የፊቼ ጫምባላላ በዓል በሀዋሳ ሁሉም ክፍለ ከተሞች በተለያዩ ካርኒቫሎች እየተከበረ ይገኛል


የፊቼ ጫምባላላ በዓል በሀዋሳ ሁሉም ክፍለ ከተሞች በተለያዩ ካርኒቫሎች እየተከበረ ይገኛል
የፊቼ ጫምባላላን በዓል ለማክበር ሲዳማ መሆን አይጠበቅም በሚል አቋም የተመራው የሀዋሳ ከተማ ነዋሪ በየክፍለ ከተሞቹ በሚገኙ የተለያዩ ቀበሊያት ድንኳን በመጣል ጭምር እየተከበረ ይገኛል፡፡
ይህ ባህላዊ የሲዳማ ምግቦች፣. አልባሳትን እና መገልገያ ቁሶችን በማሳየት እየተከበረ የሚገኘው 2012 የሲዳማ ዘመን መለወጫ በዓል ከብሔሩ ውጭ ያሉ ነዋሪዎችም ጭምር ተሳትፎ እያደረጉ የሚገኝም ነው፡፡
በአሉ የእርቅ፣ የሰላም፣ የፍቅር እና የአብሮነት ስለመሆኑ አመላካች የሆኑ መሪ ቃሎችን በማንገብ እየተከበረ የሚገኘው የሲዳማ ፊቼ ጫምባላላ ከማንኛውም የጽጥታ ስጋትም ይሁን ከጠብ አጫሪነት ተግባር የጸዳ ሆኖ እንዲከበርም ነዋሪዎቹ በቆታቸው ዘብ ስለመቆማቸውም ማሳየት ያስቻለ ነው፡፡
ከዚህ ጎን ለጎን ማንኛውም በበበዓሉ አከባባር ወቅት እና ሂደት የሚስተዋሉ እኩይ ተግባራትንም ለመቆጣጠር ይቻል ዘንድ የከተማዋ አስተዳደር ተንቀሳቃሽ ጊዚያዊ ችሎትን በየቀበሊያቱ በመመደብ ጭምር ጥረት እያደረገ እንደሚገኝም በተመሳሳይ ማወቅ ተችሏል፡፡
ይህ በከተማዋ የሚገኙ ክፍለ ከተሞች በየቀበሊያቱ የሚያደርጉት የበዓል አከባባር እንግዶችን ጭምር አቀባበል በማድረግ እየተከናወነ የሚገኝ ስለመሆኑ የዝግጅት ክፍላችን ተዘዋውሮ ያጠናቀረው ዘገባ ያመላክታል፡፡

Comments