19 ቁጥርና የሐዋሳው ልጅ
አዳነ ግርማ ከምርጥ አስር አፍሪካዊ ተጫዋቾች ውስጥ በመካተት የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ተጫዋች ነው፤ ጆሴፍ ፔፕ ጋርዲዮላ የባርሴሎናን ክለብ ማሠልጠን እንደጀመረ የመጀመሪያ ስራው ያደረገው የክለቡን ነባር ተጫዋቾች በማሰናበት በምትካቸው በዝነኛው የክለቡ ማሠልጠኛ ማዕከል ( ላሜሲያ ) ያደጉ ተጫዋቾችን በዘመቻ መልክ ማሰባሰብን ነበር። ከነዚህ ተመላሽ ካታሎናውያን መካከል በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በፈረንሳዊው አርሴን ቬንገር ለሚሰለጥነው አርሴናል አምበልና የመሃል ሜዳ አንቀሳቃሽ የነበረው ሴስክ ፋብሪጋስ ቀዳሚው ነበር። አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ተጫዋቹን ከሰሜን ለንደኑ ክለብ ለማስኮብለል ከተጠቀመባቸው አማራጮች መካከል አንዱ ራሱ በባርሴሎናና በስፔን ብሔራዊ ቡድን ሲጫወት ይለብሰው የነበረውን የማሊያ ቁጥር ( አራት ቁጥር ) እንደሚሰጠው ቃል መግባት ይገኝበታል። ሜክሲኮአዊው ራፋኤል ማርኬዝ ከባርሴሎና ጋር የነበረውን ኮንትራት አጠናቆ ወደ አሜሪካው ሜጄር ሶከር ሊግ ማምራቱን ተከትሎ ተሰቅሎ የቆየውን ማሊያ አውርዶ ለወጣቱ ጨዋታ አቀጣጣይ ሲሰጠው ተጫዋቹም በተደረገለት እንክብካቤ ከፍተኛ ደስታ ይሰማው ጀመር። ምክንያቱ ደግሞ በአርሴናል ይለብሰው የነበረውን አራት ቁጥር ማሊያ በአዲሱ ክለቡ ባርሴሎናም ለብሶ መጫወት ፍላጎቱ ስለነበር ነው። ከላይ የገለጽኩት ሐሳብ ለዕለቱ መጣጥፌ መግቢያ ይሆን ዘንድ የተጠቀምኩት ሐሳብ ነው። የዛሬው ጽሑፌ ማጠንጠኛ የሆነው ተጫዋች ተወልዶ ያደገው በደቡብ ክልል ዋና ከተማ ውቢቷ ሐዋሳ ሲሆን የመጀመሪያ ክለቡም የከተማዋ ተወካይ የሆነው ሐዋሳ ከነማ እግር ኳስ ክለብ ነው። በዚሁ ክለብ ከተከላካይነት እስከ አማካይ መስመር ባሉት ቦታዎች ላይ የተሰጡትን ሚናዎች በሚገባ እየተወጣ ማደጉ ለአሁኑ ሁ