት ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 3 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል። ፕሪምየር ሊጉን ሐዋሳ ከነማ  በ28 ነጥብ እየመራ ሲሆን አንድ ቀሪ ጨዋታ እያለው በ27 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ የሚገኘው ደደቢት ሚያዝያ 4/2005 ዓ.ም በ12 ሰዓት ከሲዳማ ቡና ወሳኝ ጨዋታ ያደርጋል። በተመሳሳይ ዜና የደደቢት አሰልጣኝ አብርሃም ተክለሃይማኖት ከኃላፊነታቸው ለቀዋል።

19 ቁጥርና የሐዋሳው ልጅ

Image
አዳነ ግርማ ከምርጥ አስር አፍሪካዊ ተጫዋቾች ውስጥ በመካተት የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ተጫዋች ነው፤   ጆሴፍ ፔፕ ጋርዲዮላ የባርሴሎናን ክለብ ማሠልጠን እንደጀመረ የመጀመሪያ ስራው ያደረገው የክለቡን ነባር ተጫዋቾች በማሰናበት በምትካቸው በዝነኛው የክለቡ ማሠልጠኛ ማዕከል ( ላሜሲያ ) ያደጉ ተጫዋቾችን በዘመቻ መልክ ማሰባሰብን ነበር። ከነዚህ ተመላሽ ካታሎናውያን መካከል በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በፈረንሳዊው አርሴን ቬንገር ለሚሰለጥነው አርሴናል አምበልና የመሃል ሜዳ አንቀሳቃሽ የነበረው ሴስክ ፋብሪጋስ ቀዳሚው ነበር። አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ተጫዋቹን ከሰሜን ለንደኑ ክለብ ለማስኮብለል ከተጠቀመባቸው አማራጮች መካከል አንዱ ራሱ በባርሴሎናና በስፔን ብሔራዊ ቡድን ሲጫወት ይለብሰው የነበረውን የማሊያ ቁጥር ( አራት ቁጥር ) እንደሚሰጠው ቃል መግባት ይገኝበታል። ሜክሲኮአዊው ራፋኤል ማርኬዝ ከባርሴሎና ጋር የነበረውን ኮንትራት አጠናቆ ወደ አሜሪካው ሜጄር ሶከር ሊግ ማምራቱን ተከትሎ ተሰቅሎ የቆየውን ማሊያ አውርዶ ለወጣቱ ጨዋታ አቀጣጣይ ሲሰጠው ተጫዋቹም በተደረገለት እንክብካቤ ከፍተኛ ደስታ ይሰማው ጀመር። ምክንያቱ ደግሞ በአርሴናል ይለብሰው የነበረውን አራት ቁጥር ማሊያ በአዲሱ ክለቡ ባርሴሎናም ለብሶ መጫወት ፍላጎቱ ስለነበር ነው። ከላይ የገለጽኩት ሐሳብ ለዕለቱ መጣጥፌ መግቢያ ይሆን ዘንድ የተጠቀምኩት ሐሳብ ነው። የዛሬው ጽሑፌ ማጠንጠኛ የሆነው ተጫዋች ተወልዶ ያደገው በደቡብ ክልል ዋና ከተማ ውቢቷ ሐዋሳ ሲሆን የመጀመሪያ ክለቡም የከተማዋ ተወካይ የሆነው ሐዋሳ ከነማ እግር ኳስ ክለብ ነው። በዚሁ ክለብ ከተከላካይነት እስከ አማካይ መስመር ባሉት ቦታዎች ላይ የተሰጡትን ሚናዎች በሚገባ እየተወጣ ማደጉ ለአሁኑ ሁ