Posts

Ethiopia’s stifled press

WHILE ENJOYING its status as an international development darling, Ethiopia has been chipping away at its citizens’ freedom of expression. The country now holds the shameful distinction of having the second-most journalists in exile in the world, after Iran. That combination of Western subsidies and political persecution should not be sustainable. According to a  new report by Human Rights Watch , at least 60 journalists have fled the country since 2010, including 30 last year, and at least 19 have been imprisoned. Twenty-two faced criminal charges in 2014. The government closed five newspapers and a magazine within the past year, leaving Ethiopia with no independent private media outlets. With the country headed toward elections in May, the pressure on the media has undermined the prospect of a free and fair vote. Ethiopia has long been known for its censorship and repression of the media, but the situation has deteriorated in recent years. According to the Committee to Protect

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምርጫ ቦርድ ላይ የሚቀርቡትን የገለልተኝነት ትችቶች አጣጣሉ

Image
‹‹ምርጫ ቦርድ እየተሰደበ የሚቀጥል አይመስለኝም››   ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ‹‹አሁንም እደግመዋለሁ ቦርዱ ገለልተኛ አይደለም››   አቶ ግርማ ሰይፉ የ2007 ዓ.ም. ግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸማቸውን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባለፈው ሐሙስ ሪፖርት ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ፣ በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ገለልተኝነት ላይ የሚሰነዘሩ ትችቶችን ጠንከር ብለው በማጣጣል ተከላከሉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ 18 ገጽ ባለው የሥራ አፈጻጸም ሪፖርታቸው ውስጥ ዘንድሮ አገሪቱ ከምታስተናግዳቸው ትልልቅ ኩነቶችና የቀጣይ አምስት ዓመት የአገሪቱ ጉዞን ከሚወስኑ ጉዳዮች ዋነኛው፣ በግንቦት ወር የሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በግንቦት ወር የሚካሄደው አምስተኛው ጠቅላላ ምርጫ ዴሞክራሲያዊ፣ ሰላማዊና በሕዝቦች ዘንድ ዓመኔታ ያለው ሆኖ እንዲጠናቀቅ መንግሥት በሁሉም መስክ አስፈላጊውን ዝግጅት እንዳደረገና በቀጣይ ሒደቱን በንቃት በመከታተል መንግሥታዊ ግዴታውን እንደሚወጣ አስታውቀዋል፡፡ ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሐሳብና አገላለጽ ግን ሊበተን የዚህን ዓመት መገባደድ በሚጠብቀው ፓርላማ ውስጥ የተቃዋሚው የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ብቸኛ ተወካይ ለሆኑት አቶ ግርማ ሰይፉ አልተዋጠላቸውም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ሪፖርት አንድ ሳምንት ቀደም ብሎ ምርጫ ቦርድ በአንድነት ፓርቲ ውስጥ በተፈጠረ አለመግባባት ላይ የሰጠው ውሳኔ፣ አቶ ግርማ የሚመሩትን የፓርቲው ወገን ዕውቅና የነፈገ በመሆኑ ነው፡፡ ‹‹ዛሬ እንደ ወትሮው ባቀረቡት ሪፖርት ላይ ዝርዝር ጉዳዮች እያነሳሁ ማብራሪያ እንዲሰጡኝ እንደማልጠይቅ የሚያውቁ ይመስለኛል፤›› በማለት የጀመሩት አቶ ግርማ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሪፖርታቸው ምርጫው በሕዝብ ዘ

