Posts

በተለያዩ የሲዳማ ከተሞች በኣነስተኛ እና ጥቃቂን ማህበራት ተደራጅተው ያሉ የሲዳማ ወጣቶች የመንግስት ትኩረት ያሻቸዋል ተባለ

Image
በሃዋሳ ከተማ በኣነስተኛ እና ጥቃቂን ኢንዱስትሪ ስር የታቀፉ የሲዳማ ወጣት ልጆች በቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ በመጨመር ላይ መሆናቸውን ሪፖርተራችን ሰሞኑን ከሃዋሳ ከተማ ያጠናቀረው ዘገባ ኣመልክቷል። የሲዳማ ወጣቶች በድንጋይ መፍጨት ስራ፤ በኮብል ስቶን ስራ፤ ቢም እና ፕረካስት ስራ የብረታብረት እና የእንጨት ስራ እና በመሳሰሉት የስራ መስኮች በኣነስተኛ እና ጥቃቂን ኢንዱስትሪ በማህበር በመደራጀት በመስራት ላይ ሲሆኑ፤ በራሳቸው ማለትም ብቻቸውን ተደራጅተው ካቋቋሙት ማህበራት በተጨማሪ ከሌሎች ብሄር እና ብሄረሰቦች ልጆች ጋር ተደራጅተው በመስራት ላይ መሆናቸው ተሰሞቷል። በሃዋሳ ከተማ ውስጥ ካሉት በተጨማሪ በሁሉም የሲዳማ ከተሞች በመስል መልኩ የማህበራት በመደራጀት በተለያዩ የስራ መስኮች የገንዘብ እና የስልጣና ድጋፎችን ኣግኝተው የራሳቸውን እና የቤተሰቦቻቸውን ኑሮ ለማሻሻል በመጣር ላይ ናቸው። ወጣቶቹ በጥቃቂን እና ኣነስተኛ ማህበራት ተደራጅተው ስራ መስራታቸው መልካም ሆኖ ሳለ በምሰሩት ስራ ያሳዩት ወጤት ብዙም ኣጥጋብ ኣይደለም። በእርግጥ ከተለያዩ የትምህርት ተቋማት የወጡትን ጨምሮ ብዙ የተግባር ስራ ልምድ የሌላቸው ጊዜያቸውን ባልቧለ ቦታ ያሳልፉ የነበሩት ወጣቶች ወደ ስራ ገብተው ውጤታማ መሆን መጀመራቸው የምካድ ባይሆንም፤ እያስመዘጋቡ ያሉትን ውጤት ከሌሎች ክልል ማህበራት የስራ ውጤቶች ጋር ሲወዳደር ልዩነቱ የእትዬ ሌሌ ነው። ከዚህ ባሻገር በስራ ላይ ውጤት በማጣታቸውም የተነሳ እስከ መበተን የደረሱም ኣሉ። እንደ ጥቻ ወራና ዘጋባ ከሆነ በሃዋሳ ከተማ ሲዳማውያን ብቻ ተደራጅተው ካቋቋሟቸው ማህበራት መካከል ሁለቱ በኣያያዝ ችግር የተነሳ ፈርሰው ከዚህ በፊት ለስራ በከታማዋ ማዘጋጃ የተሰጣቸውን የስራ ቦታ ሊ

