Posts

በሲዳማ ዞን ከ424 ሺህ ለሚበልጡ ህፃናት የተለያዩ በሽታዎች መከላከያ ክትባት ተሰጠ ተባለ

ሃዋሳ ነሐሴ 15/2005 በሲዳማ ዞን በተጠናቀቀው የበጀት አመት ከ424 ሺህ ከሚበልጡ ህፃናት የተለያዩ በሽታዎች መከላከያ ክትባት መሰጠቱን የዞኑ ጤና መምሪያ አስታወቀ ። በመምሪያዉ የጤና ልማት እቅድ የስራ ሂደት ኦፊሰር አቶ አበበ በካዬ ሰሞኑን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጡት መንግሰት ለህፃናትና እናቶች ጤና መጠበቅ በሰጠው ትኩረት በሽታን አስቀድሞ የመከላከሉ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል ። በዞኑ 19 ወረዳዎችና ሁለት የከተማ አስተዳደሮች እድሜያቸው ከአንድ አመት በታች ለሆናቸዉ 424 ሺህ 126 ህፃናት የፖሊዮ ፣ የቲቢ፣ የኩፍኝና የሳንባ ምች በሽታ መከላከያ ክትባት መሰጠቱን አስታዉቀዋል ። በዞኑ በመደበኛ የክትባት አገልግሎት በበጀት አመቱ 105 ሺህ 910 ህፃናት መከተባቸውንም አስረድተዋል። በተጨማሪ 15 ሺህ ለሚሆኑ ከፍተኛ ምግብ አጥረት ችግር ላለባቸው ነፍስጡር እናቶችና ህፃናት የተለያዩ አልሚ ምግቦች እንደተሰጣቸውና ከ 80 ሺህ ለሚበልጡ ህፃናት የቫይታሚን ኤ እደላ መደረጉንም አስረድተዋል። http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=11072&K=1

የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ኅብረትና የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲዎች ውህደት ፈፀሙ

አዲስ አበባ ነሐሴ 15/2005 የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ኅብረትና የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲዎች ውህደት መፈጸማቸውን ትናንት አስታወቁ። የኢትዮጵያ ማሕበረ ዴሞክራሲ-ደቡብ ኅብረት አንድነት ፓርቲ (ኢማዴ-ደህአፓ) በሚል አዲስ ስያሜ ውህደቱን ይፋ ያደረገው ይኸው ፓርቲ የፀረ-ሽብር ሕጉን እንደሚቃወም አስታውቋል። የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጥላሁን እንደሻው ውህደቱን አስመልክቶ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንዳሉት ሁለቱ ፓርቲዎች በአገሪቱ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ዙሪያ በነበራቸው የጋራ አቋም ራዕያቸውን በጋራ ለማሳካት ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል። የኢትዮጵያ ማሕበረ ዴሞክራሲ-ደቡብ ኅብረት አንድነት ፓርቲ (ኢማዴ-ደህአፓ) ሕጋዊ ሰውነት እንዲያገኝ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥያቄ በማቅረብ ቦርዱ ሰኔ 3 ቀን 2005 ዓ.ም የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት መስጠቱን ገልጸዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ውህደቱን በትናንትው ዕለት ይፋ ያደረገው ይኸው ፓርቲ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀድቆ በአገሪቱ ተግባራዊ የሆነውን የፀረ-ሽብር ሕግን እንደሚቃወም አስታውቋል። እንደ አቶ ጥላሁን ገለፃ የፀረ-ሽብር ሕጉ ሠላማዊ የሕዝቦች ተቃውሞን የማፈን ባህሪይ ስላለው ፓርቲያቸው እንደ ሌሎች የመድረክ አባላት ሁሉ ሕጉን ይቃወማል። ፓርቲው በማኒፌስቶው በግልጽ እንዳስቀመጠው የፀረ-ሽብር ሕጉ የዜጎችን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን የሚጋፋ በመሆኑ ሕጉን አጥብቆ እንደሚቃወም ገልጸዋል። በዚህም በኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥታዊ ፍርድ ቤት እንዲቋቋም ፓርቲው ከመፈለግ ባሻገር ትግል እንደሚያደርግ አስረድተዋል። የኢትዮጵያ ማሕበረ ዴሞክራሲ-ደቡብ ኅብረት አንድነት ፓርቲ የኃይማኖት አክራሪነትን፣ የኃይማኖታዊ መንግሥት መቋቋምን እንዲሁም ኃይማ

