Posts

ፖለቲካ እና ኩሽ ኩሸቲክ

Image
ክፍል ፩   የኩሽና የኩሸቲክ ጉዳይ የፖለቲካ መነጋገሪያ ከሆነ ሰነበተ። እውነታውን መርምሮ ከማወቅ ይልቅ እዚህም እዚያም ለጊዜያዊ ፍጆታ በሚመስል የታሪክ መሠረት የሌለው ትርክት በዘፈቀደ ሲሰጥ ይስተዋላል። ይህን ጉዳይ ፈረንጆች ሳይቀሩ ታዝበውታል፣ “ዛሬ የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች የኩሸቲክ ሕዝብ ከሴሜቲክ ሕዝብ በላይ የአገሪቱ ባለመብት እንደሆኑ አጥብቀው ያሰምሩበታል” (ብሬየር 2007:460)። ለዚህ ሦስት መሠረታዊ ምክንያቶች ማቅረብ ይቻላል። አንደኛ፣ የዘመናችን የኩሸቲክ ቋንቋ ተናጋሪዎችን ከጥንታዊ የኩሽ ሕዝቦች ጋር አለቦታቸው ማዛመድ፤ የቋንቋና የሕዝብ ግንኙነትን በውል አለመለየትና ስለቋንቋዎቹ የቅርብ ጊዜ ጥናቶች የደረሱበትን በአግባቡ አለመረዳት ችግር ነው። ሁለተኛው፣ በቀደምት ጸሐፊዎች የቀረቡ ግልፅ ያልሆኑ፣ በተወሰነ ደረጃም የሚያምታቱና አሳማኝ ታሪካዊ መረጃ የሌላቸው፣ እንዲሁም ታሪክና እምነት አለመንገዳቸው እየተደባልቁ የቀረቡባቸው ትርክቶች መቅረባቸውም ጭምር ሊሆን ይችላል። ሦስተኛው፣ ስለኩሽ ስርወ መንግሥትና ስለኩሸቲክ ቋንቋዎች ቀደም ባሉት ጊዜያት ብዙም አለመታወቁ ነበር። ስለኩሸቲክ ቋንቋዎች የእርስ በርስ ግንኙነትና አጠቃላይ የዘር ምደባ በበቂ ሁኔታ አይታወቅም ነበር። አሁንም በአርኪ ሁኔታ ታውቋል ማለት አይቻልም። ለዚህ የተለያዩ ድምዳሜ ላይ የደረሱ የቅርብ ጊዜ ጥናቶችን ማየቱ ብቻ በቂ ነው። ስለጥንታዊው የኩሽ ስርወ መንግሥትም ያለው ሁኔታ ተመሳሳይ ነው። የግብፅ ታሪክ ጥላ የሆነበት ይመስላል። ስለዚህ ስርወ መንግሥት አሁንም ብዙ ታውቋል ማለት አይቻልም። ለዚህ በርካታ ምክንያቶች አሉ። አንደኛው፣ ጽሑፍ በኩሽ ስርወ መንግሥት የጀመረው ዘግይቶ መሆኑና እሱም ቢሆን ይዘቱ አለመታወቁ ነው። ሁለተኛው ዘረኝነት ነው። የኩሽ መንግሥት በማያጠያ...