የገና በዓልና ተያያዥ ኩነቶች

Image
በአገራችን ከሚከበሩ ሕዝባዊና ሃይማኖታዊ በዓላት መካከል ገና አንዱ ነው፡፡ ይህ በዓል በክርስትና አማኞች ዘንድ የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት መታሰቢያ ነው፡፡ ከፈረንጆቹ ገና በአንድ ሳምንት ዘግይቶ የሚከበረው ይህ ሃይማኖታዊ በዓል፣ በሁሉም የክርስቲያን ቤተ እምነቶች በኩል በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች ይከበራል፡፡ የቱሪስት መስህብ በሆነው በደብረ ሮሃ ላስታ ላሊበላ ያለው አከባበር ደግሞ ከሁሉም የተለየና የሚማርክ ነው፡፡ በበዓሉ ዋዜማ ካህናቱ በሚያቀርቡት ኅብረ ዜማ ይደምቃል፡፡ ከላሊበላ አቢያተ ክርስቲያናት አንዱ በሆነው በቤተ ማርያምና በዙሪያው ባለው የማሜ ጋራ ዝማሬው በጥንግ ድርብና በጧፍ ታጅቦ ይከበራል፡፡ የሃይማኖት አባቶች እንደሚገልጹት፣ በጋራው ላይ የሚያሸበሽቡት ካህናት የመላዕክት፣ ከጋራው ሥር የሚያሸበሽቡት ካህናት ደግሞ የሰው ልጆች ምሳሌዎች ናቸው፡፡  ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደ ጊዜ ካህናትና ሰዎች በአንድነት ኢየሱስ ክርስቶስን ያመሰገኑበት ምሳሌ መሆኑ፣ በስፋት ይነገራል፡፡ የገና ባህላዊ በዓልነቱ በአብዛኛው በገጠራማው የአገራችን ክፍል የሚስተዋል ቢሆንም የተወሰኑ የባህሉ ቅሪቶች በአንዳንድ ከተሞችም አይጠፉም፡፡ በዓሉን በባህላዊ ጭፈራ፣ በገና ጨዋታ፣ ባህላዊ ልብስ ለብሶ ማክበር የተለመደ ነው፡፡  ‹‹በገና ጨዋታ አይቆጡም ጌታ›› የሚለው ብሂል እንደሚያስረዳው፣ ሁሉም ወጣት ከቤቱ ወጥቶ በሜዳ ላይ ጨዋታ፣ በደስታና በሃሴት ያከብረዋል፡፡ እንደሌሎች በዓላት ሁሉ በገና በዓል ድፎ መጋገር፣ ሰንጋ መጣል፣ ጠጅና ጠላ መጎንጨት የተለመደ ነው፡፡ እንደ ፈረንጆቹ የበዛ ባይሆንም፣ በዚህ ጊዜ ስጦታ መስጠት የበዓሉ ዓቢይ መገለጫ ነው፡፡ ሕግ የኅብረተሰብን ባህላዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ሃይማኖታዊ ትስብር የሚገዛ እንደመሆኑ መጠን እነ

ሲዳማውያን በቅርበት ልከታተሉት የምገባ የመሬት ምዝገባ አዋጅ ጸደቀ፤ ኣዋጁ ኣንድ ወጥየኢኮኖሚ ማኀበረሰብ ለመፍጠር ያለመ ነው ተብሏል

የፍትሕ ሚኒስትሩ የተቃወሙት የመሬት ምዝገባ አዋጅ ይሁንታ ተቀባይነት አገኘ፤ ኣዋጁ ከክልሎች ሥልጣን ጋር የሚጋጭ ይዘት ኣለው   የፌዴሬሽን ምክር ቤት የከተማ መሬት ምዝገባ አዋጅን ለማፅደቅ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበለትን የይሁንታ ጥያቄ በፍትሕ ሚኒስትሩና በሌሎች ሁለት አባላት ተቃውሞ አፀደቀ፡፡ የምክር ቤቱ አባል የሆኑት የኦሮሚያ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አብዱላዚዝ አህመድ፦የቀረበው ረቂቅ አዋጅ መሬትን ብቻ መመዝገብ የሚመለከት ሳይሆን፣ ከመሬት ጋር ተያያዥ የሆኑ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን አብሮ መመዝገብ የሚያካትት በመሆኑና ይህ ደግሞ የፌዴራል መንግሥት ሥልጣን ባለመሆኑ ይሁንታው መጠየቁን ጠቁመዋል፡፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የቀረበለት የከተማ መሬት ምዝገባ ረቂቅ አዋጅ የተለያዩ አንቀጾች ከክልሎች ሥልጣን ጋር የሚጋጭ ይዘት ያለው በመሆኑና አንድ ወጥ የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ ለመፍጠር ሲባል ነው የፌዴሬሽን ምክር ቤትን ይሁንታ የጠየቀው፡፡  ረቂቅ አዋጁ በአገሪቱ ውስጥ በሚገኙ ሁሉም ከተሞች መሬትንና በመሬት ላይ ያሉ ቋሚ ይዞታዎችን የመመዝገብ፣ የባለቤትነት መብትና የመጠቀም መብት ዕውቅናና ዋስትናን የሚሰጥ ነው፡፡ ነገር ግን ሕገ መንግሥቱ መሬትና የተፈጥሮ ሀብቶችን አጠቃቀምና አጠባበቅ የተመለከቱ ሕጐች የማውጣት ሥልጣን ለሕዝብ ተወካዮች ቢሰጥም፣ ክልሎች ደግሞ በፌዴራል መንግሥት የሚወጣውን ሕግ መሠረት በማድረግ የማስተዳደር ሕገ መንግሥታዊ ሥልጣን አላቸው፡፡ የቀረበው የመሬት ምዝገባ ረቂቅ አዋጅ በተወሰነ ሁኔታ የክልሎችን ሥልጣን የሚጋፋ ቢሆንም፣ አንድ ወጥ የኢኮኖሚ ማኅበረሰብን ለመፍጠር እጅግ ጠቃሚ በመሆኑ ይህንን አዋጅ በማፅደቅ ተግባራዊ ለማድረግ ክልሎች የሚወከሉበት

