የውሳኔዎች ሁሉ የበላይ ሕገ መንግሥቱን ተግባራዊ እናደርጋለን የሚለው ውሳኔ ነው
አራቱ የኢሕአዴግ ድርጅቶች በተናጠልም በጋራም ባካሄዱት ድርጅታዊ ጉባዔ የተለያዩ ውሳኔዎችን አላልፈዋል፡፡ ውሳኔዎቹን ተግባራዊ እናደርጋለን ብለውም ቃል ገብተዋል፡፡ ያለፈውን ጉዞ በመገምገም አዲስ ዕቅድ ካለም በማፅደቅ ተግባራዊ መሆን ያለባቸውን በመወሰን ተግባራዊ እናደርጋለን ማለት በኢሕአዴግ ብቻ ሳይሆን፣ በዓለም ዙሪያ ባሉ የፖለቲካ ፓርቲዎችም የሚደረግና የተለመደ ትክክለኛ አሠራር ነው፡፡ መወሰንና ውሳኔውን ተግባራዊ እናደርጋለን ማለቱ ላይ ምንም ተቃውሞ የለንም፡፡ ድጋፍ እንጂ፡፡ ከውሳኔዎች ሁሉ የበላይ የሆነው ውሳኔ ግን አለ፡፡ እሱንም ተግባራዊ እናደርጋለን ብላችሁ በይፋ ተናገሩ፣ አውጁ፣ ቃል ግቡ ብለን ደግመን ደጋግመን እንማፀናለን፡፡ የውሳኔዎች ሁሉ የበላይ የምንለው ሕገ መንግሥቱን ተግባራዊ እናደርጋለን የሚለው ውሳኔ ነው፡፡ ሕገ መንግሥታችን ለፍትሕ የቆመ ነው፡፡ ነገር ግን በተግባር ሲታይ የፍትሕ አካላት እየተዳከሙ፣ ገንዘብ፣ ጉቦና ሌላ ጥቅማ ጥቅምና ጣልቃ ገብነት እያዘቀጣቸው ይገኛል፡፡ ዜጎች ሕገ መንግሥታዊ መብታቸው ተጠብቆ የተሟላ ፍትሕ እያገኙ አይደሉም፡፡ ከሕገ መንግሥት ተገዥነት በላይ የግል ጥቅም ተገዥነት የበላይነት እየያዘ ነው፡፡ ስለሆነም ሕገ መንግሥቱ ይጠብቀናል ብሎ መተማመን የማይቻልበት ደረጃ ላይ እየደረስን ነው፡፡ ባለገንዘብ የሆነ ወንጀለኛ አይነካም፣ ያመልጣል፣ ይፈራል፣ ሕግ ጠባቂዎችን ያንበረክካል፣ ፍትሕ ሰጪዎችን ይገዛል፣ ሕገ መንግሥቱን ያረክሳል፡፡ ሕገ መንግሥታችን ለመልካም አስተዳደር የቆመ ነው፡፡ መልካም አስተዳደር ግን በእጅጉ እየተጓደለ፣ እየተረሳና እየተረገጠ ነው፡፡ ጭራሽ አቤት የሚባልበት እየታጣ ነው፡፡ የሕዝብ አገልጋይ ተብሎ በሕገ መንግሥቱ የተቋቋመው አስተዳደር ፀረ ሕዝብ እየሆነና ከሕዝብ ጥቅም ይልቅ የግ