ሲዳማ ቡና ሦስት ተጫዋቾችን ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል

Image
  አሠልጣኝ ዘርዓይ ሙሉን በማሰናበት አሠልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌን የሾሙት ሲዳማ ቡናዎች በሁለተኛው ዙር የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ተጠናክሮ ለመቅረብ ሥራዎችን እየሰሩ ይገኛሉ። በዚህም በዛሬው ዕለት ሦስት ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸው ለመቀላቀላቸው ተስማምተዋል። ቡድኑን ለመቀላቀል የተስማማው አንደኛው ተጫዋች መሐሪ መና ነው። ይህ የቀድሞ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ሲዳማ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ የግራ መስመር ተከላካይ ከአምሰት ዓመታት የፈረሰኞቹ ባት ቆይታ በኋላ በክረምቱ ክለቡን መልቀቁ የሚታወስ ሲሆን በሲዳማ የሚስተዋለውን ተፈጥሯዊ የግራ መስመር ተከላካይ እጥረት ለመሸፈን ተቀላቅሏል ። ሁለተኛው ሲዳማን የተቀላቀለው ተጫዋች ዮናስ ገረመው ነው። የቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ድሬዳዋ ከተማ፣ ጅማ አባ ጅፋር እና መቐለ 70 እንድርታ ተጫዋች የነበረው ዮናስ በትግራይ ክልል የሚጫወቱ ተጫዋቾች ለዚህ ዓመት ብቻ ወደ ሌሎች ክለቦች አምርተው እንዲጫወቱ በወጣው ልዩ የዝውውር ደንብ ተጠቅሞ ወደ ሀዲያ ሆሳዕና ለማምራት ተስማምቶ እንደነበር ይታወሳል። ነገርግን ተጫዋቹ እና ክለቡ የፈፀሙት ስምምነት ሳይፀድቅ በተከታታይ ሁለት ዓመታት የሊጉን ዋንጫ ያነሳው ተጫዋቹ የቀድሞ አሠልጣኙን የአማካይ መስመር ለማጠናከር ቡድኑን ተቀላቅሏል። የመጨረሻው ሲዳማን ለማገልገል የተስማማው ተጫዋች ሽመልስ ተገኝ ነው። ለበርካታ ዓመታት በመከላከያ ግልጋሎት የሰጠው የቀድሞ የሙገር ሲሚንቶ የመስመር ተከላካይ ተጫዋች የነበረው ሽመልስ የቡድኑን የቀኝ መስመር ለማጠናከር ቡድኑ ወዳለበት ባህር ዳር ተጉዟል። ተጫዋቾቹ ከነገ ጀምሮ በሚከፈተው የዝውውር መስኮት ውላቸውን በፌዴሬሽን ያስፀድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል። ምንጭ፤ ሶከር ኢትዮጵያ  

ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ የ69 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር ስምምነት ከሲዳማ ክልል ጋር ተፈራረመ

Image
  ሀዋሳ፤ የካቲት 19/2013 (ኢዜአ) ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ ለቀጣዮቹ አምስት ዓመታት አንድ ቢሊዮን 200 ሚሊዮን ብር  ለሚያካሄደው የተቀናጀ የልማት ፕሮግራም ከሲዳማና ደቡብ ክልሎች ጋር ስምምነት ተፈራረመ።  በሀዋሳ ከተማ ዛሬ በተካሄደው የፊርማ ሥነ -ሥርዓት ላይ ወርልድ ቪዥን  ኢትዮጵያን  በመወከል ከሁለቱም ክልሎች ጋር ስምምነቱን የተፈራረሙት የፊልድ ፕሮግራምና ስፖንሰርሺፕ አስተዳደር ዳይሬክተር ወይዘሮ እሌኒ መርጊያ ናቸው። በደቡብ ክልል ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ለሚካሄደው የልማት ፕሮግራም ስምምነት የተፈራረሙት የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አያሌው ዝና ሲሆን የሲዳማ ክልልን በመወከል ደግሞ የ69 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር ስምምነት የተፈራረሙት ደግሞ የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ አራርሶ ገረመው ናቸው። በስምምነቱ መሰረት በደቡብ ክልል ስድስት ዞኖችና 12 ወረዳዎች ተግባራዊ በሚደረገው ፕሮግራም 2 ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ ፤በሲዳማ ክልል ሁላ ወረዳ ...

Ethiopia//Top Things To Do In Hawassa (INCREDIBLE!!)

Image

በሲዳማ ክልል የ81 ህገ ወጥ የመንግስት ሰራተኞች ቅጥርና የደረጃ እድገት ተሰረዘ

በሲዳማ ክልል የ81 ህገ ወጥ የመንግስት ሰራተኞች ቅጥርና የደረጃ እድገት ተሰረዘ አዲስ አበባ ፣ የካቲት 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ክልል የ81 ህገ ወጥ የመንግስት ሰራተኞች ቅጥርና የ12 ህገ ወጥ የደረጃ እድገት እንዲሰረዝ መደረጉን የክልሉ የስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ገለጸ። ኮሚሽኑ የመንግስትና የህዝብ ንብረት የሆነ 7 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ከምዝበራ ማዳኑንም ገልጿል። የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አቶ ስጦታው ወንጫኖ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ለኮሚሽኑ ከቀረቡለት 56 አስቸኳይ የሙስና መከላከል ጥያዎች ውስጥ 54ቱን ተቀብሎ ምላሽ ሰጥቷል።  “በዚህም የ81 ሰዎች ህገ ወጥ የመንግስት ሰራተኛ ቅጥርና የ12 ሰዎች ህገ ወጥ የደረጃ እድገት እንዲሰረዝ ተደርጓል” ብለዋል። ከሁለት ቦታ ደመወዝ ሲበሉ የነበሩና ሌሎችም የመንግስት ሰራተኞች በህግ እንዲጠየቁ ሰነድ በማደራጀት ለሚመለከተው የህግ አካል መተላለፉን ተናግረዋል። በሀሰት ለተደራጁ ዘጠኝ የአረንጓዴ ፓርክ ልማትና ኮብል ስቶን ማህበራት ክፍያ ሊፈጸም የነበረውን ጨምሮ 2 ሚሊየን 367 ሺህ ብር በአስቸኳይ ሙስና መከላከል ስራ ማዳን መቻሉን ጠቁመዋል። ከተለያዩ ተቋማት ተመዝብሮ የነበረ 5 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በኦዲት ግኝት ተረጋግጦ ተመላሽ እንዲደረግ ኮሚሽኑ መስራቱን አስረድተዋል። ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ለምርጫ ስንዘጋጅ የትግል ታርካችን በጊዜ አመጣሹ እንዳይጠላሽ በቂ መረጃ ኖሮን ይሁን!

