የሐዋሳ ፍርድ ቤት በአንድ የወንጀል ድርጊት ሁለት የተለያዩ ቅጣቶችን መወሰኑ እያነጋገረ ነው
- በአንደኛው ቅጣት 10 ዓመት በሌላኛው ደግሞ ዕድሜ ልክ እስራት ወስኗል በታምሩ ጽጌ በደቡብ ክልል የሐዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአንድ ወጣት ላይ በተፈጸመ የግድያ ወንጀል በቀረቡለት የተለያዩ ክሶች ላይ የተለያዩ የቅጣት ውሳኔዎችን መስጠቱ እያነጋገረ ነው፡፡ ድርጊቱ የተፈጸመው አማረ ሙሉጌታ በተባለ የ23 ዓመት ወጣት ላይ በሐዋሳ ከተማ ሚያዝያ 5 ቀን 2003 ዓ.ም. ምሽት ላይ መሆኑን፣ ሁለቱም የክልሉ የከፍተኛ መርማሪ ከሳሾች ክሶች ያስረዳሉ፡፡ የከተማው ከፍተኛ መርማሪ ከሳሽ መጀመርያ ለሐዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግንቦት 29 ቀን 2003 ዓ.ም. ክሱን ያቀረበ ሲሆን፣ ለክሱ መነሻ የሆነው ፍሬ ጉዳይ አማረ ሙሉጌታ በተባለ የ23 ዓመት ወጣት ላይ በሁለት ጓደኞቹ የተፈጸመን የግፍ አገዳደል ወንጀል የሚያስረዳ ነው፡፡ ከሳሽ በክሱ ላይ እንዳብራራው፣ ሟች አማረ ሚያዝያ 5 ቀን 2003 ዓ.ም. እስከ ሌሊቱ አጋማሽ ድረስ አፈወርቅ ሌሊሳና ውብሸት ደሞል ከሚባሉ ጓደኞቹ ጋር በተለያዩ ሬስቶራንቶችና ሆቴሎች ሲዝናኑ ያመሻሉ፡፡ ጓደኞቹ አስቀድመው በነበራቸው የመግደል ሐሳብ፣ ወጣቱን በተለያዩ መጠጥ ቤቶች በማዞርና በማጠጣት በስካር ራሱን እንዲስት ካደረጉት በኋላ፣ ወደ ሰዋራ ሥፍራ በመውሰድ ውብሸት የተባለው ጓደኛው ሲይዘው፣ ጌታሁን የተባለው ሌላኛው ጓደኛው በስለት የግራ ደረቱን እንደወጋው ክሱ ያብራራል፡፡ ጓደኞቹ ድርጊቱን ሌላ ሰው የፈጸመው ለማስመሰል ለመሞት በማጣጣር ላይ የነበረውን አማረ ሙሉጌታን በመሸከም አሴር ወደሚባል ሆስፒታል ቢወስዱትም፣ ሕክምና ሳይደረግለት ሕይወቱ ማለፉን የቅጣት ውሳኔው ሰነድ ያስረዳል፡፡ ጓደኞቹ በጥርጣሬ ተይዘው ከታሰሩ በኋላ ፍርድ ቤት ቀርበው በሰጡት ቃል፣ ጓደኛቸው መሆኑንና ለሦስት ዓመታት