ሲዳሙ ኣፎ ጭምሮ በ25 ቋንቋዎች የትምህርት መዛግብተ ቃላት እየተዘጋጁ ነው
ሐዋሳ (ኢዜአ)፡- የትምህርትን ጥራት በየደረጃው ለማረጋገጥ መንግሥት የሚደርገውን ጥረት ለማገዝ በኢትዮጵያ 25 የብሔረሰብ አፍ መፍቻ ቋንቋዎች የተጀመረው የትምህርት መዝገበ ቃላት ዝግጅት በመጠናቀቅ ላይ መሆኑ ተገለጸ፡፡ የመዝገበ ቃላቱ ዓላማና አስፈላጊነት ላይ ግንዛቤ ለማስጨበጥ በደቡብ ክልል ደረጃ የትምህርት ባለሙያዎች የተሳተፉበት የሁለት ቀናት አውደ ጥናት በሀዋሳ ከተማ ተካሄዷል፡፡ መዝገበ ቃላቱ እየተዘጋጀ ያለው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከ20 ዓመታት በላይ የማስተማር ልምድና ዕውቀት ባላቸው ምሁራን ከሁለት ዓመት በፊት በተቋቋመው ስፖትላይት የትምህርት ማበልጸጊያ ማዕከል በተባለ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ትብብር መሆኑ ተገልጿል። የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ መሐመድ አህመዲን በአውደ ጥናቱ ላይ እንደገለጹት የትምህርት ጥራትን በየደረጃው ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት ለማሳካት የትምህርት መፃሕፍት ግብአት አቅርቦት አስተዋጽኦው ከፍተኛ መሆኑን አስታውቀዋል። በክልሉ 14 ቋንቋዎች ሳቢና ማራኪ አቀራራብ ለህጻናት አመቺ በሆነ መልኩ ከተዘጋጁት የትምህርት መጻህፍት መካከል በ10 የአፍ መፍቻ ቋንቋዎች የቀረቡት በዝርዝር ታይተው ወደ ተግባር እንዲሸጋገሩ ተደርጓል ብለዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት የደቡብ ክልል ቋንቋዎችን ጨምሮ በሀገር ደረጃ በ25 የኢትዮጵያ ቋንቋዎች እየተዘጋጁ ያሉት የትምህርት መዘገበ ቃላት የትምህርትን ጥራት ለማስጠበቅ አስተዋጾኦ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡ የማዕከሉ ሥራ አስኪያጅ ዶክተር ብርሃኑ ቦጋለ እንዳስረዱት በኢትዮጵያ 25 ቋንቋዎች የትምህርት መዝገበ ቃላት መዘጋጀተው ለትምህርት ጥራት ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳለው ተናግረዋል፡፡ ተማሪዎች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ከተማሩ በኋላ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ለመማር እንደሚገ