Image
   Information on the Sidama Liberation Movement (SLM), including history, goals, and methods; whether the group uses violence and has participated in armed conflict; treatment of members by the authorities  የመረጃው ምንጭ፤  refworld.org ነው።  1. Overview In correspondence with the Research Directorate, a lecturer in international development at the University of East London who has researched ethnic groups in Ethiopia, including the Sidama [1], characterized the Sidama Liberation Movement (SLM) as a "political organisation" that aims to "ensure Sidama peoples' national self-determination within the context of Ethiopia" (Lecturer 23 Oct. 2016). In correspondence with the Research Directorate, a research professor at Vrije Universiteit Amsterdam, who has researched history and culture in the horn of Africa, particularly Ethiopia, similarly stated that the SLM is "ethnically based and has a primarily Sidama-limited agenda" (Research Professor 21 Oct. 2016). T...

መንግሥት ከአሜሪካ ጋር በዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር የነበረው አለመግባባት እንዲቀጥል እንደማይፈልግ አስታወቀ

  የኢትዮጵያ መንግሥት በቀጣይ ከአሜሪካ ጋር የሚኖረው ግንኙነት በቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ወቅት በነበረው አለመግባባት እንዲቀጥል እንደማይፈልግ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ (አምባሳደር) ማክሰኞ የካቲት 16 ቀን 2013 ዓ.ም. በሚኒስቴሩ ሳምንታዊ መግለጫ ላይ እንዳስታወቁት፣ በቅርቡ ወደ ሥልጣን ከመጡት የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ጋር ጥሩ የሚባል ግንኙነት ለመፍጠር እየሠሩ ነው፡፡ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሥልጣን ዘመናቸው ከመጠናቀቁ ሁለት ወራት በፊት፣ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ በሰጡት አስተያየት ምክንያት በኢትዮጵያ በኩል ከፍተኛ ቁጣ አስነስቶባቸው እንደነበር ይታወሳል፡፡ ፕሬዚዳንቱ ከሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክና ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስቴር ቤንያም ናታኒያሁ ጋር በስልክ በተነጋገሩበት ወቅት ግድቡን አስመልክተው፣ ሁኔታው አደገኛ እንደሆነና ‹‹ግብፅ ግድቡን  ልታፈነዳው ትችላለች›› በማለት የሰነዘሩት አስተያየት፣ በአገር ቤትና በውጭ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ወዳጆችን አስቆጥቶ ነበር፡፡ ከዚህ ባለፈም አሜሪካ ለኢትዮጵያ በዕርዳታ መልክ ልታቀርብ አቅዳ የነበረውን 272 ሚሊዮን ዶላር ከህዳሴ ግድብ አሞላልና አጠቃቀም ጋር በተገናኘ እንዳይለቀቅ ተደርጎ ነበር፡፡ በቅርቡ ወደ ሥልጣን የመጡት የዴሞክራት ፓርቲ ተመራጩ ጆ ባይደን አስተዳደር ከጥቂት ቀናት በፊት ባወጣው መግለጫ ለኢትዮጵያ እንዲሰጥ ታስቦ የነበረውን ገንዘብ ከህዳሴ ግድብ ጋር እንዳይያያዝ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ክልል በሚያደርገው የሕግ ማስከበር ዘመቻ የኤርትራ ወታደሮች ከክልሉ ለቀው እንዲወጡና በክልሉ የተፈጠረው የሰብዓዊ መብት ጥሰት በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ብሏል፡፡...