በጥሎ ማለፉ ውድድር ሐዋሳ ከነማ ደደቢትን 4 ለ 3 ኣሽነፈ

Image
በትናንትናው እለት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄዱ የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ የእግር ኳስ ጨዋታዎች ሐዋሳ ከነማና መከላከያ ድል ቀናቸው። በተመሳሳይ መከላከያ ከዳሽን ቢራ ባደረጉት ጨዋታ በመከላከያ 2 ለ 0 አሸናፊነት ተጠናቋል። የመከላከያ የአሽናፊነት ግቦች በፍጹም ቅጣት የተገኙ ሲሆን ምንይሉ ወንድሙና መሀመድ ናስር ግቦችን ያስቆጠሩ ተጨዋች ናቸው። በተመሳሳይ 10 ሰዓት ላይ ደደቢት ከሐዋሳ ተገናኝተው በመደኛው ሰዓት 2 ለ 2  በሆነ ውጤት በመለያየታቸው ወደ መለያ ምት አምርተው ሐዋሳ ከነማ ደደቢትን 4 ለ 3  በሆነ ውጤት ረቷል። ሳሙኤል ሳኑሚ ሁለቱን ግቦች ለደደቢት ሲያስቆጥር ተመስጌን ተክሉና ገብረሚካኤል ያቆብ አንዳንድ ግቦችን ለሐዋሳ አስቆጥረዋል። በጨዋታው መጠናቀቂያ አካባቢ የሐዋሳ ከነማ ግብ ጠባቂ ሀብቶም ቢሰጠኝ ከደደቢት አጥቂ ዳዊት ፍቃዱ ጋር ባሳዩት ያልተገባ ስፖርታዊ ጨዋነት ሁለቱም በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብተዋል። ጥሎ ማለፉ ዛሬ የሚቀጥል ሲሆን አዳማ ከነማ ከወላይታ ዲቻ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከመብራት ኃይል በ 8 እና በ10 ሰዓት የሚፋለሙ ይሆናል። - See more at: http://www.ena.gov.et/index.php/sport/item/1718-2015-02-06-04-03-22#sthash.qDLTVoCA.dpuf

Ethiopia's January inflation rises 7.7 pct y/y

Image
ADDIS ABABA  (Reuters) - Ethiopia's inflation rose to 7.7 percent year-on-year in January from 7.1 percent in the previous month, the statistics office said on Friday. The Central Statistics Agency attributed the jump to higher prices of food and non-food items. Prices for such items as meat, dairy products, vegetables and fruit increased 7.1 percent last month, up from 6.5 percent in December. Non-food inflation also rose to 8.2 percent in January from 7.8 percent the previous month, mainly due to an increase in prices for clothes and khat, a narcotic leaf chewed in the Horn of Africa nation. Inflation peaked at 9.1 percent in 2014 but it has since been moving up and down.

በስምንት ምድብ የተከፈሉ 32 ዩኒቨርስቲዎች በሚፎካከሩበት የእግር ኳስ ውድድር ሀዋሳ ከምድቡ አምስት ነጥብ በመያዝ በቀዳሚነት አላፊ ሆነ

Image
ሰባተኛ ቀኑን የያዘው የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች 8ኛው የስፖርት ፌስቲቫል በዙር የማጣሪያና የፍፃሜ ውድድሮች በአጓጊነቱ እንደቀጠለ ነው። በ13 የስፖርት ዓይነቶች ከ7 ሺህ በላይ ተወዳዳሪዎች የታደሙበት ፌስቲቫሉ ያሳየው ስፖርታዊ ጨዋነት አሁንም እንደተጠበቀ ይገኛል። ትናንት የተጀመረው የውኃ ዋና ስፖርት በወንጂ የመከላከያ ሠራዊት የአዳማ ጋርመንት ፋውንዴሽን መዋኛ ሥፍራ ተጀምሯል። የ1 ሺህ 500 ሜትር የነፃ ቀዘፋ የመክፈቻ የፍጻሜ ውድድር ሆኖ ድሬዳዋና አክሱም የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ አግኝተውበታል። መቐለ በወንድ የብር፣ አክሱም ደግሞ የነሐስ ሜዳሊያ አሸናፊ ሲሆኑ፥ ባህርዳርና ወሎ ዩኒቨርስቲዎች የብርና የነሐስ ሜዳሊያ በቅደም ተከተል ለግላቸው አድርገዋል። በስምንት ምድብ የተከፈሉ 32 ዩኒቨርስቲዎች የሚፎካከሩበት የእግር ኳስ ውድድርም ሀዋሳ ከምድቡ አምስት ነጥብ በመያዝ በቀዳሚነት አላፊ መሆኑን አረጋግጧል። የመምና የሜዳ ውድድሮች እንደሚደረጉበት በሚጠበቀው አትሌቲክስም ዛሬ በሴቶች የጦር ውርወራ የፍጻሜ ውድድር ይካሄዳል። የ1 ሺህ 500፣ የ400 እና የ100 ሜትር የአጭር ርቀት የማጣሪያ ውድድሮች ዛሬ በሁለቱም ጾታዎች ይከናወናሉ። የቅርጫት፣ የመረብና እጅ ኳስ እንዲሁም ባድሜንተን፣ ቴኒስና ቼዝ በማጣሪያ የዙር ውድድሮች ቀጥለዋል። ምንጭ፦ፋና