Posts

በሚቀጥለው ሳምንት የኢሕአዴግ አባል ፓርቲዎች ስብሰባ ይጀምራሉ

አራቱ የኢሕአዴግ መሥራች ፓርቲዎች ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ የየራሳቸውን ጠቅላላ ጉባዔ ይጠራሉ፡፡ በተናጠል የሚጠሩት የፓርቲዎቹ ጠቅላላ ጉባዔዎች ቀጣዮቹን የማዕከላዊ ምክር ቤት አባላት ይመርጣሉ፡፡ በእነዚህ ጉባዔዎች የሚመረጡት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ደግሞ ብሔራዊ ፓርቲያቸውን ወክለው ለኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የሚሆኑ ሰዎችን ይመርጣሉ፡፡ ብአዴን፣ ደኢሕዴግ፣ ኦሕዴድና ሕወሓት ጠቅላላ ጉባዔያቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ከመጋቢት 14 እስከ 17 ቀን 2005 ዓ.ም. በሚካሄደው የእናት ፓርቲያቸው (ኢሕአዴግ) ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ባህር ዳር ከተማ ይከታሉ፡፡  በዚህ የኢሕአዴግ ዘጠነኛ ጉባዔ ላይ ትኩረት ከሚያገኙ አጀንዳዎች መካከል የኢሕአዴግ ጠቅላላ ጉባዔ አዳማ ከተማ ተስብስቦ ያፀደቃቸውን ዕቅዶች አፈጻጸም፣ በተለይ አዳማ ላይ ለተካሄደው ጉባዔ የቀረበው የሁለት ዓመት የፓርቲው ዕቅድ የአምስት ዓመቱ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ መነሻ በመሆኑ በጥልቀት ይገመገማል ተብሏል፡፡  ከዚህ በተጨማሪ ነባር ታጋዮችን (አመራሮችን) በመተካካት መርሐ ግብሩ እየቀነሰ በወጣት ኃይል ለመተካት የተያዘውንም ዕቅድ ይገመገማል፡፡ የብአዴን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ አለምነህ መኮንን ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በብአዴን ደረጃ መተካካቱ በተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳ እየሄደ ነው፡፡ የተለወጠ ነገር የለም ሲሉ አስረድተዋል፡፡  በአሁኑ ወቅት የአራቱ ፓርቲዎች የበታች አመራሮች በስብሰባ ተጠምደዋል፡፡ ይህ የፓርቲዎቹ የታችኛው መዋቅር ስብሰባ የሚወክሉ የጠቅላላ ጉባዔ አባላትን መርጦ ይልካል፡፡ የተመረጡት የፓርቲዎቹ ጠቅላላ ጉባዔ አባላት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን ይመርጣሉ፡፡ ማዕከላዊ ኮሚቴዎቹ ናቸው ቀደም ሲል ዘጠኝ የኢሕአዴግ ሥራ አ

የደኢህዴን/ኢህአዴግ አስተዳደሩና ጎሴኝነቱ በሲዳማ ህዝብ ላይ ያደረሰው ኪሳራ

Image
ከማህበራዊ መረብ ላይ የተገኘ ጽሁፍ በሃዋሳ ዱሜ  ኢትዮጵያ ሀገራችን ወዳና ፈቅዳ የፌዴራል መንግሥት ህገ-መንግሥት አካል አድርጋ የተቀበለችውና ዓለም ዓቀፍ ሰብአዊ መብቶች ሰነድ አንቀጽ 1 ላይ እንደተደነገገው ዘረኝነትም ሆነ ጎሴኝነት ከሰብአዊነት መርህና ከሰብአዊ መብቶች የሚቃረን መሆኑንና በዚህ መሠረት የመጀመሪያ አንቀጽ የሚያውጀው የሰው ልጆች እኩልነትን ነው፡፡ ሰዎች ሁሉ እኩል ክብርና መብቶች ይዘውና ነፃ ሆነው ተፈጥረዋል፡፡ ሰው የሚባለው ፍጡር የማሰብና የማመዛዘን ችሎታ በተፈጥሮ ስለታደለ እርስ በርሳቸው በወንድማማችነት ሊተያዩ ይገባል ይላል፡፡ በአንቀጽ ሁለት መሠረት ደግሞ ጉዳዩን ባይበልጥ በማብራራት በዘር፣በቀለም፣በቋንቋ፣ በሃይማኖት፣በፖለቲካ ወይም በሌላ አስተያየት፣በህብረተሰብ ምንጭ፣በሀብት፣በትውልድ ወይም በሌላ አቋም ምክንያት ምንም ዓይነት ልዩነት ሳይደርግበት እያንዳንዱ ሰው በተጠቀሱ መብቶችና ነፃነቶች የመጠቀም መብት አለው ይላል፡፡ ነገር ግን በሲዳማ ውስጥ በተግባር የሚታየው የዚሁ ተቃራን ነው፡፡ የተወሰኑ ማስረጃዎችን መጥቀስ ካስፈለገ፡- ደኢህዴን/ኢህአዴግ የመንግሥት መዋቅርን ማስተዳደር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የሲዳማ ህዝብ በጎሳና በቤተሰብ እንዲከፋፈልና አንድነቱ እንድናጋ ፖለቲካዊ ደባ ተሰርቶበታል፡፡ ህዝባችን ግን አስቀድሞ በመንቃቱ በጎሴኝነት ስሜት የተዘራው ቫይረስ በመንግሥትና በፖለቲካው መዋቅር ተወስኖ ቀረ እንጂ ሊያስከትል የሚችለው አደጋና ኪሳራ ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችል መገመት ይቻላል፡፡ አሁንም ቢሆን በጎሴኝነትና በዘረኝነት የተዘራብን በሽታ በየወረዳው ህዝብን ሰለባ እያደረገና ገና ብዙ ዋጋ የሚያስከፊል የተቀበረብን ፈንጂ ያለ መሆኑን አሁን በተለያዩ ጎሳዎች ላይ እየተሠራ ያለው ከፋፋይ ድራማ መገንዘብ ይቻላል፡፡ በዚሁ መ

