Posts

የሲዳማ ሕዝብ መሠረታዊ ጥያቄ

በ Hagerselam Haroressa ከማህበራዊ መረብ ላይ የተገኘ ጽሁፍ የሲዳማ ሕዝብ መሠረታዊ ጥያቄ መግቢያ አገራችን ለአያሌ ዘመናት ለተለያዩ ሰው ሠራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች ተጋልጣ የቆየች በመሆኗ አብዛኛው ህዝቧ በድህነት አረንቋና በኋላቀርነት ቀንበር ተተብትቦ መኖሩ የማይካድ ታሪካዊ ሀቅ ነው :: የሲዳማ ህዝብም የዚሁ አስከፊ ሰቆቃ ተጠቂ በመሆኑ ይህንን ነባራዊ ችግር ለመታገልና ለመፍታት ፈርጀ - ብዙ ትግል ማድረግ በማስፈለጉ፣ እንዲሁም የችግሩን መሠረታዊ ምንጭ አጉልቶ ለማሳየትና የመፍትሔውንም አቅጣጫ ለመጠቆም የሚያስችል የትግል ስልት ያካተተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ጽሑፍ ለ ማዘጋጀት ተገደናል :: እንደሚታወቀው የሲዳማ ብሔር ባለፉት አፋኝ ፀረ - ዲሞክራሲያዊ ሥርዓቶች ሥር ከመውደቁ በፊት የራሱ የሆነ ባሕላዊ የአስተዳደር ሥርዓት (The Luwa System) ፣ ቋንቋና (Sidaamu Afoo) ባህል፣ የራሱ የሆነ ታሪካዊ አመጣጥ ያለው ህዝብ ሆኖ በአንድ ጆኦግራፊያዊ ክልል ሰፍሮ የሚኖር በአንድ ስነልቦና የተሳሰረ ታላቅ ብሔር እንደሆነ ይታወቃል :: ይሁን እንጂ ህዝቡ በእነዚያ አስከፊና አፋኝ ፀረ - ዲሞክራሲያዊ ሥርዓቶች ሥር ከወደቀ በኋላ በራሱ ማስተዳደር እንዳይችልና ነፃነት እንዳይኖረው ፣ በገዛ ክልሉ ሊኮራባቸው ቀርቶ በአደባባይ በቋንቋውና በባህሉ እንዳይጠቀምበት ይልቁንም እንዲያፍርበት ተደርጎ ቆይቷል ::  በአጠቃላይ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ልማት የበላይ ባለቤትነትና ተጠቃሚነት እንዳይኖረው በተለያዩ ሥውር ስልቶች ተከልክሎ ቆይቷል :: ከእነዚህ አስከፊና አፋኝ ፀረ - ዲሞክራሲያዊ ሥርዓቶች ለመላቀቅ በየሥርዓቱ በተናጠል፣ በቡድንና በተደራጀ መልኩ ሳይታገል ያለፈበት አንድም ጊዜ አልነበረም :: በተለይ የንጉሣዊው ሥርዓ