ሕዝብ ‹‹መልካም አስተዳደር በተግባር!›› እያለ ነው

Image
መንግሥት መልካም አስተዳደር መኖር አለበት ይላል ወይ? አዎን! ኢሕአዴግም በጉባዔው ብሏል፣ በውሳኔም አሳልፏል፡፡ በየቀኑ መግለጫ ይሰጥበታል፡፡ መልካም አስተዳደር እውን የማታደርጉ ወዮላችሁ ብሏል፡፡ የመልካም አስተዳደር አለመኖር አደጋንም ገልጿል፡፡ መንግሥትም ብሏል፣ ኢሕአዴግም ብሏል፣ ሕዝብም ሰምቷል፣ አዳምጧል፡፡  ጥያቄው የተባለው፣ የተወሰነውና ቃል የተገባው መልካም አስተዳደር የት አለ የሚል ነው፡፡ የሕዝቡ ጥያቄ ‹‹መልካም አስተዳደር በተግባር!›› ነውና፡፡ በተግባር ያልታየ ነገር ‹‹ላም አለኝ በሰማይ ወተቷንም አላይ›› ነውና፡፡ መንግሥት በፌዴራል ደረጃም በክልል ደረጃም ወደ ተጨባጭና አሳማኝ ተግባር ይግባ፡፡ ይናገር ሳይሆን ያሳይ፡፡  በዚህ መሥሪያ ቤት ሕዝቡ መልካም አስተዳደር አላገኘም ከተባለ መንግሥት ያንን መሥሪያ ቤት ገባ ብሎ መመርመርና መፈተሽ አለበት፡፡ በመልካም አስተዳደር መጥፋት ምክንያት ያላግባብና ከሕግ ውጭ የተሰጠ ጥቅም ካለ ውሳኔው ትክክል አልነበረም በማለት፣ የወሰኑት ሰዎችም መጠየቅ አለባቸው ብሎ የማስተካከያና የእርምት ዕርምጃ መውሰድ አለበት፡፡  በመልካም አስተዳደር ምክንያት በደል የደረሰባቸው ዜጎች ካሉ ፈትሾ ያላግባብና ከሕግ ውጭ መብታቸው ተጥሷል፣ ተጎድተዋል በማለት የደረሰባቸው በደል እንዳይቀጥል አስተካክሎ፣ አርሞና ይቅርታ ጠይቆ ትክክለኛ ዕርምጃ ሊወስድ ይገባል፡፡ ያኔ ነው ሕዝብ እውነትም መልካም አስተዳደር አለ የሚለው፡፡ እውነትም ለመልካም አስተዳደር ከልብ ቆሟል ብሎ ሕዝብ የሚያምነውና ከጎኑ የሚቆመው፡፡ ስለዚህ ተግባር! ተግባር! አሁንም ተግባር! መንግሥት ለመልካም አስተዳደር መስፈን እንቅስቃሴ ሲያደርግ ሥራው ቀላልና ፈጣን ይሆንለታል ማለት አይደለም፡፡ ሴረኛ ያደናቅፈዋል፡፡ ሙሰኛና ፀረ መልካም

