Posts

በሲዳማ ዞን አርቤጐና ወረዳ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማትን መሰረት ያደረጉ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን የወረዳው ግብርና ልማት ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

በሲዳማ ዞን አርቤጐና ወረዳ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማትን መሰረት ያደረጉ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን የወረዳው ግብርና ልማት ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ሽመልስ ሃጥሶ እንደገለፁት ዘንድሮ በወረዳው ውስጥ በሚገኙ ሁሉም ቀበሌዎች 38 የንኡስ ተፋሰሶችን በመለየት የተለያዩ ተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራዎች በመሰራት ላይ ይገኛሉ፡፡ ወረዳው ያለውን ከፍተኛ የውሃ ሀብት ከግምት በማስገባት ጽህፈት ቤቱ በተያዘነው የበጀት አመት 23ዐ ሄክታር መሬት በተለያዩ የውሃ አማራጮች ለማልማት ግብ መጣሉን ገልፀዋል፡፡በእስከ አሁኑ ከ26 ሄክታር በላይ መሬት መልማቱን በመጠቆም፡፡ አምዛዬ አዳነ ከበንሳ ቅርንጫፍ እንደዘገበው ፡፡ ፡፡ http://www.smm.gov.et/_Text/6MegTextN204.html   

በሲዳማ ዞን ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ህጋዊ ነጋዴዎችን በብዛትና በጥራት ማፍራት መቻሉን የዞኑ ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት መምሪያ አስታወቀ :

በሲዳማ ዞን ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ህጋዊ ነጋዴዎችን በብዛትና በጥራት ማፍራት መቻሉን የዞኑ ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት መምሪያ አስታወቀ፡፡መምሪያው ከአንድ ሺህ በላይ ለሚሆኑ ነጋዴዎች የንግድ ፈቃድ ሰጥቶ ወደ ስራ ማስማራቱንም ጨምሮ ገልጿል፡፡ በዞኑ 19 ወረዳዎችና 2 የከተማ አስተዳደሮች 1 ሺህ 4 መቶ 44 የንግድ ፈቃድ ምዝገባ ለማካሄድ ታቅዶ ከዕቅድ በላይ 1 ሺህ 6 መቶ 12 የንግድ ምዝገባ ማከናወን መቻሉን በመምሪያ የንግድ ማስፋፊያ ዋና የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ሲኮራ ኤቢሶ ገልፀዋል፡፡በበጀት አመቱ 1ዐ ሺህ 214 የሚሆኑ የንግድ ተቋሟት የምዝገባና የንግደ ፈቃድ አገልግሎት ማግኘታቸውን ገልፀው በዚህም 1 ሚሊዮን 52 ሺህ ብር ገቢ መገኘቱን አስረድተዋል፡፡ሪፖርተራችን ካሳ ጀንቦላ ከበንሳ ቅርንጫፋችን እንደዘገበው ፡፡ ፡፡

በይርጋለም ከተማ በትምህርቱ ዘርፍ የጐልማሶች ትምህርት ውጤት እያስገኘ መሆኑን የከተማዋ ከንቲባ ገለፁ :

Image
በይርጋለም ከተማ በትምህርቱ ዘርፍ የጐልማሶች ትምህርት ውጤት እያስገኘ መሆኑን የከተማዋ ከንቲባ ገለፁ፡፡የይርጋለም ከተማ ዋና አፈ-ጉባኤ አቶ ተክለስላሴ ዌኬሬ እንዳሉት ሀገሪቱ የተያያዘችውን የትራንስፎርሜሽን እቅድ ለማሣካት የሚቻለው የምክር ቤት አባላት በግንባር ቀደምትነት ተሳታፊ ሲሆኑ ነው ብለዋል፡፡ የከተማው አስተዳደር ከንቲባ አቶ ወንድወሰን ቦልካ በ6 ወራቱ የስራ ክንውን መከላከልን መሰረት ያደረገው የጤና ፖሊሲ ውጤት እያስገኘ መሆኑን ገልጿል ፡፡በተለይም በከተማ የጤና ኤክስቴንሽን ረገድ፡፡በትምህርት ዘርፍ የጐልማሶች ትምህርትን ለማጠናከር በተደረገው ጥረትም ውጤታማ ተግባር መከናወኑን ተናግረዋል፡፡ምክር ቤቱ የ3 ካቢኔ አባላትን ሹመት ያፀደቀ ሲሆን በቀጣይም ለሚሰሩ ተግባራት አቅጣጫ በማስቀመጥ መጠናቀቁን የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ዘግቧል፡፡ ፡፡

