33ቱ ፓርቲዎች የምክትል ጠ/ሚኒስትሮቹን ሹመት ተቃወመ
Written by ሠላም ገረመው ኢራፓ “ስርአቱ ይስተካከል እንጂ ሹመቱን አልቃወምም” ብሏል በቅርቡ በአገሪቱ ጠ/ሚኒስትር በአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በፓርላማ ቀርቦ የፀደቀው የሁለት ምክትል ጠ/ሚኒስትሮች ሹመት ህገመንግስቱን የሚፃረር ነው ሲሉ በአዳማ ከተማ ፔቲሽን ተፈራርመው ለምርጫ ቦርድ ጥያቄዎቻቸውን ያቀረቡ 33 ፓርቲዎች ተቃወሙ፡፡ ኢራፓ በበኩሉ የኢህአዴግ ስርዓት ይስተካከል እንጂ ከህገመንግስት ውጭ ቢሆንም ለአገር እስከጠቀመ ድረስ ሹመቱን አልቃወምም ብሏል፡፡ የአገሪቱ ጠ/ሚኒስትር ሁለት ባለስልጣናትን በምክትል ጠ/ሚኒስትርነት ማዕረግ ለፓርላማ አቅርበው ማፀደቃቸው ህገመንግስቱን የጣሰ ተግባር ነው ብለዋል - ፓርቲዎቹ፡፡ ባለፉት ጊዜያትም በጥድፊያና ከህገመንግስቱ ጋር በሚፃረር መልኩ የወጡት የፀረሙስና የመያዶች የፕሬስና የፀረ ሽብር አዋጆች ሁኔታው ቀጣይ እንጂ አዲስ ነገር አለመሆኑን ያሳያል ብለዋል - በመግለጫቸው፡፡ “የአጀንዳው አቀራረብም ሆነ የሹመቱ አፀዳደቅ ከፓርላማው የአሰራር ስነስርዓት ጋር ያልተጣጣመና በተለመደው ጥድፊያ የተከናወነ ነው አጀንዳው ለፓርላማ አባላት በተለመደው አሰራር መሰረት ያልተሰራጨ ከመሆኑም በላይ በሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ከህገመንግስቱ አንፃር ሳይመረመርና ሳይታይ መፅደቁ ይህን ያረጋግጣል” ብለዋል ፓርቲዎቹ፡፡ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤትም በተለያዩ ጊዜያት የህገመንግስቱን ድንጋጌዎች የሚጥሱ አምዶችን ተቀብሎ ማፅደቁን ፓርቲዎቹ ጠቁመው፤ አሁንም ከዚህ ድርጊቱ ሳይቆጠብ በህገ መንግስቱ አንቀፆች 74፣ 75 እና 76 ሀገሪቱ አንድ ምክትል ጠ/ሚኒስትር እንደሚኖራትበግልጽ ቢቀመጥም ከህገመንግስቱ ውጪ ሌሎች ሹመቶችን ተቀብሎ ማጽደቁ ህገመንግስቱን መጣስ ነው ሲሉ ተችተዋል፡፡ ገዢው ፓ