የሀዋሳ ከነማ ስፖርት ክለብ ታሪክ
አመሠራረት የ የሁለት ጊዜ የኢትዮጲያ ፕርሚየር ሊግ አሸናፊ ሀዋሳ ከነማ ስፖርት ክለብ ከኢትዮጲያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ 273 ኪ . ሜ ዕርቀት እና በ 162.804 ሄክታር ቋዳ ስፋት ላይ በምትገኘው ሀዋሳ ከተማ ይገኛል፡፡ የሀዋሳ ከተማ በ 1953 ዓ . ም የተመሰረተች ሲሆን ከ 1985 ዓ . ም ጀምሮ ደግሞ የደቡብ ክልል ርዕሰ ከተማ በመሆን በማገልገል ላይ ትገኛለች፡፡ የደቡብ ክልል አምብርት በሆነችው ሀዋሳ ከተማ የሚገኘው የሀዋሳ ከነማ ስፖርት ክለብ የተመሰረተው በ 1976 ዓ . ም ነው፡፡ የሀዋሳ ከተማ ባለፈው መንግስት ዘመን በሁለት ከፍተኞች የተከፈለች ከተማ ነበረች፡፡ በሁለቱ ከፍተኞች ስም የተቋቋሙ ሁለት ቡድኖችም ነበሩ፡፡ እነዚህ ቡድኖች ከ 1968-1975 ዓ . ም ከቆዩ በሆላ በ 1976 ዓ . ም ሁለቱ ቡድኖች ተዋህደው ሀዋሳ ከነማ ሊወለድ እንደቻለ ከክለቡ ፅ / ቤት ካገኘነው መረጃ ለማወቅ ተችሏል፡፡ የሀዋሳ ከነማ ክለብ በሀዋሳ ከተማ የከተማውን ነዋሪ የሚወክል አንድ ቡድን መኖር አለበት በሚል በመዘጋጃ ቤቱ ሃላፊዎች ተነሳሽነትና በነዋሪው ጠያቂነት ሊቋቋም እንደቻለ ታውቋል፡፡ ክለቡ በተጠቀሰው ጊዜ ሲመሰረት ሀዋሳ ሐይቅ በሆላም ቀይ ኮከብ የሚባል ስያሜ እንደነበረው የክለቡ ታሪክ ማህደር ያስረዳል፡፡ የሀዋሳ ከነማ ስፖርት ክለብን ከ 1976 ዓ . ም ጀምሮ በባለቤትነት እያስተዳደረ የሚገኘው የሀዋሳ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ነው፡፡ ይሁንና ስፖርት ክለቡ በሂደት ራሱን ችሎ መውጣት አለበት በሚል ህሳቤ ከ 1996 ዓ . ም ጀምሮ አሁን ያለውን አደረጃጀት እንዲይዝ ተደርጓል፡፡ ሙሉ ታሪኩን እዚህ ተጭነው ያንቡ