Posts

የተባበሩት መንግስታት የሰብኣዊ መብት ድንጋጌዎች

PREAMBLE Whereas recognition of the inherent dignity and of the equal and inalienable rights of all members of the human family is the foundation of freedom, justice and peace in the world, Whereas disregard and contempt for human rights have resulted in barbarous acts which have outraged the conscience of mankind, and the advent of a world in which human beings shall enjoy freedom of speech and belief and freedom from fear and want has been proclaimed as the highest aspiration of the common people, Whereas it is essential, if man is not to be compelled to have recourse, as a last resort, to rebellion against tyranny and oppression, that human rights should be protected by the rule of law, Whereas it is essential to promote the development of friendly relations between nations, Whereas the peoples of the United Nations have in the Charter reaffirmed their faith in fundamental human rights, in the dignity and worth of the human person and in the equal rights of men and women

Sidama to Sidamo to Sidama

Image
posted by  Luke Tiny changes are sometimes the most significant. The  Ethiopian Commodity Exchange  recently  renamed  one of that country’s most iconic products: Sidamo Coffee, long one of the best-recognized coffee brands in the world, will now be officially traded as Sidama Coffee. The switcharoo has passed with little fanfare, and many American roasters continue to offer their customers Sidamo—though this trend does seem to be changing. What’s the story here? Ethiopia’s Sidama zone (also formerly Sidamo) occupies the southwestern corner of that country, spreading out across a landscape of green hills from the great Rift Valley lakes of Abaya and Awasa. Coffee originated not far from here—the  details are debated , but the northern Rift Valley and the Horn of Africa are generally recognized as the ancestral, wild homeland of  arabica  coffee. The  Sidama people  have lived here for longer than any tradition can recall, part of the Kushitic cultural patchwork that exten

የኢሕአዴግ ታጋዮች ጡረታ ትግሉን ከተቀላቀሉበት ጊዜ ጀምሮ ሊሰላ ነው

Image
የቀድሞውን ወታደራዊ አገዛዝ የመገርሰስ ትግል ውስጥ የተሳተፉና በአሁኑ ወቅት በመንግሥት ተቋማት ውስጥ በማገልገል ላይ የሚገኙ የቀድሞ ታጋዮች ጡረታ (ማኅበራዊ ዋስትና) ትግሉን ከተቀላቀሉበት ጊዜ አንስቶ እንዲሰላ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ለሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት በጻፈው ደብዳቤ አሳሰበ፡፡ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ለመንግሥት ተቋማት የተሰራጨው ደብዳቤ ከሰኔ 13 ቀን 2004 ዓ.ም. ጀምሮ እንደሆነና ይህም ማለት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በሕይወት በነበሩበት ወቅት ነው፡፡  የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት ደብዳቤውን ያሰራጨው በሕግ ላይ ተመሥርቶ ይሁን አይሁን በእርግጠኝነት ለመናገር እንደማይችሉ የሪፖርተር ምንጮች የገለጹ ቢሆንም፣ ምናልባት ለሕዝብ ይፋ ያልሆነ መመርያ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ፀድቆ ሊሆን እንደሚችልና ደብዳቤውም በዚህ ላይ የተመሠረተ ሊሆን ይችላል ሲሉ ጥርጣሬያቸውን ገልጸዋል፡፡  ይህንን መረጃ በመንተራስ ሪፖርተር አንዳንድ በመንግሥት ሥራ ላይ የተሰማሩ የቀድሞ ታጋዮችን ለማነጋገር የሞከረ ሲሆን፣ ከእነዚህም ውስጥ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) በአባልነት እያገለገሉ ያሉ ይገኙበታል፡፡ ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁት እነዚሁ የምክር ቤቱ አባላት የመረጃውን ትክክለኝነት ያረጋገጡ ሲሆን፣ የምክር ቤቱ ጽሕፈት ቤት ጉዳዩን አስመልክቶ ባቀረበው ጥሪ መሠረት ማንነታቸውን የሚገልጽ፣ ትግሉን የተቀላቀሉበትን ወቅትና በአሁኑ ጊዜ የሚያገለግሉበትን የመንግሥት ተቋምና ሌሎች ጉዳዮችን በተዘጋጀ ቅጽ ላይ መሙላታቸውን ገልጸዋል፡፡  ይህንን ቅጽ ከሞሉ በኋላ ደግሞ የምክር ቤቱ ጽሕፈት ቤት ከሰሞኑ በድጋሚ ማስታወቂያ እንዳወጣ፣ ማስታወቂያውም የተሞላውን ቅጽ ተንተርሶ የመንግሥት ሠራተኞች ማ

