Posts

ሲዳማን ጨምሮ በደቡብ ክልል የማጅራት ገትር በሽታ መከላከያ ክትባት እየተሰጠ ነው

Image
Photo: Wikipedia   በደቡብ ክልል የማጅራት ገትር በሽታ መከላከያ ክትባት እየተሰጠ ነው ሀዋሳ ጥቅምት 8/2007 በደቡብ ክልል ከ11 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ተደራሽ የሚያደርግ የማጅራት ገትር በሽታ መከላከያ ክትባት የመስጠት ዘመቻ ዛሬ መጀመሩን የክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ ገለጸ፡፡ በቢሮው ጤናና ጤና ነክ ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ዋና የስራ ሂደት ባለቤት አቶ ጀማል ሀሰን እንደገለጹት ክትባቱ በዘመቻ የሚሰጠው ከዛሬ ጀምሮ ለሚቀጥሉት ለአስር ቀናት ነው፡፡ በዚህ በክልሉ 11 ዞኖችና አራት ልዩ ወረዳዎች ዕድሜያቸው ከ1 እስከ 29 ዓመት የሆናቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ክትባቱ እንዲያገኙ ይደረጋል፡፡ አቶ ጀማል እንዳስረዱት  ሞቃታማ ፣ደረቅና ነፋሻማ የሆነውን የአየር ንብረት ተከትሎ በወረርሽኝ መልክ ሊከሰት የሚችለውን የማጅራት ገትር በሽታ አስቀድሞ ለመከላከል ክትባቱ ይሰጣል ፡፡ ከሁለት አመት በፊት በክልሉ ቤንች ማጂ ፣ ሸካ ደቡብ ኦሞና ካፋ ዞኖች የመጀመሪያ ዙር የመከላከያ ክትባት መሰጠቱን አመልክተዋል፡፡ ሁለተኛው ዙር የማጅራት ገትር በሽታ መከላከያ ክትባት ደግሞ በቀሪዎቹ የክልሉ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች በዘመቻ መጀመሩን ተናግረዋል፡፡ ዘመቻውን ለማሳካትም  በክትባቱ ለሚሳተፉ በየደረጃው ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ስልጠና መሰጠቱም ተመልከቷል፡፡ ክትባቱ በተመረጡ ትምህርት ቤቶች በጤና ተቋማትና ህዝብ በብዛት በሚገኝባቸው አካባቢዎች ማዕከላት እንደሚሰጥና ለክትባቱ አስፈላጊ የሆኑ መድሀኒቶችና ሌሎች ተጓዳኝ ቁሳቁሶች መሰራጨታቸውም  የስራ ሂደት ባለቤት ገልጸዋል፡፡ ህብረተሰቡም ይህንን አውቁ በየአካባቢው ባሉ የክትባት ማዕከላት በመገኘት ልጆቹን ማስከተብ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ በዚህ ዘመቻም በክልሉ የሚ

በኮንፈረንሱ የኢትዮጵያን ቡና ለማሰተዋወቅ ታስቧል

Image
በሶስተኛው ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ቡና ኮንፈረንስ የአገሪቱን ቡና በስፋት በማስተዋወቅና የጥራት ደረጃውን በሚያሳድጉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት እንደሚደረግ የኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች ማህበር አስታወቀ። የማህበሩ የሥራ አመራር ቦርድ ፕሬዝዳንት አቶ ሁሴን አድራው እንደተናገሩት ማህበሩ በሚያዘጋጀው ተመሳሳይ ጉባኤ በአለም አቀፍ ደረጃ የትላልቅ ቡና ገዥ ኩባንያዎችንና ከቡናዘርፍ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ዓለም አቀፋዊና አህጉራዊ ድርጅቶችን ትኩረት መሳብ ተችሏል። ከጥቀምት 27 ጀምሮ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ቡና ኮንፈረንስም አገሪቱ በቡናው ዘርፍ ያላትን ሚና በማሳየትም ትልቅ የገጽታ ግንባታ መድረክ ይሆናልም ብለዋል። በኮንፈረንሱም አገሪቱ ወደ ውጭ የምትልከው ቡና ጥራት ደረጃን በመገምገም ደረጃውን ይበልጥ ለማሻሻል በሚያስችሉ ነጥቦች ላይ ትኩረት ይደረጋል። በኮንፈረንሱ ከቻይና፣ ከደቡብ ኮሪያ፣ ከህንድ እና ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ታዳሚዎች ይፈሉበታል ተብሎ እንደሚጠበቅ ኢዜአ ዘግቧል።  

