የሲዳማ ሕዝብ ለአገር ዕድገትና ብልፅግና ከሌሎች የሀገሪቱ ብሔር ብሔርሰቦችና ሕዝቦች ጋር ተባብሮ እየሰራ ነው
ሃዋሳ ነሐሴ 9/2004 የሲዳማ ሕዝብ ቋንቋው፣ ባህሉና ማንነቱ ተክብሮለት ለአገር ዕድገትና ብልፅግና ከሌሎች የሀገሪቱ ብሔር ብሔርሰቦችና ሕዝቦች ጋር ተባብሮ እየሰራ መሆኑን የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አስታወቁ፡፡ የሲዳማ ሕዝብ የዘመን መለወጫ የፍቼ ጫምባላለ በዓልና የብሔሩ 18ኛው የቋንቋና ባህል ስምፖዚየም በሲዳማ ባህል አዳራሽ ትናንት በድምቀት ተከብረዋል፡፡ የፍቼ ጫምባላለ በዓልን ባህላዊ የአከባበር ስነ ስርዓት በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት /ዩኔስኮ/ ለማስመዝገብ ዝግጅት መደረጉም ተመልክተዋል፡፡ ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ የሲዳማ ብሔረሰብ ከሌሎች ብሔር ብሔርሰቦችና ሕዝቦች ጋር በመሆን ባካሄደው እልህ አስጨራሽ ትግል አምባገነኑን የደርግ ሥርዓት በመገርሰስ በሀገሪቱ የሰላም፣ የልማትና የዴሞክራሲ ሥርዓት እንዲሰፍን የድርሻውን ተወጥቷል፡፡ የሲዳማ ህዝብ በሀገሪቱ እየተገነባ ባለው የሰላም፣ የልማትና የዴሞክራሲ ሥርዓት ማንነቱ ተክብሮ በቋንቋው የመናገር፣ የመዳኘትና የመማር መብቱ ህገ-መንግስታዊ ዋስትና ማግኘት ችሏል ብለዋል፡፡ እንደ ርዕሰ መስተዳድሩ ገለጻ የሲዳማ ህዝብ በሥርዓቱ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብት በመከበሩ በክልሉ ብሎም በአገሪቱ ባለፉት ስምንት ተከታታይ ዓመታት በሁሉም ዘርፍ ለተመዘገበው ፈጣን ልማት ጉልህ አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡ የሲዳማ ህዝብ የኢትዮጵያን ህዳሴ በፅኑ መሰረት ላይ ለመገንባት እየተደረገ ላለው ሁለንተናዊ ጥረት ስኬት ከሌሎች ብሔር ብሔርሰቦችና ሕዝቦች ጋር በመሆን እያካሄደ ያለውን ፀረ-ድህነት ትግል አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል፡፡ የሲዳማ ተወላጆች የፍቼ ጫምባላለ በዓልን ጠብቀው ለተተኪው ትውልድ በማስተላለፍና የሌሎችንም ባህል በማክበር በድህነት ላይ እየ