Posts

ክልሎች ከፌዴራል መንግሥት በሚጋሯቸው ገቢዎች ላይ ጥያቄ አነሱ

በዮሐንስ አንበርብር ክልሎች ከፌዴራል መንግሥት ጋር የሚጋሯቸው የተለያዩ የገቢ ዓይነቶች መከፋፈያ ቀመር ጊዜው ያለፈበትና አሁን ያለውን የዕድገት ደረጃ ያላገናዘበ በመሆኑ እንዲሻሻል ጥያቄ አቀረቡ፡፡ የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ለፌዴራል መንግሥቱ ከሚሰጣቸው ሥልጣኖች አንዱ ከክልል መንግሥታት ጋር ያለውን የጋራ ገቢ እንዲሰበስብና ለክልሎቹ የሚገባቸውን ድርሻ እንዲያስተላልፍ ነው፡፡ በዚህም መሠረት የፌዴራል መንግሥትና የክልሎች የጋራ ገቢዎች የሚባሉት በሕግ ተወስነው ተለይተዋል፡፡ እነዚህም በፌዴራል መንግሥትና በክልሎች የጋራ ባለቤትነት ከተመሠረቱ የልማት ድርጅቶች የሚገኝ ገቢ፣ በክልል የተመሠረቱ ኃላፊነታቸው የተወሰነ የግል ማኅበራት (ፒኤልሲ) እና በክልሎች የሚገኙ የተለያዩ የተፈጥሮ ሀብቶችን ለማውጣትና ለመጠቀም ፈቃድ የተሰጣቸው ድርጅቶች ከሚከፍሉት ሮያሊቲ የሚገኝ ገቢ ናቸው፡፡ ከእነዚህ ዘርፎችና የገቢ ዓይነቶች የሚገኘውን ሀብት ክልሎች ከፌዴራል መንግሥት ጋር የሚከፋፈሉት በ1989 ዓ.ም በፌዴሬሽን ምክር ቤት ፀድቆ በሥራ ላይ እንዲውል በተደረገው ቀመር አማካይነት ነው፡፡ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በትናንትናው ዕለት ባደረገው ስብሰባ በዚህ ቀመር ላይ በዋነኝነት ተወያይቷል፡፡ የምክር ቤቱ የድጎማ፣ የበጀትና የገቢዎች ድልድል ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ የክልሎችን ጥያቄ በመንተራስ፣ በዚህ ዓመት የገቢ ማከፋፈያ ቀመሩን ለመፈተሽ ዕቅድ ይዟል፡፡ የኮሚቴው ሰብሳቢ የሆኑት የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንቱ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ሪፖርት፣ ቀመሩ አሁንም በሥራ ላይ የሚገኝ ቢሆንም ቀመሩ ግን በቂ ግንዛቤ ያልተጨበጠበት እንደሆነ፣ ባለድርሻ አካላትና ክልሎች በቀመሩ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት እንዲሰጣቸውና እንዲሻሻል ተደጋጋሚ ጥሪ ማቅረባቸውን ተናግረዋል፡፡ በአሁ