ክልሎች ከፌዴራል መንግሥት በሚጋሯቸው ገቢዎች ላይ ጥያቄ አነሱ

በዮሐንስ አንበርብር ክልሎች ከፌዴራል መንግሥት ጋር የሚጋሯቸው የተለያዩ የገቢ ዓይነቶች መከፋፈያ ቀመር ጊዜው ያለፈበትና አሁን ያለውን የዕድገት ደረጃ ያላገናዘበ በመሆኑ እንዲሻሻል ጥያቄ አቀረቡ፡፡ የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ለፌዴራል መንግሥቱ ከሚሰጣቸው ሥልጣኖች አንዱ ከክልል መንግሥታት ጋር ያለውን የጋራ ገቢ እንዲሰበስብና ለክልሎቹ የሚገባቸውን ድርሻ እንዲያስተላልፍ ነው፡፡ በዚህም መሠረት የፌዴራል መንግሥትና የክልሎች የጋራ ገቢዎች የሚባሉት በሕግ ተወስነው ተለይተዋል፡፡ እነዚህም በፌዴራል መንግሥትና በክልሎች የጋራ ባለቤትነት ከተመሠረቱ የልማት ድርጅቶች የሚገኝ ገቢ፣ በክልል የተመሠረቱ ኃላፊነታቸው የተወሰነ የግል ማኅበራት (ፒኤልሲ) እና በክልሎች የሚገኙ የተለያዩ የተፈጥሮ ሀብቶችን ለማውጣትና ለመጠቀም ፈቃድ የተሰጣቸው ድርጅቶች ከሚከፍሉት ሮያሊቲ የሚገኝ ገቢ ናቸው፡፡ ከእነዚህ ዘርፎችና የገቢ ዓይነቶች የሚገኘውን ሀብት ክልሎች ከፌዴራል መንግሥት ጋር የሚከፋፈሉት በ1989 ዓ.ም በፌዴሬሽን ምክር ቤት ፀድቆ በሥራ ላይ እንዲውል በተደረገው ቀመር አማካይነት ነው፡፡ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በትናንትናው ዕለት ባደረገው ስብሰባ በዚህ ቀመር ላይ በዋነኝነት ተወያይቷል፡፡ የምክር ቤቱ የድጎማ፣ የበጀትና የገቢዎች ድልድል ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ የክልሎችን ጥያቄ በመንተራስ፣ በዚህ ዓመት የገቢ ማከፋፈያ ቀመሩን ለመፈተሽ ዕቅድ ይዟል፡፡ የኮሚቴው ሰብሳቢ የሆኑት የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንቱ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ሪፖርት፣ ቀመሩ አሁንም በሥራ ላይ የሚገኝ ቢሆንም ቀመሩ ግን በቂ ግንዛቤ ያልተጨበጠበት እንደሆነ፣ ባለድርሻ አካላትና ክልሎች በቀመሩ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት እንዲሰጣቸውና እንዲሻሻል ተደጋጋሚ ጥሪ ማቅረባቸውን ተናግረዋል፡፡ በአሁ

ደቡብ ግሎባል ባንክ በይፋ ሥራ ጀመረ

Image
አዲስ አበባ፡- በ266 ሚሊዮን 964 ሺ ብር የተፈረመና በ138 ሚሊዮን 901 ሺ 836 ብር የተከፈለ ካፒታል የተቋቋመው ደቡብ ግሎባል ባንክ በይፋ ተመርቆ ሥራ ጀመረ። ባንኩ በአዲስ አበባ በተለምዶ በቅሎ ቤት በሚባለው ስፍራ በሚገኘው ዋና መሥሪያ ቤቱ ትናንት ተመርቆ በተከፈተበት ወቅት የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ወርቁ ለማ እንደገለጹት፤ ባንኩ በ5ሺ 481 ባለ አክሲዮኖች የተቋቋመ ነው። ባንኩ የተከፈለ ካፒታል በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ውስጥ ወደ አንድ ቢሊዮን ብር ለማሳደግ አቅዶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን አመልክተው፤ ከነሐሴ 22 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ ለደንበኞቹ አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆኑንም ጠቁመዋል። በባንክ ዘርፉ ያለው ውድድር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን የተናገሩት ፕሬዚዳንቱ ውድድሩን ለማሸነፍ ባንኮች አሰራሮችን ለማሻሻል የቅርንጫፉችን ቁጥር መጨመርና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በአስፈላጊው ደረጃ ጥቅም ላይ ማዋላቸውን ገልፀዋል። እንደ ፕሬዚዳንቱ ገለፃ ባንኩ በወቅቱ ያለውን የውድድር ሁኔታ አሸናፊ ሆኖ በስኬት ጐዳና እንዲራመድ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት አቅዷል። ዘመናዊ የባንክ አሠራሮችን ተግባራዊ በማድረግ የወለድ አልባ ባንክ አገልግሎት የካርድና ኢ-ባንኪንግ አገልግሎቶች ለመስጠት ተዘጋጅቷል።  ባንኩ በተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች ቅርንጫፎችን ለመክፈት መዘጋጀቱን ጠቁመው፤ በሚቀጥለው ሳምንት የሐዋሳና ሆሳዕና ቅርንጫፎች ሥራ እንደሚጀምሩ አመልክተዋል። የደቡብ ግሎባል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ኑረዲን አውል በበኩላቸው በዕለቱ እንደገለጹት፤ ባንኩ በሥራ ላይ ባለው የመንግሥት ፖሊሲ ላይ በመመርኮዝ ለኢንቨስትመንትና በንግድ የሥራ ዘርፍ የተሰማሩ ባለሀብቶችን ጥረት ለመደገፍና ለባለአክሲዮኖች ተገቢውን ጥቅም ለ