ፓርቲዎች በምርጫ ማስፈጸሚያ የጊዜ ሰሌዳ ላይ ውይይት ጀመሩ

Image
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በ2007 ዓ.ም በሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ አፈጻጸም የጊዜ ሰሌዳ ረቂቅ ላይ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት አካሄደ። ለ5ኛ ጊዜ በመጪው ግንቦት የሚካሄደው አገራዊ ምርጫ አፈጻጸም የጊዜ ሰሌዳ ረቂቅ ላይ ከ23 አገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች ጋር ነው ውይይቱ የተካሄደው። የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መርጋ በቃና እንዳሉት ውይይቱ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ቦርዱ ባዘጋጀው ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት እንዲንቀሳቀሱ የጋራ መግባባት ለመፍጠር ከፍተኛ እገዛ ይኖረዋል።   በምርጫ ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳ የምክክር መድረክ ላይ ከተገኙት የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ ፕሬዝዳንት አቶ ተሻለ ሰብሮ ረቂቁ ሊያሰራ የሚችል ተስማሚ የጊዜ ሰሌዳ መሆኑን ተናግረዋል። የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዝዳንት አቶ አየለ ጫሚሶ በበኩላቸው ረቂቅ የምርጫ ድርጊት መርሃ ግብሩ መካተት ያለባቸው ጉዳዮች የያዘ በመሆኑ ፓርቲያቸው የተወሰኑ መስተካከል ያለባቸው ጉዳዮች እንዳሉ አስታውቀዋል። የኢህአዴግ ተወካይ የሆኑት አቶ ደስታ ተስፋው በበኩላቸው "የ2007 ዓ.ም የምርጫ አፈጻጸም የድርጊት መርሃ ግብር ረቂቅ የሚያሰራ እና በተቀመጠው መሰረት ወደ ስራ የሚያስገባ ረቂቅ ሰነድ ነው" ብለዋል። የአዲስ ትውልድ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ    አስፋው ጌታቸው    ምርጫ ቦርድ እንደዚህ አይነት የውይይት መድረክ ማዘጋጀቱ ለአገሪቱ የዲሞክራሲ ባህል ግንባታ ሂደት ትልቅ ሚና እንዳለው ገልጸው የቀረበውን ረቂቅ እን ደሚቀበሉት ተናግረዋል።   የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መርጋ ከተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በረቂቁ ላይ በሰጡት አስተያየት የመራጮች ምዝገባ፤ የፓርቲዎች

Ethiopian event celebrates culture, literacy

Image
NW mom nurtures communities for multi-racial families. Photo: www.northdenvertr ibune.com Ethiopian event celebrates culture, literacy Sloan’s Lake—Jen Kraft builds communities. As the adopted mother of a three-year-old Ethiopian daughter, she is the hub of a group of Ethiopian-American families in Denver whose adopted children are the same age. The families stay connected to Denver’s larger community of Ethiopian immigrants. Kraft moved from Manhattan to Northwest Denver in 2004. She adopted Tali Bamlak in 2011 when she was four months old. Kraft met other adoptive parents from Denver at the orphanage in Ethiopia. “We realized our children were born at the same time and we became good friends. Our five children now attend the same preschool here in Denver. It’s important to keep Tali with her friends from Ethiopia because they share such an important history,” Kraft said. Kraft is helping to coordinate “An Ethiopian Odyssey,” a showing of work by four artists who travelle

Child marriage common to both Ethiopia, India: Experts

New Delhi, Oct 17 (IANS):  The problem of child marriage is common to both Ethiopia and India and both can learn from each other's development models for tackling it, experts said here Friday. Tesfaynesh Aregaw, director, Youth Affairs, Ministry of Women and Children of Ethiopia, said: "As in India, the problem of early or child marriage exists in many parts of Ethiopia." She was speaking at a conference on the Ethiopian policymakers' knowledge visit to India. She said that Ethiopia has formulated a structure where women's self-help groups address these issues and the Indian government can study this model to see if it can be effective in India. Aregaw said though the problem of child marriage facing India and Ethiopia was the same, the issues leading to it were different. She added: "In India, it is related to social causes like dowry while in Ethiopia, it is more due to poverty." Leena Sushant, director research at NGO Breakthrough, said