በሲዳማ ዞን ቦርቻ ወረዳ ከ16 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በበልግ ይለማል
New አዋሳ, የካቲት 23 ቀን 2004 (ሃዋሳ) - በሲዳማ ዞን የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆነችው ቦርቻ ወረዳ በተያዘው የበልግ ወቅት ከ16 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት እየተሰራ ነው፡፡ ከልማቱም ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ይሰበሰባል ተብሎ እንደሚጠበቅ የወረዳው አስተዳደር አስታውቋል፡፡ አርሶ አደሮቹ በበኩላቸው የተለያዩ ግብዓቶችን በመጠቀም ምርታማነታቸውን ለማሻሻል በመስራት ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አማኑኤል አዴላ ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በወረዳው ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ሁሉም አርሶ አደር ከዘርፉ ተጠቃሚ እንዲሆን እየተሰራ ነው፡፡ በወረዳው ከሚሰበሰበው ምርት 70 በመቶ ያህሉ በበልግ ወቅት ከሚለማ መሬት የሚገኝ በመሆኑ ለበልግ እርሻ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ የእርሻ ሥራ በመከናወን ላይ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ የወረዳው ግብርና ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ታዲዮስ ነዲ በበኩላቸው ዘንድሮ 16 ሺህ 614 ሄክታር መሬት በቦሎቄ፣ በበቆሎ እና በተለያዩ ስራስሮችና ዓመታዊ በሆኑ የተክል ዓይነቶች እንደሚሸፈን ገልፀዋል፡፡ በዘንድሮው በልግ በልዩ ልዩ ዘር ከሚሸፈነው መሬት ከ 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ይሰበሰባል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል፡፡ የተያዘውን ዕቅድ ለመሳካት ከወረዳ እስከ ቀበሌ ባለው መዋቅር ከሚገኙ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ የግብርና ባለሙያዎችና ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት መደረጉን ገልፀዋል፡፡ ጽህፈት ቤቱ ከደቡብ ክልል ምርጥ ዘር አቅርቦት ድርጅት ጋር በመቀናጀት ከ1ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ 850 ኩንታል ምርጥ ዘር ተገዝቶ ለአርሶ አደሩ መቅረቡንም ጠቁመዋል፡፡ በተጨማሪም 37 ሺህ 700 ኩንታል በ