ሲዳማ ብርቅዬ ልጆቿን ለልማትና ለመልካም አስተዳደር ግንባታ የምትጠራበት ጊዜ አሁን ነው!!


የሲዳማ ክልል ፕሬዚዳንት ዶክተር መሳይ፣ በክልሉ የሚታየውን የኢኮኖሚ ስብራት ለመጠገንና የልማት ሂደቱን ለማፋጠን ከሲዳማ ዲያስፖራና ምሁራን ጋር በትብብር ለመሥራት መዘጋጀታቸው አበረታች እርምጃ ነው።

እንግዲህ ይህንን መልካም ፍላጎት በተግባር የሚገለጽ ለማድረግ ጊዜ ሳያጠፉ ሁሉንም የሲዳማ ብርቅዬ ልጆች የሚያሳትፍ ግልጽና ዘላቂ የትብብር መድረክ መፍጠር ያስፈልጋል። ሲዳማን በኢኮኖሚ ዕድገት፣ በመልካም አስተዳደርና በማኅበራዊ ልማት በአገሪቱ አርአያ የሆነ ክልል ለማድረግ የልጆቿ ዕውቀት፣ ልምድ፣ ሀብትና የፈጠራ አቅም ወሳኝ ናቸው።

ስለዚህ የክልሉ መንግሥት በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካ፣ በትምህርት፣ በቴክኖሎጂና በማኅበራዊ ዘርፎች የተካኑ የሲዳማ ምሁራንንና ባለሙያዎችን በማሰባሰብ ዕውቀታቸውንና ልምዳቸውን ለክልሉ ዕድገት እንዲያውሉ ጥሪ ማቅረብ አለበት። ይህ ጥሪ በቃላት ብቻ ሳይወሰን፣ በግልጽ የተግባር ዕቅድ፣ በተጨባጭ የትብብር መዋቅርና በተጠያቂነት ሊደገፍ ይገባል።

ሲዳማ በብርቅዬ ልጆቿ ዕውቀትና ትብብር የምትገነባበት፣ በልማትና በመልካም አስተዳደር ለሌሎች ክልሎች አርአያ የምትሆንበት ጊዜ አሁን ነው!!

Comments

Popular posts from this blog

ስለከሸፈው “መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ” ጥራዝ አንዳንድ ነጥቦች

SIDAMA Micro-Finance Institution

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት