Posts

በሁለት ክፍለ ከተሞቿ ሲትጋይ ያደረችው ሐዋሳ እና ጥያቄ ውስጥ የገባው የከተማ ኣስተዳደር የእሳት ኣደጋን ለመቆጣጠር ያለው ዝግጅትና ብቃት

Image
ፎቶ ከ ተፈሪ ታደሰ በከተማ ታሪክ ከፍተኛ በተባለው በዚህ የእሳት ኣደጋ በሰው ህይወት እና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል፤ ኣላሙራ ኣዲሱ ገበያ ሙሉ በሙሉ ወድሟል፤ በተመሳሳይ ምሽት በቱላ ክፍለ ከተማም ሁለት ቤቶች በቃጠሎው ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ታውቋል፤ የከተማዋ ኣስተዳደር መሰል የእሳት ኣደጋዎችን ለመቆጣጠር ያለው ዝግጅትና ብቃት ጥያቄ ውስጥ ገብቷል፤ በሲዳማዋ መዲና ሐዋሳ ከተማ በሁለት ክፍለ ከተሞቿ በተነሱ የእሳት ኣደጋዎች በሰው፤ በእንስሳት እና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል። የእሳት ኣደጋ የደረሰው በኣላሙራ ኣዲሱ ገበያ እና በቱላ ክፍለ ከተማ ነው። የወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ የኣይን እማኞችን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ በታቦር ክፍለ ከተማ ፉራ ቀበሌ በሚገኘው በተለምዶ ኣዲሱ ገበያ ተብሎ በምጠራው ስፍራ ላይ ባለፈው ቅዳሜ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ላይ የተነሳው የእሳት አደጋ ገበያውን ሙሉ በሙሉ አውድሟል። ባልታወቀ ምክንያት በተከሰተውና ከሰዓታት በቆየው የእሳት ቃጠሎ አንድ የአንድ አመት ከስድስት ወር ህጻን ልጅ ህይወቱ ሲያልፍ በአንድ አዛውንት ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት መድረሱን ገልጸዋል የመንግስት ዜና ኣውታሮች የዘገቡ ቢሆንም ከተለያዩ ምንጭ የተገኙ መረጃዎች የጉዳት መጠን ከፍተኛ መሆኑን ያመለክታሉ፡፡ የእሳት ቃጠሎውን ለማጥፋት የሀዋሳ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የእሳት አደጋ መከላከያ ብርጌድ፣ የሀዋሳ ጨርቃ ጨርቅና የሻሸመኔ ከተማ እሳት አደጋ መከላከያና የክልሉ ልዩ ሀይል ፖሊስ እሳት አደጋ መከላከያ እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች የተሳተፉ ሲሆን፤ የከተማው ኣስተዳደር መሰል ኣደጋዎችን ለመቆጣጠ ያለው ዝግጁነት እና ብቃት ኣነስተኛ መሆኑ ለጉዳቱ መባባስ ምክንያት መሆኑ ታውቋል።

“ቡና ኃይለኛ የቆዳ ካንሰር ሊከላከል ይችላል”

Image
ብሔራዊ የካንሰር ኢንስቲትዩት ይፋ ያደረገው ጥናት እንደሚለው ከሆነ ቡና ሜላኖማን የመከላከል ኃይል አለው፡፡ 447 ሺህ  357  ሰዎችን ያሳተፈውና በአማካይ ለ10 ዓመታት የዘለቀው ይህ ጥናት ቡና በብዛት የሚጠጡ ሰዎች ለበሽታው ያላቸው ተጋላጭነት አነስተኛ መሆኑን አመላክቷል። በመሆኑም በቀን አራት ስኒ ቡና ወይም ከዚያ በላይ የሚጠጡ ሰዎች ለሜላኖማ የመጋለጥ ዕድላቸው ቡና ከማይጠጡ ሰዎች በ20 በመቶ ያነሰ መሆኑን ጠቁሟል። ይሁንና የጥናቱ ውጤት ያንኑ ናሙናው የተወሰደበትን ማህበረሰብ እንጂ ሌሎችን እንደማይወክልና በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ጥናት እንደሚያስፈልግ ተመራማሪዎቹ አልሸሸጉም። ምንጭ፡-  ዘ ታይምስ ኦፍ ኢንዲያ

ድንገት የእሳት ቃጠሎ ለደረሰበት ሰው መድረግ ያለበት የመጀመሪያ ደረጃ እርዳታ

Image
•    የእሳት ቃጠሎ አደጋ የደረሰበትን ሰው በአፋጣኝ ከቃጠሎው ቦታ ማራቅ •    በጣም ያለቀዘቀዘ ወይንም በረዶ ያልሆነ ውሃን በተቃጠለው አካል ላይ ማደረግ ምክንያቱም በረዶ ቃጠሎ የደረሰበትን ቆዳችንን ስለሚጎዳ ነው። •    ማንኛውንም ልብስ ወይም ጌጣጌጥ አደጋው ከደረሰበት ሰው ላይ ማውለቅ፥ ነገር ግን ከቆዳ ጋር ተጣብቆ ያለ ማንኛውንም ነገር ለማንሳት መሞከር ለመጀመሪያ ደረጃ እርዳታ ተገቢ አይደለም፡፡ •    አደጋው የደረሰበት ሰው በብርድ እንዳይጠቃ መከላከል •    የህመም ማስታገሻ መድሀኒቶች በአቅራቢያ ካገኙ መስጠት •    በአፋጣኝ ወደ ህክምና ቦታ መውሰድ ናቸው።

በሐዋሳ ከተማ ኣዲሱ ገበያ በተከሰተው የእሳት ኣደጋ በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ

Image
Post by Abu Sa'adayin Fathudiin . በሐዋሳ ከተማ በተለምዶ  ኣዲሱ ገበያ ተብሎም በምታወቀው ኣከባቢ በትናንትናው እለት የተነሳው ድንገተኛ እሳት በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱ ታውቋል። ከተለያዩ ማህበራዊ መረቦች ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው፤  አዲሱ ገበያ እና በኣከባቢው የነበሩት የንግድና መኖሪያ ቤቶች በእሳት ቃጠሎ ወድመዋል። እስከ ኣሁን ድረስ የእሳት ኣደጋው መንስዔ ምንነት ካለመታወቁ በላይ በንብረት ላይ የደረሰው ጉዳት በገንዘብ ስተመን ምን ያህል ልሆን እንደምችልም የተነገረ  ነገር የለም።

ሁለቱ የሲዳማ የሴቶች እግር ኳስ ክለቦች 7 ተጫዋቶችን ለሉሲ ኣስመረጡ

Image
በአሰልጣኝ በኃይሏ ዘለቀ  የሚመራው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን መጋቢት 23 ቀን 2007 ለመላው አፍሪካ ጨዋታዎች ማጣርያ ከካሜሩን አቻው ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ 40 ተጫዋቾችን የመረጠ ሲሆን የሲዳማ ክለቦች የሆኑት ሲዳማ ቡና እና ሐዋሳ ከነማ በድምሩ ሰባት ተጨዋቾችን ኣስመርጠዋል፡፡ በተለይ ሲዳማ ቡና የሴቶች እግር ኳስ ቡድን ሊያ ሽብሩን በግብ ጠባቂነት፤ ፋስካ በቀለን በተከላካይነት፤ የካቲት መንግስቱን በኣማካይነት፤ መሳይ ተመስገን እና ወርቅነሽ መልሜሎን በኣጥቂነት በድምሩ ኣምስት ተጫዋቶችን ለብሔራዊ ቡድኑ በማስመረጥ ስድስት ተጫዋቾችን ካስመረጠው ደደቢት ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ሐዋሳ ከነማ በበኩሉ፧ ኣዲስ በፍቃዱን እና ምህረት መለሰን በኣማካይ እና በተከላካይ ቦታ ኣስመርጧል።   ሉሲዎቹ ዝግጅታቸውን ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ የሚጀምሩ ሲሆን የኢትዮጰያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግም ለአንድ ወር ያህል ይቋረጣል ተብሏል፡፡ ለሉሲዎቹ የተመረጡት 40 ተጫዋቾች የሚከተሉት ናቸው፡- ተ.ቁ ስም ክለብ ግብ ጠባቂዎች 1 ዳግማዊት መኮንን የኢት. ንግድ ባንክ 2 ማርታ በቀለ ዳሽን ቢራ 3 ትእግስት አበራ ወላይታ ድቻ 4 ታሪኳ በርገና ድሬዳዋ ከነማ 5 ሊያ ሽብሩ ሲዳማ ቡና ተከላካዮች 6 ሳምራዊት ኃይሉ መከላከያ 7 መስከረም ኮንካ ደደቢት 8 ጥሩአንቺ መንገሻ የኢት.ንግድ ባንክ 9 ፅየን እስጢፋኖስ ቅዱስ ጊዮርጊስ 10 ፋሲካ በቀለ ሲዳማ ቡና 11 አረጋሽ ፀጋ አርባምንጭ ከነማ 12 እፀገነት ብዙነህ የኢት. ንግድ ባንክ 13 ውባለም ፀጋዬ ደደቢት 14 ፋጡማ አሊ ደደቢት 154 መልካም ተፈራ ቅዱስ ጊዮርጊስ 16 ምህረት መለሰ ሀዋሳ ከነማ 17 አሳቤ ምኤሶ አዳማ ከነማ 18 ገነት ኃይሌ ድሬዳዋ ከነማ አማካዮች 19