የተተኪው ጠቅላይ ሚኒስትር ፈተናዎች
ሽግግር - ፓርቲዎች ወደሚፎካከሩበት እውነተኛ ምርጫ እመርታ - የዜጎችን ኑሮ ወደ ሚያሻሽል የነፃ ገበያ ኢኮኖሚ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብና ማስነገር ብቻውን በቂ አይደለም። በተጨባጭ የዜጎችን ኑሮ የሚሻሽል የነፃ ገበያ ስርዓት ማስፋፋት ያስፈልጋል - ዘመኑ የቢዝነስ ዘመን ነውና። አመት እየቆጠሩ የፖለቲካ ምርጫ ማካሄድ ብቻውን በቂ አይደለም። የአገራችን የፖለቲካ ምርጫዎች፣ ዜጎች በነፃነት የሚሳተፉበትና ፓርቲዎች የሚፎካከሩበት መሆን አለበት - ዘመኑ የ”ዲሞክራሲ” ዘመን ነውና። አንድ ሁለት የቲቪ ቻናሎችን መጨመርና የኤፍኤም ጣቢያዎችን ማበራከት ብቻውን በቂ አይደለም። የግል ነፃ ሚዲያ እንዲስፋፋ መፍቀድ ይገባል - ዘመኑ የመረጃ ዘመን ነውና። ዜጎች ህግ አክባሪ እንዲሆኑ መጠበቅ ብቻውን በቂ አይደለም። ከሁሉም በፊት መንግስት ራሱ የህግ ተገዢ በመሆን የህግ የበላይነትን ማስፋፋት ይኖርበታል - ዘመኑ የመንግስት ገናናነትን ሳይሆን የመንግስት ቅነሳን የሚጠይቅ ነውና። ከጓዳ እስከ አደባባይ የዜጎችን ህይወት ለመቆጣጠር ከታች እስከ ላይ “1ለ5” በቡድንና በተዋረድ ከማደራጀት ይልቅ፤ እያንዳንዱ ሰው እንደዝንባሌው እንዲሰራና እንደፈቀደው እንዲተባበር የሚያነቃቃ የነፃነት መንፈስን ማስፈን ያስፈልጋል - ዘመኑ የፈጠራ ዘመን ነውና። በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካ፣ በፕሬስ ነፃነት፣ በህግ የበላይነትና በነፃነት መንፈስ ዙሪያ የተጠቀሱት አምስት ፈታኝ ስራዎች በሙሉ፤ ስልጣኔን የመገንባት የረዥም ጊዜ ፈተናዎች ናቸው ማለት ይቻላል። ቅድሚያ ለእርጋታ - ሹመት ያዳብር በእርግጥ ከዋና ዋናዎቹ ፈታኝ ስራዎች በፊት መቅደም ያለበት ሌላ ስራ አለ - የተረጋጋ ሁኔታን መፍጠር። “ኖርማላይዜሽን” ልንለው እንችላለን። ለምሳሌ፣ በፖለቲካው መስክ፣ መሪዎችን በጊዜ መሰየም ወ