የመለስ ሕልፈት በኢሕአዴግ ጫንቃ ላይ የሚያሳርፈው ታላቅ ሸክም አለ
በክንፈ ኪሩቤል ተስፋሚካኤል የኢትዮጵያ ሕዝብ ጀግናዬ ነው የሚለው መሪውን መለስ ዜናዊን በሞት ካጣበት ቀን ጀምሮ አክብሮቱንና ፍቅሩን በታላቅ ሐዘንና እንባ ገልጿል፡፡ መለስ ላይመለስ አርፎአል፡፡ ዕድሜውን ሙሉ ዕረፍት ወስዶ አያውቅምና፡፡ ብዙዎች እንደ ተዝናኑት አልተዝናናም፡፡ እርግጥ ነው ሥጋዊ ደማዊ ለሆነ ሰብዓዊ ፍጡር ሁሉ ሞት አይቀሬ ነው፤ ምድራዊ ሥልጣን ዘለዓለማዊ አይደለም፡፡ ገንዘብ፣ ሀብትና ንብረትን ትቶ መሰናበት የግድ ነው፡፡ ነገር ግን ለአገር፣ ለወገንና ለሕዝብ ታላቅና አኩሪ ሥራ ሠርቶ ማለፍ ግን ክብር ነው! ሲዘከርም ይኖራል፡፡ ኢሕአዴግ ታላቅና ፈታኝ ሁኔታ ከፊቱ ተደቅኖበታል ሆኖም ግን ጥበብና ማስተዋል፣ ትዕግሥትና እርጋታ በተሞላበት እንዲሁም ጨዋነትና ይቅርባይነት በታከለበት መንገድ አመራሩን ከቀጠለ ሁሉንም መሰናክል ማለፍ ይቻለዋል፡፡ አቶ መለስ በትግሉና ከትግሉ በኋላ ራሳቸውን በኢኮኖሚክስና በማኔጅመንት ትምህርቶች አስተምረው ዕውቀትን ያገኙና ለአገራቸው ዕድገት የቀሰሙትን ዕውቀት ወደ ተግባርም የለወጡ ሰው ነበሩ፡፡ ስለ መለስ የአዕምሮ ችሎታ የሚወዷቸው ቀርቶ የሚጠሏቸው እንኳን አይክዱትም፡፡ ይህንን አይነት ሰው መተካት ለጊዜውም ቢሆን ይከብዳል፡፡ ስለ መለስ ባህርይ እንዲሁም ስለ ሥራዎቻቸው ጠንካራና ደካማ ጎን እንዲሁም ስለ ትክክለኛ ውሳኔያቸውና ስለ ስህተቶቻቸው የታሪክ ጸሐፊዎችና ተመራማሪዎች ወደ ፊት ይጽፉታል ብሎ የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ ያምናል፡፡ ሆኖም ግን ለአንባብያን ማስታወስ የሚፈልገው ጉዳይ አለ፡፡ ይህ ጸሐፊ ከወራት በፊት በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ ያሰፈረው ጽሑፉ በአጭሩ እንዲህ ይላል፡፡ ‹‹በተለይ አሁን እንደሚታየው ብዙዎቹ የአገሪቱ ቁልፍ መሪዎች በዕድሜ እየገፉ ናቸው፡፡ ብዙዎቹም በሥራ ድካምና በሕመም ያሉ ይኖራሉ፡፡ አን