ጥቂት ስለ ዋራ _የኣካባቢው ህዝብ ብዛት እየጨመረ ከመምጣቱ ጋር በተያያዘ ወደ እርሻ መሬትነት እየተቀየረ ነው
Wara Sidama በሲዳማ ትልቁ ሜዳ የሆነው ዋራ የኣካባቢው ህዝብ ብዛት እየጨመረ ከመምጣቱ ጋር በተያያዘ ወደ እርሻ መሬትነት እየተቀየረ በመምጣቱ ስፋቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያነሰ መጥቷል። የዋራ ሜዳ በሲዳማ ህዝብ ዘንድ ታሪካዊ ፋይዳ ያለው ቦታ ሲሆን፤ በታሪክም የዛሬ 400 ኣመታት በፊት ሲዳማ እና ሆፋ የተባለ ጎሳ፤ ዛሬ የሲዳማ ህዝብ የሰፈረበትን መሬት በባለቤትነት ለመያዝ ታሪካዊ ጦርነት ያደረገበት ቦታ ነው። የታሪክ ድርሳናት እንደሚያወሱት፤ የዋራ ሜዳ ለሲዳማ ከብት ኣርብዎች ሁነኛ የግጦሽ ማዕከል ነው። በኣሁኑ ጊዜ የኣከባቢው ህዝብ ባለበት የመሬት ጥበት የተነሳ የከብት እርባታን በመተው የእርሻ ስራን በማስፋፋት ላይ በመሆኑ የዋራ ሜዳ ስፋት እንድቀንስ ሆኗል። የዋራ ሜዳ ከታሪካዊ ፋይዳው በተጨማሪ የሲዳማ ክልል የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ለምታዘጋጀው ዓለም ኣቀፋዊ ክሩሴይድ ከግማሽ ሚሊዮን ህዝብ በላይ ከመላው ኣለም የምሰባሰብበት ቦታ ነው።