በሀዋሣ ከተማ በሳምንቱ ከነበረው የነጭ ጤፍ የገበያ ውሎ በሀላባ ከተማ የ2ዐዐ ብር ቅናሽ መስተዋሉን የክልሉ ግብይትና ህብረት ስራ ቢሮ በላከልን መረጃ አመለከተ ::

Image
በሀዋሣ ከተማ በሳምንቱ ከነበረው የነጭ ጤፍ የገበያ ውሎ በሀላባ ከተማ የ2ዐዐ ብር ቅናሽ መስተዋሉን የክልሉ ግብይትና ህብረት ስራ ቢሮ በላከልን መረጃ አመለከተ፡፡በሀላባ ከተማ 1 ኪሎ በርበሬ 42.5ዐ ሳንቲም ዋጋ ሲሸጥ በሀዋሣ ከተማ የ14 ብር ጭማሪ አሳይቷል ፡፡በዛሬው የገበያ ውሎ ዳሰሳችን በሳምንቱ የሀዋሣ፣ ሆሣዕናና ሀላባ ከተሞች ገበያ ውሎን እናስቃኛችሁአለን፡፡ በሳምንቱ ከነበረው የገበያ ውሎ ነጭ ጤፍ በሐዋሣ ከተማ ኩነታሉን 1 ሺህ 37ዐ ብር በችርቻሮ የተሸጠ ሲሆን የ7ዐ ብር ቅናሽ በማሳየት በሆሣዕና ከተማ 1ሺህ 3ዐዐ ብር በሀላባ ከተማ 2ዐዐ ብር ቅናሽ በማሳየት ኩንታሉ በችርቻሮ 1ሺህ 17ዐ ብር ሲሸጥ ሰንብቷል፡፡ከብርዕ ሰብል ወደ አገዳ ሰብል ስናመራ በቆሎ በሀላባ ከተማ ኩንታሉን በችርቻሮ 43ዐ ብር ተሽጧል፡፡ በሆሣዕና የ1ዐዐ ብር ጭማሪ በማሳየት 53ዐ ብር እንደዚሁም በሐዋሣ ከተማ 54ዐ ኩንታል በችርቻሮ ንግድ ተሽጧል፡፡ ወደ ጥራጥሬ እህል የገበያ ውሎ ስንሸጋገር ደግሞ አንድ ኩንታል አተር በሐዋሣ ከተማ በችርቻሮ 1ሺህ 62ዐ ብር ሲያወጣ በሆሣዕና ከተማ 12ዐ ብር ቅናሽ በማየት የ1ሺህ 5ዐዐ ዋጋ አውጥቷል፡፡ በሀላባ ገበያ በመሸጥ ከሆሣዕና ገበያ 14ዐ ጭማሪ ተስተውሏል፡፡የአትክልትና የስራስር ተክሎች ሳምንታዊ የገበያ ውሎን ስንመለከት አንድ ኪሎ ቲማቲም በሆሣዕና ከተማ 12 ብር ሲሸጥ የሰነበተ ሲሆን በሀላባ ከተማ የ3.5ዐ ሳንቲም በሀዋሣ ከተማ ደግሞ የ4 ብር ቅናሽ በማሳየት ተሽጧል፡፡ ቀይ ሽንኩር 1 ኪሎ ግራም በሐዋሳ ከተማ በችርቻሮ ተሽጧል፡፡ በሆሣዕናና በሀላባ ከተሞች ደግሞ የ9 ብር ዋጋ አውጥቷል፡፡ ነጭ ሽንኩርት በሆሣዕና ከተማ 1 ኪሎ 5ዐ ብር በሀላባ 46 ብር እንደዚሁም የሀዋሣ ከተማ የ14 ብር ቅናሽ በማሳት በ3

ሃዋሳ ከነማ በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ የ2ኛ ዙር የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታውን በአየር ሀይል ሜዳ ይጀምራል

Image
በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ መጋቢት 12/2004 ዓ.ም 9 ሰዓት ቢሾፍቱ ላይ አየር ሀይል እና የሀዋሳ ከነማ ይጫወታሉ፡፡ ባለፈው ቅዳሜ በፕሪምየር ሊግ ቀሪ ተስተካከይ ጨዋታ በቅዱስ ጊዮርጊስ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት የተሸነፈው አየር ሀይል የሁለተኛ ዙር የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታውን በሜዳው ሀዋሳ ከነማን በማስተናገድ ይጀምራል፡፡ አሰልጣኝ ክፍሌ ቦልተናን በማሰናበት አሰልጣኝ ንጉሴ ደስታን የቀጠረው አየር ሀይል በፕሪምየር ሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ በ9 ነጥብ እና 10 የግብ እዳ 14ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከመከላከያ በ2ኛው ዙር በመጀመሪያ ሳምንት ዛሬ መጋቢት 12/2004 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታድየም የሚያካሂዱት ጨዋታ ለሰኔ 12/2004 ዓ.ም እንደተላለፈ የኢትዮጰያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡ ፕሪምየር ሊጉን ቅዱስ ጊዮርጊስ በ30 ነጥብ ይመራል መብራት ሀይል በ28 ነጥብ ይከተላል፡፡ ደደቢት በ26 ነጥብ 3ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡የኮከብ ጎል አግቢነቱን ጌታነህ ከበደ ከደደቢት በ13 ጎል ይመራል፡፡መድሀኔ ታደሰ ከኢትዮጵያ ቡና በ11 ጎል ይከተላል፡፡