Very Nice Ethiopian music 2013 Teferi Lembo Sidama

Image
Very Nice Ethiopian music 2013 Teferi Lembo Sidama  

ጥቂቶች ሊመነደጉ፤ ብዙዎች አሽቆልቁለዋል

ከአዲሱ ጠ/ሚኒስትር አዲስ ራዕይ እንፈልጋለን “የራበው ሥራ ፈልጐ ማግኘት የማይችልና ልጆቹን ለማስተማር አቅም ያጣ ሰው ከባርነት ነፃ ነው ማለት አይቻልም፡፡” የሚለው የአሜሪካዊው ፕሬዚዳንት ሊንደን ቢ. ጆንሰን ንግግር እውነትነት አሁን አሁን በጆሮዬ መደወሉ ራሴን እያስገረመኝ መጥቷል፡፡ የዛሬ አምስትና ስድስት ዓመት ገደማ ደራሲና ጋዜጠኛ አለማየሁ ገላጋይ፤ ስለኑሮ ውድነት ሲጽፍ ብዙዎቻችን እያነበብን ፈገግ ከማለት በቀር ብዙ ልባችን አልተነካም ነበር፡፡ ምናልባትም በጣም አልፎ አልፎ ከምናነባቸው መጣጥፎች ይልቅ መንግስት ስለ ልማት የሚነፋው ጥሩንባ አደናቁሮን ይሆናል፡፡ አሁን አሁን የመንግሥት መዝገበ ቃላት “ልማት” የሚለው ትርጓሜ ግራ እያጋባን መጥቶ ጭራሽ ወደ ብስጭት የተመነዘረብን ብዙ ነን ብዬ አስባለሁ፡፡ መንግስት ልማት የሚለው ከእኛ አፍ “ቫት” እያለ የሚነጥቃትን ገንዘብ ሰብስቦ ለሌቦች ካጠገበ በኋላ፣ በፍርፋሪዋ የሚሠራትን መንገድና ጤና ጣቢያ ወይም ትምህርት ቤት ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ “ኮንደሚኒየም” እየተባሉ የተሠሩት ቤቶች አካባቢ ያለውን ግድየለሽነት ተመልከቱ፡፡ የውሃ መፍሰሻ ቦዮቹ ገና ተሠርተው ሳያልቁ ይፈርሣሉ። ሕንፃው ውስጥ ያሉትን የግብር ይውጣ ሥራዎች ተውአቸው፡፡ ለመሆኑ ልማትና ዕድገት ምንድነው? ወረቀት ላይ የሃሰት ሪፖርቶችን ከምሮ መቀለድ ነው። ቀልድና ውሸትስ እስከ የት ያዘልቀናል? ከወር ወደ ወር ሰዎች በልተው የማደር አቅማቸውን እያጡ፣ ልጆቻቸውን ማስተማር ተራራ መቧጠጥ እየሆነባቸው ሲመጣ --- እንዴት ስለ ዕድገት ይወራል? ጋዜጠኛ መሳይ ካድሬዎች ስለልማትና እድገት ብዙ ቢለፈልፉም ከሕዝቡ የበለጠ ጓዳውን የሚያውቅ ማንም ሊኖር አይችልም፡፡ አለ ቢባልም ከተራ ቀልድነት አያልፍም፡፡ እርግጥ ነው፤ ባለፉት ሃያ ዓመታት ጥቂት