የደኢህዴን/ኢህአዴግ አስተዳደሩና ጎሴኝነቱ በሲዳማ ህዝብ ላይ ያደረሰው ኪሳራ
ከማህበራዊ መረብ ላይ የተገኘ ጽሁፍ በሃዋሳ ዱሜ ኢትዮጵያ ሀገራችን ወዳና ፈቅዳ የፌዴራል መንግሥት ህገ-መንግሥት አካል አድርጋ የተቀበለችውና ዓለም ዓቀፍ ሰብአዊ መብቶች ሰነድ አንቀጽ 1 ላይ እንደተደነገገው ዘረኝነትም ሆነ ጎሴኝነት ከሰብአዊነት መርህና ከሰብአዊ መብቶች የሚቃረን መሆኑንና በዚህ መሠረት የመጀመሪያ አንቀጽ የሚያውጀው የሰው ልጆች እኩልነትን ነው፡፡ ሰዎች ሁሉ እኩል ክብርና መብቶች ይዘውና ነፃ ሆነው ተፈጥረዋል፡፡ ሰው የሚባለው ፍጡር የማሰብና የማመዛዘን ችሎታ በተፈጥሮ ስለታደለ እርስ በርሳቸው በወንድማማችነት ሊተያዩ ይገባል ይላል፡፡ በአንቀጽ ሁለት መሠረት ደግሞ ጉዳዩን ባይበልጥ በማብራራት በዘር፣በቀለም፣በቋንቋ፣ በሃይማኖት፣በፖለቲካ ወይም በሌላ አስተያየት፣በህብረተሰብ ምንጭ፣በሀብት፣በትውልድ ወይም በሌላ አቋም ምክንያት ምንም ዓይነት ልዩነት ሳይደርግበት እያንዳንዱ ሰው በተጠቀሱ መብቶችና ነፃነቶች የመጠቀም መብት አለው ይላል፡፡ ነገር ግን በሲዳማ ውስጥ በተግባር የሚታየው የዚሁ ተቃራን ነው፡፡ የተወሰኑ ማስረጃዎችን መጥቀስ ካስፈለገ፡- ደኢህዴን/ኢህአዴግ የመንግሥት መዋቅርን ማስተዳደር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የሲዳማ ህዝብ በጎሳና በቤተሰብ እንዲከፋፈልና አንድነቱ እንድናጋ ፖለቲካዊ ደባ ተሰርቶበታል፡፡ ህዝባችን ግን አስቀድሞ በመንቃቱ በጎሴኝነት ስሜት የተዘራው ቫይረስ በመንግሥትና በፖለቲካው መዋቅር ተወስኖ ቀረ እንጂ ሊያስከትል የሚችለው አደጋና ኪሳራ ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችል መገመት ይቻላል፡፡ አሁንም ቢሆን በጎሴኝነትና በዘረኝነት የተዘራብን በሽታ በየወረዳው ህዝብን ሰለባ እያደረገና ገና ብዙ ዋጋ የሚያስከፊል የተቀበረብን ፈንጂ ያለ መሆኑን አሁን በተለያዩ ጎሳዎች ላይ እየተሠራ ያለው ከፋፋይ ድራማ መገንዘብ ይቻላል፡፡ በዚሁ መ