በሃዋሳ ከተማ ወደ ባለሃብትነት የተሸጋገሩ ኢንተርፕራይዞች ተመረቁ
ሃዋሳ, ታህሳስ 27 ቀን 2004 (ሃዋሳ) - በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራዝ ልማት የተሰማሩ ወጣቶች ሀገሪቱ ስራ አጥነትን በመቅረፍ ልማታዊ ባለሃብትን ለመፍጠር በምታደርገው ጥረት ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆናቸውን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ገለጸ፡፡ በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ተሰማርተው ወደ ልማታዊ ባለሃብትነት የተሸጋገሩ 16 ማህበራት መመረቃቸው ተገልጿል፡፡ የአስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ዮናስ ዮሴፍ ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ የከተማውን ነዋሪ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ገጽታ በመቀየር በርካታ ስራ በማከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡ ኢንተርፕራይዞቹ በከተማው ስራአጥነትና ድህነትን በመቀነስ ከግብርና መር ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ ለመሸጋገር በሚደረገው እንቅስቃሴ ከፍተኛ ሚና በመጫወት ላይ እንደሚገኙ ገልጸው አመራሩ ባለሙያውና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ለዘርፉ ጥንካሬ ትኩረት ሰጥተው መስራት እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡ ማህበራቱ ሙስናና ብልሹ አሰራር እንዲቀረፍ እንዲሁም ፍትሃዊ የሃብት አከፋፈልና አጠቃቀም በከተማው እንዲሰፍን እስካሁን ያበረከቱት አስተዋጽኦ አበረታች እንደነበር አስታውሰው ኪራይ ሰብሳቢነት በልማታዊ አስተሳሰብ እንዲለወጥ ጠንክረው ሊሰሩ አንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ በሃዋሳ ከተማ በስምንቱ ክፍለ ከተሞች በተለያየ የስራ ዘርፎች የተሰማሩ ከ100 የሚበልጡ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ልማቶች እንደሚገኙ የገለጹት አቶ ዮናስ በመንግስት፣ መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች የተቀናጀ ስራ ወደ ልማታዊ ባለሃብትነት የተሸጋገሩ 16 ማህበራት መመረቃቸውን ተናግረዋል፡፡ ማህበራቱ ባለፉት አምስት ዓመታት እያንዳንዳቸው ከአንድ ሚልዮን ብር በላይ ካፒታል በማስመዝገ