በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት ምክንያት በኢትዮጵያ የሥልጣን ሳይሆን የአመራር ብቃት ክፍተት ሊያጋጥም እንደሚችል አንድ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ጉዳዮች ተንታኝ አስታወቁ ። በአለም አቀፉ የፀጥታ ጉዳዮች ጥናት ተቋም አጥኚ ዶክተር መሐሪ ታደለ ለዶቼቬለ እንደተናገሩት በመለስ አለመኖር አገሪቱ የሥልጣን ክፍተት አያጋጥማትም እስካሁን የመረጋጋት ችግር እልታየባትምም ፣ወደፊት ግን የአመራር ብቃት ክፍተት ሊኖር ይችላል ። በፖለቲካው መስክ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት ደግሞ ገዥው ፓርቲ የምክክር ና የስምምነት መድረኮችን ማዘጋጀቱ ጠቃሚ ይሆናል ብለዋል ። ላለፊት 21 አመታት ኢትዮጵያን በፕሬዝዳንትነትና በጠቅላይ ሚኒስትርነት ከመሩት ከአቶ መለስ ዜናዊ ህልፈት በኋላ የገዥው ፓርቲ የኢህአዲግ አመራር እንዴት ይቀጥላል ? ኢትዮጵያስ ከመለስ በኋላ ከአለም አቀፉ ማህበረሰብ የምታገኘው ድጋፍና የሚኖራት ተቀባይነት ምን ይሆናል ? መለስስ በምን ይታወሳሉ የሚሉትና የመሳሰሉት ጥያቄዎች ማነጋገራቸውን ቀጥለዋል ። በአለምአቀፍ የፀጥታ ጉዳዮች ጥናት ተቋም ተመራማሪ ዶክተር መሐሪ ታደለ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአመራር ዘመናቸው በኤኮኖሚና ማህበራዊ መስኮች ለኢትዮጵያ አዳዲስ ውጤቶች ማሰገኘታቸው ይጠቅሳሉ ። በፖለቲካው መስክ ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይከተሉት የነበረው መርህ ብዙ ችግሮችና ቅሬታዎች ያስከተሉ እንደነበር ዶክተር መሐሪ ገልፀዋል ። ይም ሆኖ ሃገሪቱ መሠረታዊ እንቅስቃሴ ውስጥ እንድትገባ ያደረጉ ጠቅላይ ሚኒስትር ነበሩ ብለዋል ። ከእንግዲህ በኋላስ የሚለው ሌላው ጥያቄአችን ነበር ። ዶክተር መሃሪ እንደሚሉት በተለይ አቶ መለስ ጥሩ አመራር ሰጥተው ውጤት አሳይተዋል ባሉት የኢኮኖሚ መስክ የታዩ ለውጦችን መቀጠል ከባድ ፈተና መሆኑን ይገልፃሉ ። በፖለቲካ መስክ ደግሞ አሁ