ኮሚሽኑ የተሿሚዎችን፣የተመራጮችንና የመንግሥት ሠራተኞች የሀብት ምዝገባ የሚይዝበትን ስምምነት ተፈራረ

Image
አዲስ አበባ ነሐሴ 14/2005 የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የተሿሚዎችን፣የተመራጮችንና በሕግ ግዴታ የተጣለባቸውን የመንግሥት ሠራተኞች የሀብት ምዝገባ በመረጃ ቋት የሚይዝበትን ስምምነት ከአንድ ኩባንያ ጋር ዛሬ ተፈራረመ። ኮሚሽኑ ሲ ኤስ ኤም ሳይበርቴክ ሶፍት ዌር ኤንድ መልቲ ሚዲያ ከተባለው የሕንድ የግል አማካሪ ተቋም ጋር የተደረገው ስምምነት ለሀብት ምዝገባው የሚያስፈልገውን ሶፍት ዌር ለማሰራት ያስችላል። ለፍትህ ሥርዓት ማሻሻያ ሥርዓት ከተመደበው 198ሺህ 530 ዶላር ድጋፍ የሚሰራው ሶፍት ዌር በፌዴራል ደረጃ የተመዘገቡ 60ሺህ አስመዝጋቢዎችን ሀብት ምዝገባ ውጤት ለሕዝብ ክፍት እንደሚያደርግም ኮሚሽኑ አመልክቷል። የሶፍት ዌር ሥራው ሲጠናቀቅ በሀብት ምዝገባው ዓዋጅ መሠረት ውጤቱን ለሕዝብ ተደራሽ ለማድረግ ከማገዙም በላይ፤በቀጣይ ሀብታቸውን የሚያስመዝግቡ ግለሰቦች ባሉበት ሆነው የመመዝገቢያውን ቅጽ በማውጣት መመዝገብ ይችላሉ። ኮሚሽኑ ከክልሎች የሥነ ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽኖች ጋር ያለውን የመረጃ ልውውጥ እንደሚያቀላጥፈው መግለጹን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዘገባ አስታውቋል። http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=11046&K=1

ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ውግዘትና የመንግሥት ክርክር

በመስፍን መንግሥቱ ኢሕአዴግ ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ መንግሥት በዓለም አቀፍ ሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች የገዛ ዜጎቹን መብቶች ያለገደብ የሚጥስና ሰብዓዊ መብት የሚጥስ እየተባለ ያልተከሰሰበት ጊዜ የለም ማለት ይቻላል፡፡ ይሁን እንጂ ይህ መንግሥት በዜጎች ላይ ይፈጽመዋል በሚባለው የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ዓለም አቀፍ ትኩረትን በሚመለከት የመጀመሪያ ምዕራፍ አይደለም፡፡ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት ከተገረሰሰ በኋላ በኢትዮጵያ የተፈጸሙ የዜጎች ጅምላ ግድያዎችን ዓለም በከፍተኛ መገረም ተከታትሎ አውግዟቸዋል፡፡ ፕሬዚዳንት መንግሥቱ ኃይለ ማሪያም አገዛዛቸው በኢትዮጵያ የከፍተኛ ጭካኔና የመብት ጥሰት ዘመን ሆኖ በዓለም አቀፍ ደረጃ ባተረፈው ታዋቂነት ምክንያት የውግዘት ዒላማ ሆኖ አልፏል፡፡  የደርግ መውደቅ በኢትዮጵያ በዚህ ረገድ የፍፃሜ ምዕራፍ ይሆናል ተብሎ ተስፋ ተደርጎ ነበር፡፡ ነገር ግን አልሆነም፡፡ ከኢሕአዴግ ወደ ሥልጣን መምጣት በኋላም ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በተለይም ሒዩማን ራይት ዎችና አምነስቲ ኢንተርናሽናል ያኔ አዲስ የነበረውን የኢትዮጵያ መንግሥት በሰብዓዊ መብት ጥሰት በማብጠልጠል ነበር የተቀበሉት፡፡ ባለፉት ሃያ ዓመታት ይህ ሥራቸው ሆኖ ዘልቋል፡፡ ጋዜጠኞችን ከመንግሥት ጥቃት በመከላከል ላይ የተሰማሩ ዓለም አቀፍ ድርጀቶችም የኢትዮጵያን መንግሥት በየጊዜው መክሰስ ሥራቸው ሆኗል፡፡ ከእነኝህ ዓለም አቀፍ  ድርጅቶች በተጨማሪ የአሜሪካ  መንግሥት ውጭ ጉዳይ መሥርያ ቤትም በየጊዜው በሚያወጣው ዓመታዊ መግለጫው የኢትዮጵያ መንግሥትን በሰብዓዊ መብት ጥሰትና የፖለቲካ መብቶችን ማፈን ሳይከስ ያለፈበት ጊዜ የለም፡፡ አሁን አሁን የእነኚህን አካላት መግለጫዎች የታወቁ ዓለም አቀፍ መገናኛ ድርጅቶች በመቀባበል