የሲዳማ ሕዝቦች አርነት ንቅናቄን ጨምሮ የዘንድሮ ምርጫ ተቃዋሚ ፓርቲዎችንና ምርጫ ቦርድን ማወዛገብ ጀመረ
በታምሩ ጽጌ በሚያዝያ ወር 2005 ዓ.ም. የሚደረገው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤትና የአካባቢ ምርጫ ከወዲሁ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድንና የፖለቲካ ፓርቲዎችን ማወዛገብ ጀመረ፡፡ ቦርዱ ጥቅምት 15 ቀን 2005 ዓ.ም. “የምርጫ ሰሌዳ የምክክር መድረክ” በሚል በአዳማ ከተማ በተደረገው ውይይት፣ በወቅቱ ከተሳተፉት 66 የፖለቲካ ፓርቲዎች ከግማሽ በላይ የሚሆኑት፣ ቦርዱ ካዘጋጀው የመወያያ ርዕሰ ጉዳይ ውጭ የተለያዩ ጥያቄዎችን ማንሳታቸውንና ምላሽ ማጣታቸውን ተከትሎ አለመግባባት ተፈጥሯል፡፡ ቦርዱ ከምርጫ ሰሌዳው በኋላ በሚወጡ የምርጫ የማስፈጸሚያ ደንቦችና መመርያዎችን ረቂቅ አዘጋጅቶ ፓርቲዎቹን ለማወያየት በጠራው የውይይት መድረክ ላይ፣ 41 የሚሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተስማሙበትንና መስተካከል እንዳለበት ያመኑበትን ጥያቄ ማቅረባቸውን፣ በ34 ፓርቲዎች የተወከለውና ሰባት አባላት ያሉት ጊዜያዊ ኮሚቴ ጥቅምት 30 ቀን 2005 ዓ.ም. አስታውቋል፡፡ “በምርጫ ሰሌዳ ዙርያ ከመወያየታችን በፊት የአገሪቱ የፖለቲካ ምኅዳር መጥበብና የምርጫ ውድድር ሜዳው የተስተካከለ አለመሆን፣ ቀደም ብሎ የተደረጉ ምርጫዎች በአፈጻጸም ችግሮች የተተበተቡ መሆቸውን፣ በየደረጃው ያሉ የምርጫ ቦርድ አመራርና አስፈጻሚዎች ተዓማኒነትና ተቀባይነት ላይ ቅድሚያ ሰጥተን ብንወያይ ይገባል፤” የሚል ጥያቄ ከኢሕአዴግና አጋር የፖለቲካ ድርጅቶች ውጭ ያሉት 41 የፖለቲካ ፓርቲ ድርጅቶች ጥያቄ ማንሳታቸውን ኮሚቴው አስታውሷል፡፡ አንድነት ለፍትሕና ለዴሞክራሲ ፓርቲ፣ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት፣ ሰማያዊ ፓርቲ፣ የጌዴኦ ሕዝቦች ንቅናቄ፣ የከንባታ ሕዝቦች ኮንግረንስ፣ የሲዳማ ሕዝቦች አርነት ንቅናቄን ጨምሮ 34 የፖለቲካ ፓርቲዎች ከላይ ያነሷቸው ጥያቄዎች