Posts

በሲዳማ ዞን ጭኮ ወረዳ የተነሳው ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው

Image
ሰኔ ፲፱ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት የወረዳው የመረጃ ምንጭ እንደገለጠው ተቃውሞው የተነሳው ዛሬ 4 ሰአት ላይ ነው። በትናንትናው እለት እንደዘገብነው የካናዳ ጉብኝታቸውን አቋርጠው ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱት የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በቅርቡ በሲዳማ ዞን የተነሳውን ተቃውሞ ያነሳሱት ባለሀብቶችና ተቃዋሚዎች ናቸው በማለት የተናገሩትን ለመቃወም ነበር ዛሬ ሰለማዊ ሰልፉ የተጠራው። አቶ ሽፈራው ያደረጉትን ንግግር ያስቆጣቸው የጭኮ ወረዳ ነዋሪዎች በተወካዮቻቸው አማካኝነት ሰለማዋዊ ሰልፍ ለማድረግ እንዲፈቀድላቸው ጥያቄያቸውን ወረዳው አስተዳዳሪ ለሆኑት ለአቶ አሻግሬ ጀምበሬ ደብዳቤ አስገብተው ነበር። በዚህም መሰረት ዛሬ ጧት የተቃውሞ ሰልፉን ለማካሄድ ወደ ስታዲየሙ ሲያቀኑ የወረዳው የጸጥታ ዘርፍ ሀላፊ የሆኑት አቶ አለማየሁ ክፍሌ የፌደራል ፖሊስ በመጥራት የህዝቡ መሪዎች እንዲያዙ አድርገዋል። የከተማው ነዋሪ ተወካዮችን ለማስለቀቅ ከፌደራል ፖሊስ አባላት ጋር ውዝግብ ውስጥ መግባቱን ተከትሎ፣ ፖሊሶች ለተቃውሞ የመጣውን ሰላማዊ ሰው በቆመጥ እየደበደቡ ለመበትን ሲሞክሩ ቆይተዋል። ከሰአት በሁዋላ የከተማው ህዝብ በነቂስ በመውጣት የታሰሩት መሪዎች እንዲፈቱለት ፖሊስ ጣቢያውን በመክበብ ጥያቄውን አቅርቧል። ስቱዲዮ እስከገባንበት ጊዜ ድረስ ህዝቡ የፖሊስ ጣቢያውን እንደከበበ ነበር። ህዝቡን ውስጥ ለውስጥ ለአመጽ እንዲነሳ አድርገዋል በሚል የወረዳው ፖሊስ አዛዥ የሆኑት ዘላለም ላላም ታስረዋል። እንዲሁም ከመንግስት ሰራተኞች መካከል አቶ ገረመው ፊሳ፣ አቶ ኤፍሬም ተፈራ፣ ኢዛ እንዳለና ንጉሴ ታደሰ የታሰሩ ሲሆን፣ ባለሀብቱ አቶ አስቻለው በቀለም ታስረዋል። አቶ ገረመው ፊሳ፣ አቶ ኤፍሬም ተፈራ፣ አቶ

ደቡብ ኢትዮጵያ የሚኖረዉ የሲዳማ ብሔረሰብ እራሱን የቻለ መስተዳድር እንዲሰጠዉ ሰሞኑን በተከታታይ ባደረገዉ ሠላማዊ ሠልፍ ጠየቀ

Image
የሲዳማ አርነት ንቅናቄ እንዳስታወቀዉ የሕዝቡ ጥያቄ ሠላማዊና የሕገ-መንግሥቱን ድንጋጌዎች የጠበቀ ነዉ።በሌላ በኩል የደቡብ ኢትዮጵያ መስተዳድርን ከኦሮሚያ መስተዳድር ጋር በሚያዋስኑ አካባቢዎች በተከሰተ ግጭት ሰዎች መሞት፥ መቁሰላቸዉ ተነግሯል። ደቡብ ኢትዮጵያ የሚኖረዉ የሲዳማ ብሔረሰብ እራሱን የቻለ መስተዳድር እንዲሰጠዉ ሰሞኑን በተከታታይ ባደረገዉ ሠላማዊ ሠልፍ ጠየቀ።በደቡብ ኢትዮጵያ ርዕሠ-ከተማ በአዋሳና በአካባቢዉ ከተሞች አደባባይ የወጣዉን ሕዝብ ለመቆጣጠር መንግሥት በርካታ ፀጥታ አስከባሪዎች አስፍሯል።የሲዳማ አርነት ንቅናቄ እንዳስታወቀዉ የሕዝቡ ጥያቄ ሠላማዊና የሕገ-መንግሥቱን ድንጋጌዎች የጠበቀ ነዉ።በሌላ በኩል የደቡብ ኢትዮጵያ መስተዳድርን ከኦሮሚያ መስተዳድር ጋር በሚያዋስኑ አካባቢዎች በተከሰተ ግጭት ሰዎች መሞት፥ መቁሰላቸዉ ተነግሯል።ወኪላችን ታደሰ እንግዳዉ ከአዲስ አበባ ሁኔታዉን ተከታትሎታል። ሙሉ ዘጋባውን በሚቀጥለው ሊንክ ያዳምጡ ሠላማዊ ሠልፍና ግጭት በደቡብ ኢትዮጵያ