የሐዋሳ ፍርድ ቤት በአንድ የወንጀል ድርጊት ሁለት የተለያዩ ቅጣቶችን መወሰኑ እያነጋገረ ነው

Image
-    በአንደኛው ቅጣት 10 ዓመት በሌላኛው ደግሞ ዕድሜ ልክ እስራት ወስኗል በታምሩ ጽጌ በደቡብ ክልል የሐዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአንድ ወጣት ላይ በተፈጸመ የግድያ ወንጀል በቀረቡለት የተለያዩ ክሶች ላይ የተለያዩ የቅጣት ውሳኔዎችን መስጠቱ እያነጋገረ ነው፡፡ ድርጊቱ የተፈጸመው አማረ ሙሉጌታ በተባለ የ23 ዓመት ወጣት ላይ በሐዋሳ ከተማ ሚያዝያ 5 ቀን 2003 ዓ.ም. ምሽት ላይ መሆኑን፣ ሁለቱም የክልሉ የከፍተኛ መርማሪ ከሳሾች ክሶች ያስረዳሉ፡፡ የከተማው ከፍተኛ መርማሪ ከሳሽ መጀመርያ ለሐዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግንቦት 29 ቀን 2003 ዓ.ም. ክሱን ያቀረበ ሲሆን፣ ለክሱ መነሻ የሆነው ፍሬ ጉዳይ አማረ ሙሉጌታ በተባለ የ23 ዓመት ወጣት ላይ በሁለት ጓደኞቹ የተፈጸመን የግፍ አገዳደል ወንጀል የሚያስረዳ ነው፡፡ ከሳሽ በክሱ ላይ እንዳብራራው፣ ሟች አማረ ሚያዝያ 5 ቀን 2003 ዓ.ም. እስከ ሌሊቱ አጋማሽ ድረስ አፈወርቅ ሌሊሳና ውብሸት ደሞል ከሚባሉ ጓደኞቹ ጋር በተለያዩ ሬስቶራንቶችና ሆቴሎች ሲዝናኑ ያመሻሉ፡፡ ጓደኞቹ አስቀድመው በነበራቸው የመግደል ሐሳብ፣ ወጣቱን በተለያዩ መጠጥ ቤቶች በማዞርና በማጠጣት በስካር ራሱን እንዲስት ካደረጉት በኋላ፣ ወደ ሰዋራ ሥፍራ በመውሰድ ውብሸት የተባለው ጓደኛው ሲይዘው፣ ጌታሁን የተባለው ሌላኛው ጓደኛው በስለት የግራ ደረቱን እንደወጋው ክሱ ያብራራል፡፡ ጓደኞቹ ድርጊቱን ሌላ ሰው የፈጸመው ለማስመሰል ለመሞት በማጣጣር ላይ የነበረውን አማረ ሙሉጌታን በመሸከም አሴር ወደሚባል ሆስፒታል ቢወስዱትም፣ ሕክምና ሳይደረግለት ሕይወቱ ማለፉን የቅጣት ውሳኔው ሰነድ ያስረዳል፡፡ ጓደኞቹ በጥርጣሬ ተይዘው ከታሰሩ በኋላ ፍርድ ቤት ቀርበው በሰጡት ቃል፣ ጓደኛቸው መሆኑንና ለሦስት ዓመታት

Sidama Coffee and Arba Minch will clash in the southern state derby in Yirgalem.

Image
Addis Ababa, Ethiopia – Week 4 of the Ethiopia Premier League will continue here with current leaders Dedebit FC taking on Ethiopian Insurance; EEPCO hosting Adama and defending champions St. George entertaining newly promoted side, Ethiopian Water Works FC. Mugher Cement will face Harar Beer at home and Sidama Coffee and Arba Minch will clash in the southern state derby in Yirgalem. The league will continue on Monday with two matches featuring Ethiopian Coffee vs Hawassa and CBE vs Defence Force. After 3 matches, Dedebit and Harar Beer seat on top of the league with 7 points each, followed by EEPCO, Ethiopian Coffee and St. George FC. Week 4 Sunday, November 11 Dedebit v Insurance EEPCO v Adama Mugher v Harar Brewery Sidama Coffee v Arba Minch Water Works Sport v St George Monday, November 12: CBE v Defence Force Ethiopian Coffee v Awassa

ኢትዮጵያ ከቡና ለማግኘት ያሰበችውን ገቢ ለማሳካት በዘርፉ የተሰማሩ አካላት ተቀናጅተው ለመሥራት ተስማሙ

Image
አዲስ አበባ ህዳር 1/2005 ኢትዮጵያ ከቡና በዚህ ዓመት ለማግኘት ያሰበችውን ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ለማሳካት በዘርፉ የተሰማሩ አካላት የተቀናጀ ጥረት እንደሚያደርጉ የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የቡና ጉባዔ ተሳታፊዎች አረጋገጡ። በአዲስ አበባ ከተማ ላለፉት ሁለት ቀናት የተካሄደው ጉባዔ ተካፋዮች በማጠናቀቂያቸው ላይ እንደገለጹት የአገሪቱ ቡና በዓለም ገበያ ባለው ተቀባይነትና በተለይም ስፔሻሊቲ ቡና ባለው ተፈላጊነት ምርቱን በጥራትና በብዛት በማቅረብ በዕቅዱ የተያዘውን ገቢ ለማሟላት የጋራ ጥረት ያደርጋሉ። አገሪቱ ለዓለም ያበረከተችውን ቡና አልምታ ልትጠቀምባቸው የምትችላቸው ምቹ ሁኔታዎች እንዳሉ ተሳታፊዎቹ አመልክተው፣የቡናውን ልዩ ባህርያት በመመርኮዝ ልማቱንና ግብይቱን በማሳደግ የተሻለ ገቢ ለማግኘት እንደሚቻል አስረድተዋል። ለዚህም ባለድርሻ አካላት ተገቢ ሚናቸውን እንዲወጡ በተቀናጀ መንገድ መንቀሳቀስ እንደሚገባቸውም አሳስበዋል። ጉባዔው በቡና ምርትና ግብይት ሂደት የተሰማሩ አካላትን በማሳበሰብ የኢትዮጵያን ቡና ሁኔታ የሚያሳውቅበት መልካም አጋጣሚ መፍጠሩን የኢትዮጵያ ኮፊ ኤክስፖርተርስ አሶሴሽን የቦርድ አባል አቶ ታደሰ መስቀላ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት አስረድተዋል። ጉባዔው በቡናው ዘርፍ ያሉትን ችግሮችና መልካም አጋጣሚዎች በስፋት በመዳሰስ በቀጣይ መከናወን ያለባቸውን ተግባራት ለመለየት የሚያስችሉ ጥናታዊ ጽሁፎች እንደቀረቡበት አስታውቀዋል። ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ጉባዔው በየዓመቱ ኤግዚቢሽንና የመስክ ጉብኝትን በማካተት እስከ አራት ቀናት ቆይታ እንዲኖረው ለማድረግ ከስምምነት ላይ መደረሱን አቶ ታደሰ ተናግረዋል። ተሳታፊዎቹ ኢትዮጵያ ጥራቱ የተጠበቀ ቡና ተከታታይነት ባለው መንገድ ማቅረብ በምትችልበት፣የኢትዮጵያን ቡና በዓለም አቀፍ ገበያ ያ

