Posts

ባለፈው ሳምንት ግጭት ተከስቶባቸው የነበሩት የማልጋ እና የወንዶ ገነት ወረዳዎች እየተረጋጉ መምጣታቸው ተገለጸ

Image
በፈዴራል ፖሊስ እና በመልጋ ወረዳ ነዋሪዎች መካከል የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ  በወረዳው የነበረው ከፍተኛ የፖለቲካ ውጥረት በመቀነስ ላይ ያለ ቢሆንም መንግስታዊ ስራዎች እንደቆሙ ናቸው። ግጭቱን ምክንያት ኣድርጎ ወደ ወረዳው የገባው የመንግስት የጸጥታ ኃይል እስከኣሁን ድረስ ጉጉማን ጨምሮ በወረዳው እንደሰፈረ ይገኛል። ኣንዳንድ የወረዳው ነዋሪዎች የጸጥታው ኃይል ከወረዳው በኣስቸካይ ለቆ እንዲወጣ በመጠየቅ ላይ ናቸው። ባለፈው ሳምንት በወረዳው ህዝብ እና በፊዴራል ፖለስ ኃይል መካከል በተፈጠረው ግጭት ከሁለቱም ወገን ሰዎች መጎዳታቸው ይታወሳል። በተያያዘ ዜና የማልጋ ወረዳ ግጭት ተከትሎ በወንዶ ገነት ወረዳ ተፈጥሮ የነበረው ኣለመረጋጋት እንዲሁ በመስከን ላይ ነው።  

ኣቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከሁሉም የሲዳማ ወረዳዎች ከተወጣጡ ሽማግሌዎች ጋር በክልል ጥያቄ ዙሪያ ልመክሩ ነው

Image
ውስጥ ኣዋቂ ምንጮች ለወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ እንደጠቆሙት፤ ካለፈው ወር ጀምሮ በሲዳማ ዞን ውስጥ ክልልን ጨምሮ በሌሎች የመልካም ኣስተዳር ጥያቄዎች ላይ ዙሪያ በተቀጣጠለው ህዝባዊ ንቅናቄ በተመለከተ ከሲዳማ ሽማግሌዎች ጋር ለመምከር የክልሉ ርእስ መስተዳደር ቀጠሮ ይዘዋል። በሚቀጥለው ማክሰኞ ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው በዚሁ ምክክር ስብሰባ ላይ እንዲገኙ ከሁሉም የሲዳማ ወረዳዎች ከ 40 እስከ 50 የሚሆኑ የኣገር ሽማግሌዎች የተጋበዙ ሲሆን፤ የኣገር ሽማግሌዎቹ ምንን መሰረት ባደረገ መልኩ እንደተመረጡ ኣልታወቀም። እንደ የሲዳማ ፖለቲካ ተንታኞች ከሆነ እነዚህ ወደ ኣንድ ሺ የሚጠጉ ሽማግሌዎች የሲዳማ ህዝብ ያነሳውን የክልል ጥያቄ እንዲተው የማሳመን ስራ እንዲሰሩ በመንግስት የተመለመሉ ሳይሆኑ ኣይቀሩም። መንግስት በቅርቡ የሲዳማ ህዝብ ያነሳውን ክልል ይገባኛል ጥያቄ  ለመቀልበስ በተለያዬ መልክ ጥረት በማድረግ ላይ ሲሆን፤ በሚቀጥለው ሳምንት የምደረገው ጉባኤ የጥረቱ ኣካል ነው። ከኣስር ኣመት በፊት በተመሳሳይ መልኩ መንግስት ደጋፊ ሽማግሌዎችን በማሰባሰብ በወቅቱ የክልል ጥያቄ  ኣንስተው የነበሩት ሰዎች ጸረ ሰላም ኃይሎች በማስባል ማስኮነኑ ይታወሳል።

የሃዋሳ ከተማ ደኢህዴን ቅርንጫፍ ለጊዜው ባልታወቀ ምክንያት የኣመራር ሹም ሽር ተደረገ

Image
የከተማው የደኢህዴን ጽህፈት ቤት ከዚህ በፊት በተለያዩ የስልጣን እርከኖች ላይ ተመድበው ይሰሩ የነበሩት ካላ ሳሙኤል ሼባን ጨምሮ  ሌሎች ሁለት ኣመራራትን ከቦታቸው ኣንስቶ በምትካቸው ካላ ባጥሶ ዌጥሶን እና ሌሎች ሁለት ሰዎች ተክቷቸዋል። እነዚህ ከቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ የተነሱት ካላ ሳሙኤል ሼባ ወደ ዞን የተዛወሩ ሲሆን የተቀሩት ሁለቱ ደግሞ ወደ ክልል መወሰዳቸው ተነግሯል። ከስልጣን ላይ የተነሱት ሰዎች በምን ምክንያት እንደተነሱ ለጊዜው የታወቀ ነገር ባይኖርም ከቅርብ ጊዜ ጅምሮ በሲዳማ ዞን ብሎም በሃዋሳ ከተማ ባለው የፖለቲካ ውጥረት ሳይሆን እንደማይቀር ተገምቷል።

በሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር ላለፉት ሰባት እና ስምንት ወራት ክፍት በነበሩ የሹመት መደቦች ላይ ሰዎች መሾማቸው ተገለጸ

ከኣስተዳዳሩ የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት፤ የከተማዋን ምክትል ከንቲባ እና ንግድ እና ኢንዱስትሪ መደብን ጨምሮ በሌሎች ስድስት መደቦች ላይ ኣዳዲስ ሰዎች ተሹመዋል። እነዚህ የሹመት መደቦች ለረዥም ወራት ሰዎች ሳይመደቡባቸው መቆየታቸው በከተማዋ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ የስራ ሂዳት ላይ ክፍተት መፈጠራቸውን ኣንዳንድ የከተማዋ ነዋሪዎች ከዚህ በፊት ለወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ መጠቆማቸው የሚታወስ ሲሆን፤መደባው የነበረውን ክፍተት እንደሚሞላው ታምኗል። መደቦቹ ላይ ከዚህ በፊት እንደነበረው ሁሉ ሙሉ በሙሉ የሲዳማ ተወላጆች የተሾሙ ሲሆን፤ ሹመቱ የኣዋሳ ከተማ ኣስተዳደር ከሲዳማ እጅ ልነጠቅ ነው በሚል ተነስቶ የነበረውን ህዝባዊ ንቅናቄ ሊያበርደው ይችላል የሚል ግምት ተሰጥቶታል።

Wolde Amanuel Dubale Foundation launching and consultation Forum took place at Hawassa

Image
The official WaDF Launching and consultation Forum was held on 21 July 2012 at Sidama Cultural hall, Hawassa.  The Forum was attended by 200 participants including government officials, over sea partners, representatives of non-governmental organizations, community elders and other invited guests.  On the occasion Ato Shiferaw Shigute addressed the participants and he appreciated the initiations of the Foundation and pledged to render any support from the government side. The Founder and general manager of WaDF, Ato Melesse Woldeamanuel said that the Foundation was established to realize the dreams of the honored Ato Woldeamanuel Dubale through all-rounded development interventions. The honored guest from PPEP, Dr John Arnold shared his experiences and realization of his dreams by being inspired by the well known American Freedom Fighter, Marthen Luther King. He recited the slogan ” Yes We Can! Si Se Pude” and asked the audiences to recite after him. Ato Mi