በመላው ኣለም ላይ የሚገኙ የሲዳማ ዳይስፖራ በሲዳማ ዞን ውስጥ እየተካሄደ ያለውን ህዝባዊ ንቅናቄ በንቃት በመከታተል እና በመደገፍ ላይ መሆናቸውን ገለጹ።

የዳይስፖራው ተወካዮች ለሲዳማ ወራንቻ የኢንፎርሜሽን ማእከል በላኩት መልእክት እንዳስታወቁት፤ የሲዳማ ህዝብ ያነሳቸውን የመልካም ኣስተዳደር እና የክልል ጥያቄዎችን ይደግፋሉ ለተግባራዊነቱም ከዞኑ ህዝብ ጎን ይቆማሉ። በሰሜን ኣሜሪካ፡ በታላቋ ብርታኒያ፡ በኖርዌይ፡ በኔዘርላንድ፡ በመካከላኛው ኣውሮፓ ኣገራት፡ በህንድ፡ በሳውድ ኣረቢያ እና ደቡብ ኣፍሪካ ነዋሪ የሆኑት የዞኑ ዳይስፖራ ኣባላት ህዝባዊ ንቅናቄውን በቅርበት በመከታተል ላይ መሆናቸውን ኣስታውቀዋል። ህዝባዊ ንቅናቄው ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በንቅናቄው ላይ የኣለም ህዝብ ትክክለኛ ግንዛቤ እንዲኖረው በተለያዩ የዜና ኣውታሮች የሚቀርቡ ዘገባዎች ከህዝባዊው ንቅናቄ ኣላማዎች ጋር የተጣጣሙ እንዲሆኑ የማደረግ ስራ በመስራት ላይ መሆናቸውን ኣስረድታዋል። ኣያይዘውም ለህዝባዊ ንቅናቄ መሳካት ኣስፈላጊውን ደጋፍ ለማደረግ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ባለፈው ሳምንት በሲዳማ ዞን የተነሳው ተቃውሞ ወደ ዘር ግጭት ሊያመራ ይችላል የሚለው የኢሳት ዘገባ የሲዳማ ተወላጆች ያነሱትን ዋነኛ ጥያቄ ያልዳሰሰ ነው በማለት የሲዳማ ተወላጆች አስተያየቶቻቸውን ልከዋል።

Image
ሰኔ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ባለፈው ሳምንት ከአዋሳ እና ከሲዳማ ዞን ጋር በተያያዘ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ በካናዳ ትምህርታዊ ጉብኝት ሲያደርጉ የነበሩት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ጉብኝታቸውን ትተው በመመለስ ትናንት መግለጫ ሰጥተዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ባለፈው ሳምንት በሲዳማ ዞን የተነሳው ተቃውሞ ወደ ዘር ግጭት ሊያመራ ይችላል የሚለው የኢሳት ዘገባ የሲዳማ ተወላጆች ያነሱትን ዋነኛ ጥያቄ ያልዳሰሰ ነው በማለት የሲዳማ ተወላጆች አስተያየቶቻቸውን ልከዋል። አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በአዋሳ ጉዳይ ለተነሳው ተቃውሞና ለጠፋው የሰው ህይወት ችግሩን የቀሰቀሱትን ለፍርድ እንደሚያቀርቡ ለክልሉ ራዲዮ ተናግረዋል። አቶ ሽፈራው የአዋሳ ጉዳይ በሀሳብ ደረጃ ተነሳ እንጅ ውሳኔ ያልተሰጠበት በመሆኑ ህዝቡ እንዲረጋጋ ጠይቀዋል። ከህዝቡና ፣ ከሀገር ሽማግሌዎችና ከሚመለከታቸው ሰዎች ጋር በመሆን ጉዳዩን እንደሚያብላሉትም ገልጠዋል። ፕሬዚዳንቱ ሰሞኑነ በተነሳው ግጭት የሰው ህይወት መጥፋቱንና ንብረት መውደሙን ቢገልጡም ሀላፊነቱን ለመውሰድና ይቅርታ ለመጠየቅ አልሞከሩም፣ ይልቁንም ችግሩን የፈጠሩት የተቃዋሚ አባላት ፓርቲና አንዳንድ ባለሀብቶች መሆናቸውን በመግለጥ ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀታቸውን ነው የተናገሩት። ሌሎች ወገኖች ግን ግጭቱን የቀሰቀሱት የደኢህዴግ ኢህአዴግ አባላት ናቸው:: አዋሳ አሁንም በፌደራል ፖሊስ እየተጠበቀች ነው። ወደ ይርጋለም በሚወስደው መንገድ ላይ ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆነ የፌደራል ፖሊስ አባላት ሰፍረው ይገኛሉ። ይህ በእንዲህ እንዳለ ባለፈው ሳምንት በሲዳማ ዞን የተነሳው ተቃውሞ ወደ ዘር ግጭት ሊያመራ ይችላል የሚለው የኢሳት ዘገባ የሲዳማ ተወላጆች ያነሱትን ዋነኛ ጥያቄ ያልዳሰሰ ነው በማለት

Freedom

Image