Posts

"An Assessment of the Impacts of Evangelical Christianity on the socio-cultural and religious transformation of Ethiopian society with specific reference to the southern region especially Sidama"

Seminar: Aklilu Lalegoa Submitted by administrator on Tue, 03/01/2012 - 15:25 Calendar Start:  22/02/2012 11:00 Timezone:  Europe/London "An Assessment of the Impacts of Evangelical Christianity on the socio-cultural and religious transformation of Ethiopian society with specific reference to the southern region especially  Sidama " http://www.ocms.ac.uk/content/index.php?q=node/358  

በሲዳማ ዞን ሁላ ወረዳ በግማሽ የበጀት አመት ቀጥታና ቀጥታ ካልሆኑ የገቢ አርዕስቶች ከ5 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ ገቢ መሰብሰቡን የወረዳው ገቢዎች ባለስልጣን ንዑስ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

በሲዳማ ዞን ሁላ ወረዳ በግማሽ የበጀት አመት ቀጥታና ቀጥታ ካልሆኑ የገቢ አርዕስቶች ከ5 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ ገቢ መሰብሰቡን የወረዳው ገቢዎች ባለስልጣን ንዑስ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ከበደ መኩሪያ እንደገለፁት ገቢው ከአምና ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከ1 ነጥብ 9 ሚሊዮን በላይ ብር ብልጫ እንዳለውና የእቅዱ አፈፃፀም 98 በመቶ መድረሱን ተናግረዋል፡፡ ለገቢው መገኘት ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ክትትልና የቅርብ ድጋፍ ማድረጋቸው እንዲሁም ከማዘጋጃ ቤት ጋር በቅንጅት መስራቱ አስተዋጽኦ ማድረጉን አስረድተዋል፡፡በጽህፈት ቤቱ የገቢ አሰባሰብ የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ፍስሐ በኬ በበኩላቸው ለባለሙያዎች በገቢ አሰባሰብ ስርአት የሚሰጠው የግልፀኝነት፣ የተጠያቂነትና የስነ ምግባር ትምህርት ስራቸውን በታማኝነት እንዲሰሩ አድርጓቸዋል ማለታቸውን የዞኑ ባህል ቱሪዝምና የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ዘግቧል ፡፡ ፡፡ http://www.smm.gov.et/_Text/8MegTextN104.html  

በሲዳማ ዞን አርቤጐና ወረዳ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማትን መሰረት ያደረጉ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን የወረዳው ግብርና ልማት ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

በሲዳማ ዞን አርቤጐና ወረዳ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማትን መሰረት ያደረጉ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን የወረዳው ግብርና ልማት ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ሽመልስ ሃጥሶ እንደገለፁት ዘንድሮ በወረዳው ውስጥ በሚገኙ ሁሉም ቀበሌዎች 38 የንኡስ ተፋሰሶችን በመለየት የተለያዩ ተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራዎች በመሰራት ላይ ይገኛሉ፡፡ ወረዳው ያለውን ከፍተኛ የውሃ ሀብት ከግምት በማስገባት ጽህፈት ቤቱ በተያዘነው የበጀት አመት 23ዐ ሄክታር መሬት በተለያዩ የውሃ አማራጮች ለማልማት ግብ መጣሉን ገልፀዋል፡፡በእስከ አሁኑ ከ26 ሄክታር በላይ መሬት መልማቱን በመጠቆም፡፡ አምዛዬ አዳነ ከበንሳ ቅርንጫፍ እንደዘገበው ፡፡ ፡፡ http://www.smm.gov.et/_Text/6MegTextN204.html   

በሲዳማ ዞን ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ህጋዊ ነጋዴዎችን በብዛትና በጥራት ማፍራት መቻሉን የዞኑ ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት መምሪያ አስታወቀ :

በሲዳማ ዞን ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ህጋዊ ነጋዴዎችን በብዛትና በጥራት ማፍራት መቻሉን የዞኑ ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት መምሪያ አስታወቀ፡፡መምሪያው ከአንድ ሺህ በላይ ለሚሆኑ ነጋዴዎች የንግድ ፈቃድ ሰጥቶ ወደ ስራ ማስማራቱንም ጨምሮ ገልጿል፡፡ በዞኑ 19 ወረዳዎችና 2 የከተማ አስተዳደሮች 1 ሺህ 4 መቶ 44 የንግድ ፈቃድ ምዝገባ ለማካሄድ ታቅዶ ከዕቅድ በላይ 1 ሺህ 6 መቶ 12 የንግድ ምዝገባ ማከናወን መቻሉን በመምሪያ የንግድ ማስፋፊያ ዋና የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ሲኮራ ኤቢሶ ገልፀዋል፡፡በበጀት አመቱ 1ዐ ሺህ 214 የሚሆኑ የንግድ ተቋሟት የምዝገባና የንግደ ፈቃድ አገልግሎት ማግኘታቸውን ገልፀው በዚህም 1 ሚሊዮን 52 ሺህ ብር ገቢ መገኘቱን አስረድተዋል፡፡ሪፖርተራችን ካሳ ጀንቦላ ከበንሳ ቅርንጫፋችን እንደዘገበው ፡፡ ፡፡

በይርጋለም ከተማ በትምህርቱ ዘርፍ የጐልማሶች ትምህርት ውጤት እያስገኘ መሆኑን የከተማዋ ከንቲባ ገለፁ :

Image
በይርጋለም ከተማ በትምህርቱ ዘርፍ የጐልማሶች ትምህርት ውጤት እያስገኘ መሆኑን የከተማዋ ከንቲባ ገለፁ፡፡የይርጋለም ከተማ ዋና አፈ-ጉባኤ አቶ ተክለስላሴ ዌኬሬ እንዳሉት ሀገሪቱ የተያያዘችውን የትራንስፎርሜሽን እቅድ ለማሣካት የሚቻለው የምክር ቤት አባላት በግንባር ቀደምትነት ተሳታፊ ሲሆኑ ነው ብለዋል፡፡ የከተማው አስተዳደር ከንቲባ አቶ ወንድወሰን ቦልካ በ6 ወራቱ የስራ ክንውን መከላከልን መሰረት ያደረገው የጤና ፖሊሲ ውጤት እያስገኘ መሆኑን ገልጿል ፡፡በተለይም በከተማ የጤና ኤክስቴንሽን ረገድ፡፡በትምህርት ዘርፍ የጐልማሶች ትምህርትን ለማጠናከር በተደረገው ጥረትም ውጤታማ ተግባር መከናወኑን ተናግረዋል፡፡ምክር ቤቱ የ3 ካቢኔ አባላትን ሹመት ያፀደቀ ሲሆን በቀጣይም ለሚሰሩ ተግባራት አቅጣጫ በማስቀመጥ መጠናቀቁን የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ዘግቧል፡፡ ፡፡