ማሸነፍም መሸነፍም እንደ አሜሪካ ምርጫ!

Image
የኦባማ ማሸነፍና የኢህአዴግ 1ለ5 ስትራቴጂ ሚስታቸውን የሚወዱ መሪዎች እንፈልጋለን!በምርጫ 99 በመቶ ማሸነፍ ከመሸነፍ እኩል ነው!ከሁሉም በፊት መወያየት ያለብን የኢቴቪ ደባል ሆኖ ስለገባው የቻይና ኮሙኒስት መንግስት የቴሊቪዥን ጣቢያ /ሲሲቲቪ/ ነው፡፡ እንዴ --- እኔ እኮ እንዲህ አልመሰለኝም ነበር፡፡ ባለፈው ሰሞን  የቻይና ቴሊቪዥን ሃላፊዎች ከኢቴቪ ጋር በጋራ ለመስራት ስምምነት መፈራረማቸውን ስሰማ ትከሻዬን የከበደኝ ለካ ለዚህ ነው፡፡ በቃ ደስ አላለኝም ነበር፡፡ እናንተ ነገሩ ቀልድ እንዳይመስላችሁ - ቻይና በአጭር ጊዜ ውስጥ አፍሪካን በሙሉ ኮሙኒስት ካላደረገች ታዘቡኝ፡፡ አረ አያያዟ አያምርም! ኢህአዴግማ ደስታው ነው - በሰበቡ የኮሙኒስትነት አራራውን ይወጣብናል! /እንኳን ዘንቦብሽ --/  እኔ ግን ተናግሬአለሁ---አንድ ቀን አማን ነው ብለን ከእንቅልፋችን ስንነሳ እቺ ምስኪን አገር ኮሙኒስት ሆና እንዳትጠብቀን፡፡ የኢህአዴግን ባህል የማያውቁ የዋህ ዜጎች “እንዴ እኛ ሳንፈቅድ?” ሊሉ እንደሚችሉ እገምታለሁ /ሰውየው “ሚስትህ አረገዘች ወይ?” ቢሉት “ማንን ወንድ ብላ” አለ!/ የቀድሞው የአገሪቱ ፕሬዚዳንት የአሁኑ የተቃዋሚ ፓርቲ ሊ/መንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ያሉትን አልሰማችሁም? “ኢህአዴግ አስር ዓመት ሙሉ ሶሻሊስት ነኝ ሲል ቆይቶ ድንገት ተነስቶ “ነጭ ካፒታሊዝም” ተከታይ ነኝ አለኝ” ብለው ክህደት እንደተፈፀመባቸው ተናግረዋል እኮ፡፡ ስለዚህ እንደሳቸው “ሰርፕራይዝድ” እንዳትሆኑ! ወዳጆቼ--- የስነልቦና ዝግጅት ማድረግ እኮ ቀላል በረከት አይደለም፡፡ እንደው ሌላው ቢቀር ድንገት ፌንት ከማድረግ ይታደጋል፡፡ እኔ የምለው--- ባለፈው ሳምንት ሲሲቲቪ በኢቴቪ ያሰራጨውን ዜና ሰማችሁልኝ? አንደኛው የቻይና ዳያስፖራዎች ወደ አገራቸው እየተመለ