ደቡብ ግሎባል ባንክ በይፋ ሥራ ጀመረ

Image
አዲስ አበባ፡- በ266 ሚሊዮን 964 ሺ ብር የተፈረመና በ138 ሚሊዮን 901 ሺ 836 ብር የተከፈለ ካፒታል የተቋቋመው ደቡብ ግሎባል ባንክ በይፋ ተመርቆ ሥራ ጀመረ። ባንኩ በአዲስ አበባ በተለምዶ በቅሎ ቤት በሚባለው ስፍራ በሚገኘው ዋና መሥሪያ ቤቱ ትናንት ተመርቆ በተከፈተበት ወቅት የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ወርቁ ለማ እንደገለጹት፤ ባንኩ በ5ሺ 481 ባለ አክሲዮኖች የተቋቋመ ነው። ባንኩ የተከፈለ ካፒታል በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ውስጥ ወደ አንድ ቢሊዮን ብር ለማሳደግ አቅዶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን አመልክተው፤ ከነሐሴ 22 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ ለደንበኞቹ አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆኑንም ጠቁመዋል። በባንክ ዘርፉ ያለው ውድድር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን የተናገሩት ፕሬዚዳንቱ ውድድሩን ለማሸነፍ ባንኮች አሰራሮችን ለማሻሻል የቅርንጫፉችን ቁጥር መጨመርና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በአስፈላጊው ደረጃ ጥቅም ላይ ማዋላቸውን ገልፀዋል። እንደ ፕሬዚዳንቱ ገለፃ ባንኩ በወቅቱ ያለውን የውድድር ሁኔታ አሸናፊ ሆኖ በስኬት ጐዳና እንዲራመድ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት አቅዷል። ዘመናዊ የባንክ አሠራሮችን ተግባራዊ በማድረግ የወለድ አልባ ባንክ አገልግሎት የካርድና ኢ-ባንኪንግ አገልግሎቶች ለመስጠት ተዘጋጅቷል።  ባንኩ በተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች ቅርንጫፎችን ለመክፈት መዘጋጀቱን ጠቁመው፤ በሚቀጥለው ሳምንት የሐዋሳና ሆሳዕና ቅርንጫፎች ሥራ እንደሚጀምሩ አመልክተዋል። የደቡብ ግሎባል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ኑረዲን አውል በበኩላቸው በዕለቱ እንደገለጹት፤ ባንኩ በሥራ ላይ ባለው የመንግሥት ፖሊሲ ላይ በመመርኮዝ ለኢንቨስትመንትና በንግድ የሥራ ዘርፍ የተሰማሩ ባለሀብቶችን ጥረት ለመደገፍና ለባለአክሲዮኖች ተገቢውን ጥቅም ለ

ስለድጐማ በጀትና ገቢዎች ድልድል በቂ ግንዛቤ ለመፍጠር ታቅዷል

Image
አዲስ አበባ፡- በ2005 በጀት ዓመት የድጐማ በጀትና የገቢዎች ድልድልን በተመለከተ በቂ ግንዛቤ የማስፋፋት ሥራ እንደሚያከናውን ፌዴሬሽን ምክር ቤት አስታወቀ። በምክር ቤቱ የድጐማ በጀትና የገቢዎች ድልድል ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እና የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ትናንት በተካሄደው የምክር ቤቱ አራተኛ ዘመን ሦስተኛ ዓመት አንደኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ የቋሚ ኮሚቴውን የ2005 በጀት ዓመት ዕቅድና የትኩረት አቅጣጫዎች ባመለከቱበት ወቅት እንደገለጹት፤ ዘንድሮ ግንዛቤ የማስፋፋት ሥራ ትኩረት ተሰጥቶት ተግባራዊ ይደረጋል። የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላትንና የቋሚ ኮሚቴ አባላትን አቅም መገንባት፣ የክልል መንግሥታት የገቢ አሰባሰብና የቀመር ባለሙያዎችን አቅም ማጠናከር እንዲሁም የክልል ምክር ቤት አባላት፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትንና የልዩ ልዩ አደረጃጀቶች ተወካዮችን ግንዛቤ ማሳደግ ላይ በስፋት እንደሚሠራ ጠቁመዋል። የክልሎች ገቢ የመሰብሰብ አቅም የሌሎች አገሮችን ተሞክሮ በመውሰድና የአገሪቱን ተጨባጭ ሁኔታ በመገምገም እንዲጠና የሚደረግ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ሽፈራው፤ ሥራው በየወቅቱ መከናወን እንዲችልና ተቋማዊ ባለቤት እንዲኖረው ጥናታዊ አስተያየት ተዘጋጅቶ እንደሚቀርብ አመልክተዋል። ለድጐማ በጀት ቀመር ዝግጅት ከተለያዩ ምንጮች የተገኙ ልዩ ልዩ መረጃዎች ጥቅም ላይ የዋሉ ቢሆንም ለቀመር ዝግጅቱ ዋነኛ የመረጃ ምንጭ ሆኖ ያገለገለው ከደቡብ አፍሪካ ስታትስቲክሰ መሥሪያ ቤት የተገኘው እንደሆነ ገልጸዋል። በፌዴራል ደረጃ በአዲሱ የድጐማ በጀት ማከፋፈያ ቀመር ላይ አገራዊ መድረክ የማዘጋጀት ዕቅድ መኖሩን ያመለከቱት አቶ ሽፈራው፤ ከተያዘው የበጀት ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ በተደረገው የድጐማ በጀት ማ

የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለማቃለል አገራዊ የህዝብ ንቅናቄ ይካሄዳል

Image
አዲስ አበባ፡-በየሥራ መስኩ የሚታዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለማቃለል የሚያስችል ሕዝባዊና አገራዊ ንቅናቄ በተያዘው ዓመት እንደሚካሄድ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ አስታወቁ። የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ትናንት የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የአራተኛ ዙር የሥራ ዘመን ሦስተኛ ዓመት የጋራ ስብሰባ በከፈቱበት ወቅት እንደተናገሩት፤ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለማስወገድና የተገኙ ስኬቶችን ለማስጠበቅ የሚያስችል አገራዊ እንቅስቃሴ በዚህ ዓመት ይካሄዳል። በአገር አቀፍ ደረጃ በሚካሄደው መልካም አስተዳደርን የማጐልበት ሕዝባዊ ንቅናቄ የሚመለከታቸው አካላት የበኩላቸ ውን ሚና እንዲጫወቱ ጥሪ አቅርበዋል። ሕዝባዊና አገራዊ ንቅናቄው በአሁኑ ወቅት በተጨባጭ የሚታዩ ችግሮችን ነቅሶ በማውጣት የመፍታትና የሕዝብን እርካታ የማረጋገጥ ግብ ያለው መሆኑን ፕሬዚዳንቱ አመልክተው፤ ለዚህ ግብ መሳካት ሁሉም ሕዝብ በንቃትና በተደጋጋፊነት እንዲሣተፍና የመልካም አስተዳደር ራዕዩን እውንነት እንዲረጋገጥ የዘርፉ ተዋናዮች ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል። እንደ ፕሬዚዳንቱ ገለፃ፤ ላለፉት 21 ዓመታት በሀገሪቱ ዴሞክራሲያዊና መልካም አስተዳደር የሰፈነበት ሥርዓት ለመገንባት በተደረገው ጥረት የዜጎችና የሕዝቦችን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ለማስከበር ሰፊ እንቅስቃሴ ተደርጓል። ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን በፅናት ከማክበር ጀምሮ በነፃ የሕዝብ ምርጫ መንግሥትን እስከመመሥረት ድረስ በርካታ መሠረታዊ የዴሞክራሲያዊ ለውጥ ተግባራት ተከናውነዋል። ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን ለማስጠበቅና ለማጠናከር ሲባል የተቋቋሙት በየደረጃው ያሉት ምክር ቤቶች፣ የሕግ ተርጓሚና የአስፈፃሚው አካላት በሀገሪቱ የግልፅነትና የተጠያቂነት ሥር

በሲዳማ ዞን ዳራ ወረዳ የኑራ ቆራቴ አገልግሎት ህብረት ሥራ ማህበር በ7 ቀበሌያት ለሚገኙ 11 አንደኛ ደረጃ 1ኛና 2ኛ...፡፡

በሲዳማ ዞን ዳራ ወረዳ የኑራ ቆራቴ አገልግሎት ህብረት ሥራ ማህበር በ7 ቀበሌያት ለሚገኙ 11 አንደኛ ደረጃ  1ኛና 2ኛ ሳይክል ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ከ1ዐዐ ሺህ ብር በላይ ወጪ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ፡፡ የትምህርት ቁሳቁስ ተገዝቶ የተሰጣቸው ወላጆቻቻው የማህበሩ አባላት ለሆኑ ተማሪዎች ነው ተብሏል፡፡ የማህበሩ ሊቀመንበር አቶ ማቴዎስ ዲጋሳ በዚህን ወቅት እንዳሉት ተገዝቶ በተበረከተው የትምሀርት ቁሳቁስ 4 ሺህ 554 ተማሪዎች ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡ በተጨማሪም በተለያዩ ኮሌጆችና ዩኒቨርስቲዎች ለሚማሩ በርካታ ተማሪዎች የትራንስፖርትና የትምህርት ወጪ መሸፈኑንም ገልፀዋል፡፡ የወረዳው ግበይትና ህብረት ስራ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዘማች እርጥባ በበኩላቸው ማህበሩ እያደረገ የሚገኘው በጎ ተግባር አርሶ አደሩ የማህበሩ አባል በመሆኑ ብቻ ከራሱ አልፎ ቤተሰቡም ጭምር ተጠቃሚ መሆኑን ማረጋገጫ እንደሚሆን አመልክተዋል፡፡ ሌሎች ማህበራትም ይህን አርያ እንዲከተሉ የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ መልዕክታቸውን ማስተላለፋቸውን የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳይ ጽህፈት ቤት ዘግቧል፡፡ http://www.smm.gov.et/_Text/26MesTextN205.html