የዓለም ቡና ዋጋ ማሽቆልቆል በአገር ውስጥ ግብይት ላይ ተፅዕኖ እየፈጠረ ነው

Image
በዓለም የቡና ዋጋ ማሽቆልቆል የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለፈው ሳምንት እስከ 12 በመቶ ድረስ አውርዶት የነበረውን ዝቅተኛውን የመገበያያ ዋጋ ገደብ እንደገና ወደ አምስት በመቶ እንዲወርድ አደረገ፡፡ ምርት ገበያው ባሳለፍነው ሳምንት ዝቅተኛውን የግብይት ወለል ወደ 12 በመቶ እንዲወርድ ያደረገው፣ በዓለም አቀፍ ገበያ የቡና ዋጋ እየወረደ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ የአገር ውስጥ ግብይትም በተመሳሳይ ሁኔታ መቀነስ ይጠበቅበት ስለነበረ ነው ተብሏል፡፡ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር እሌኒ ገብረ መድኅን ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በአሁኑ ጊዜ እየታየ ያለው ዓለም አቀፍ የቡና የዋጋ ማሽቆልቆል በአገር ውስጥ ያለውን የግብይት ዋጋ ከዓለም አቀፉ ገበያ በላይ እንዲሆን አስገድዶት ነበር፡፡ ይህም በመደረጉ በሁለት ቀናት ውስጥ የቡና ዋጋ እንዲወርድና የመጫረቻ ዋጋውም በኒውዮርክ ገበያ ካለው ዋጋ ጋር ተቀራራቢ እየሆነ በመምጣቱ፣ ለሁለት ቀናት የተሠራበት የመገበያያ ገደብ ተመልሶ ወደ አምስት በመቶ ዝቅ እንዲል መደረጉን ዶ/ር እሌኒ አስረድተዋል፡፡ በምሳሌ ያቀረቡትም ባለፈው ሳምንት አንድ ሺሕ ብር ዋጋ የነበረው ቡና ከለውጡ በኋላ ዋጋው ወደ 900 ብር እንዲወርድ ሆኗል በማለት ነው፡፡ ከዚህ በኋላም ግብይቱ 900 ብር ዋጋን ይዞ ከአምስት በመቶ ወደላይ ወይም ወደታች ሳይወርድ የቡና ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡ ይህም አሁን እየወረደ ካለው ዓለም አቀፍ የቡና ዋጋ ጋር እንዲጣጣም ያደርገዋል ተብሏል፡፡ የአገር ውስጥ ግብይትን ከኒውዮርክ ገበያ ዋጋ ጋር ለማጣጣም ሲባል ባለፈው ሳምንት የተወሰደው ዕርምጃ፣ የአገር ውስጥ ዋጋን እንዲወርድ በማድረጉ እንደገና የዋጋ ገደቡን ወደ አምስት በመቶ እንዲወርድና ግብይቱ በዚሁ መንገድ እንዲቀጥል የተደረገ መሆኑንም ለማወ

የደቡብ ክልል የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ስልጣናቸውን ያለአግባብ በመገልገል የተጠረጠሩ ኃላፊዎች ጉዳያቸው በህግ እየታየ መሆኑን አስታወቀ

Image
በደቡብ ክልል ስልጣናቸውን ያለአግባብ በመገልገል በመንግስትና በህዝብ መሬትና ገንዘብ ላይ ወንጀል ፈፅመዋል ተብለው የተጠረጠሩ ኃላፊዎች ጉዳያቸው በህግ እየታየ መሆኑን የክልሉ የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ። ኮሚሽኑ እንዳለው በተጠርጣሪዎቹ እና በግብረአበሮቻቸው የተመዘበረ የመንግስት መሬትና ገንዘብን የማስመለስ ስራም ተጠናክሮ ቀጥሏል። የአዲሱ መሸሻን   ሪፖርት   ከቀጣዩ   ቪዲዮ   ይመልከቱ፡፡ http://www.ertagov.com/amerta/erta-news-archive/49-erta-tv-hot-news-addis-ababa-ethiopia/1859-2012-03-16-16-51-48.html