Sidama Traditional Medicinal Plants Get link Facebook X Pinterest Email Other Apps August 29, 2014 McAlvay_Sidama_Plant_Based_Medicine.pdf ምንጭ፦ http://www.surgery.wisc.edu/system/assets/1951/McAlvay_Sidama_Plant_Based_Medicine.pdf?1389376111 Get link Facebook X Pinterest Email Other Apps Comments
የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት September 01, 2019 የለበሰው ያደፈ ቁምጣና ሹራብ ከቅዝቃዜው አላዳነውም፡፡ ካፊያው ልብሱን አርሶታል፡፡ ሽው እያለ ከሐይቁ የሚነሳው ነፋስ የሚፈጥረው ቅዝቃዜ ያንቀጠቅጠዋል፡፡ የተጫማው ያረጀ ሲሊፐር እግሩን ከምንም አላዳነውም፡፡ በባዶ እግሩ የሚራመድ ያህል ጨቅይቷል፡፡ ተደባዳቢ ይመስል ፊቱ የተሞነጫጨረ ነው፡፡ ገና 12 ዓመቱ ቢሆንም፣ ቁመናው እንደ ትልቅ ሰው ግዙፍ ነው፡፡ የሚለብሰውን እንደ ልቡ ባያገኝም፣ የሚያስፈልገውን ነገር ለማሟላት ቤሳቢስቲን የሌላቸው ወላጆቹን አያስቸግርም፡፡ ከቤተሰቦቹ ጋር ከሚኖሩበት ታቦር ተራራ ጀርባ ወዳለው ሐዋሳ ሐይቅ ከወረደ እንኳንስ የራሱን የቤተሰቦቹንም የዕለት ጉርስ የሚሸፍንበት ገንዘብ አያጣም፡፡ የአስጎብኚነት ዕውቀት፣ ከሐይቁም ውስጥ ዓሳ የሚያጠምድበት መረብም ሆነ ፈቃድ የለውም፡፡ ሙሉቀን (ስሙ ተቀይሯል) እና ጓደኞቹ ሐይቁን ለመጎብኘት የሚሄዱ ጎብኚዎች በካሜራቸው ጥሩ ፎቶ እንዲያስቀሩ ድባቡን የማሳመር ሥራ ይሠራሉ፡፡ ካሜራውን ይዞ ቁጭ ብድግ እያለ ጥሩ ፎቶ ለማንሳት ጥረት የሚያደርግ ሲያዩ፣ ቆርጠው የያዙትን የዓሳ ሥጋ ይዘው ጠጋ ጠጋ ይላሉ፡፡ ቁርጥራጩን የዓሳ ሥጋ ምግብ ለሚቀሙት አባኮዳዎች ሻሞ ይላሉ፡፡ የተወረወረላቸውን ቀድመው ለመቅለብ አባኮዳዎቹ ክንፋቸውን እየመቱ ወደ ላይ ብድግ ይላሉ፡፡ የናሽናል ጆግሪፊ የፎቶግራፍ ባለሙያዎች ያነሱት ዓይነት ፎቶዎች ሳያስቡት ያነሳሉ፡፡ በሁኔታው ተደስተው ደጋግመው ድንቅ ፎቶዎችን ለመውሰድ ሲዘጋጁ እነ ሙሉቀንም አጀንዳቸውን ይፋ ማድረግ ይጀምራሉ፡፡ አቶ ዳዊት አብርሃም ‹‹አንዱን ዓሳ በአሥር ብር ገዝቼ ነው እንዲህ የማዘጋጀው፤›› በማለት በቅድሚያ መረጃ ይሰጣሉ፡፡ ለቀጣዩ ዜና በዚህ መልኩ እንዲዘጋጁ ካደረጉ በኋላ፣ ሌሎች ሰዎች መቶም ሁለት መቶም ብር እንደሚሰጧቸው... Read more
የሲዳማ ክልል ባለስልጣናትን ጨምሮ የተገለገሉት የሰሞኑ የቻርተር አውሮፕላን በረራዎች! February 21, 2022 ከሰሞኑ አንዳንድ የስራ ሀላፊዎች የቻርተር አውሮፕላን በረራዎችን ደጋግመው ሲጠቀሙ ተመልክተናል። ታድያ እነዚህ በአንድ ጉዞ ብቻ የመቶ ሺህ ብሮችን ወጪ የሚጠይቁ በረራዎች የተካሄዱት የኢትዮጵያ አየር መንገድ መደበኛ በረራ ጠፍቶ ወይስ በምን አግባብ ይሆን? በግሌ ለማየት እንደሞከርኩት በነዚህ ቀናት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎች ነበሩ። ለምሳሌ ባለፈው አርብ የሲዳማ ክልል ፕሬዝደንት የሚድሮክን King Air 360 ቻርተር አውሮፕላን በተጠቀሙበት እለት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ET228 ከአዲስ አበባ ወደ ጅግጅጋ በረራ ነበረው፣ ሌሎቹም እንዲሁ። እርግጥ ነው እንደ ቡህታን ንጉስ ያሉ ቢሊየነሮች አይደለም የቻርተር በረራ የራሳቸው ግዙፍ አውሮፕላን አላቸው። ነገር ግን ተጠያቂነት ባለባቸው ሀገራት ከህዝብ በሚሰበሰብ ገንዘብ እንዲህ አይነት አሰራር አይታሰብም። በአንድ ወቅት የአሜሪካው ሴናተር ቴድ ክሩዝ በመንገደኛ አውሮፕላን ከህዝብ ጋር ተሳፍረው ሳለ ያጋጠማቸውን ሰምታችሁ/አንብባችሁ ይሆናል። ጦርነት፣ ድርቅ እንዲሁም ሌሎች ውስጣዊ እና ውጫዊ ምክንያቶች ከፍተኛ ጫና ሀገር ላይ እያደረሱ ባሉበት ወቅት እንዲህ አይነት ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቁ ጉዞዎች ተገቢ ናቸው ብላችሁ ታስባላችሁ? ኤሊያስ መሰረት Read more
ኣዲሱ የሲዳማ ካርታ ሃዋሳ እና ከቅርብ ኣመታት ወዲህ በሃዋሳ ከተማ ስር የተካተቱትን ኣዳዲስ ክፍለ ከተሞችን ኣያካትትም July 12, 2012 ኣዲሱ የሲዳማ ካርታ ያልተካተቱት የሲዳማ ኣካባቢዎች መካከል ሃዋሳ፤ ከቅርብ ኣመታት ወዲህ በሃዋሳ ከተማ ስር የተካተተውን ኣዲሱን ክፍለ ከተማ ኣቤላ ቱላን ጨምሮ ከከተማ ዙሪያ ያሉትን ዳቶ ኦዳሄ እና ሎቄን የመሳሰሉ ቀበሌዎችን ናቸው። የተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑድርጅቶች ለተለያዩ ጉዳዮች ሲዳማን በተመለከተ እየተጠቀሙ ያሉት ኣዲሱ ካርታ ኣዳዲስ ወረዳዎችን ጨምሮ ከላይ የተጠቀሱትን የሲዳማ ዞን ኣካባቢዎችን በስተቀር ሁሉንም ወረዳዎችን ያካተተ ሲሆን የሃዋሳን ከተማና የኣካባቢውን ቀበሌዎች ኣለማከተቱ በቅርቡ በዞኑ ውስጥ ተነስቶ ለነበረው ህዝባዊ ንቅናቄ መንስኤ ከሆነው የማወያያ ጽሁፍ ጋር መያያዝ ኣለመያያዙ ኣልታወቀም። Read more
Comments
Post a Comment