ኢትዮጵያ ከእናት ወደ ልጅ የሚተላለፈውን የኤች.አይ.ቪ/ስርጭት ስርጭት ለመግታት ብዙ መሥራት ይጠበቅባታል
አዲስ አበባ ጥቅምት 17/2005 ኢትዮጵያ ከእናት ወደ ልጅ የሚተላለፈውን የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ቫይረስ ስርጭት በመግታት ረገድ ብዙ መሥራት እንደሚጠበቅባት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ አስታወቀ፡፡ ቢሮውና ኢንትራ ሄልዝ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ከእናት ለእናት አመቻች ቡድን ጋር በመስራት ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ከእናት ወደ ልጅ /ጽንስ/ እንዳይተላለፍ በተሰጠው አገልግሎት ተጠቃሚ የሆኑ የ200 ሕጻናት እናቶች ዛሬ የምስክር ወረቀት ተቀብለዋል፡፡ የቢሮ ኃላፊዋ ወይዘሮ ፋንቱ ጸጋዬ በዚሁ ጊዜ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ስርጭትን በመከላከል ውጤታማ እየሆኑ ከመጡ ጥቂት አገሮች አንዷ ብትሆንም፤ ከእናት ወደ ልጅ የሚተላለፈውን ስርጭት ለመከላከል የተጠናከረ እንቅስቃሴ ማድረግ ያስፈልጋል። በአሁኑ ወቅት ቫይረሱ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ በመግታት ረገድ ያለውን ክፍተት ለመድፈን በዓለም አቀፍ ደረጃ በሕጻናት ላይ የሚኖረውን የቫይረሱን አዲስ ስርጭት ሙሉ ለሙሉ ለማስቀረት የተያዘውን እቅድ በመቀበል ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ እንደምትገኝ ጠቁመዋል፡፡ የእቅዱ መተግበሪያ ዋነኛው መንገድም እናቶች በእርግዝና ወቅት ምርመራ እንዲያደርጉና ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩ ከሆነም አስፈላጊውን ሕክምናና የምክር አገልግሎት አግኝተው መከላከያ በመውሰድ ከቫይረሱ ነፃ የሆነ ሕጻን እንዲወልዱ ማድረግ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ለዚህም የጤና ተቋማትን ማስፋፋትና በሁሉም ተቋማት አገልግሎቱ እንዲሰጥ ማድረግ ወሳኝነት እንዳለው ኃላፊው ተናግረዋል፡፡ በዚሁ መሠረት ከተማዋ የነበሯትን የጤና ጣቢያዎች ቁጥር በማሳደግና አገልግሎቱን በማጠናከር ሰፊ ሥራ መከናወኑንና በግል ጤና ተቋማት ጭምር አገልግሎቱ መስፋፋቱን አመልክተዋል፡፡ የጤና ተቋማቱን ቁጥር ወደ 11