ማጆ እና ጭሬ ከተሞችን መሰረት ኣድርጎ በኣሮሬሳ ወረዳ ውስጥ በእናቶች ጤና ላይ በመስራት ላይ ያለው ሜድኮ ሲን ፍሮንተራስ የውሎ ትረካ

Image
De cómo Happy me manchó el chaleco de MSF: relato de un logista por Kevin P. Kavanaugh (logista de Médicos Sin Fronteras en Aroressa, Etiopía). Paisaje con típicas viviendas locales en Aroressa (© Faith Schwieker-Miyandazi). Soy un humilde logista en Etiopía, del equipo de Médicos Sin Fronteras en Aroressa. Estamos ubicados en las tierras altas de la  región de Sidama , en el sur del país. Nuestra misión tiene dos áreas de proyecto, en las ciudades de Mejo y Chire. La conexión entre ambas localidades es una carretera de montaña de 64 kilómetros que atraviesa verdes valles y montañas envueltas en nubes con precipicios verticales de más de 300 metros. La carretera serpentea desde Mejo a través de los valles y del ascenso a la montaña en su camino hasta el proyecto hermano en Chire. Los valles son verdes, con ríos, arroyos, cascadas e imágenes propias de postal, con caballos pastando junto a las casas con forma de hongo. A veces, cuando los atravieso, me imagino ver a Frodo

Displacement, Intimidation and Abuse Land Loyalties in Ethiopia

Image
WEEKEND EDITION MARCH 1-3, 2013 Displacement, Intimidation and Abuse Land Loyalties in Ethiopia by GRAHAM PEEBLES Land grab (and associated water appropriation), Oxfam states, occurs when “governments, banks or private investors buy up huge plots of land to make equally huge profits”. Since 2008 such speculation has vastly expanded; in 2009 alone the OI recorded that “foreign investors acquired 60 million ha of land [worldwide] – the size of France – through purchases or leases of land for commercial farming,” up from an annual average, pre-2008, of 4 million ha. Three quarters of all land deals take place in sub-Saharan Africa, in some of the most food-insecure, economically vulnerable, politically repressive countries in the world; precisely, some say, because of such advantageous commercial factors. In Ethiopia, land sales are occurring in six key areas. Oromia and Gambella in the south, Amhara, Beneshangul, Gumuz, the Sidaama zone, or SNNP and the Lower Omo Valley – a

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሃዋሳ ከነማ ወደ መሪነት ተመለሰ

Image
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 22 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መለስ ዋንጫ ትናንት በተደረጉ ጨዋታዎች ሃዋሳ ከነማ እና መብራት ሃይል ድል ቀንቷቸዋል። ሃዋሳ ከነማ ከቀኑ 9 ሰአት ከአዳማ ከነማ ጋር ባደረገው ጨዋታ 2 ለ 0 በማሸነፍ ወደ መሪነት ተመልሷል። እዚህ አዲስ አበባ ላይ በተደረጉ ሁለት ጨዋታወች ደግሞ እስካሁን ማሸነፍ ያልቻለው ኢትዮጵያ ውሃ ስፖርት ፥ በኢትዮጵያ መድን 2 ለ 1 ተሸንፏል። 11 ሰአት ላይ በተደረገ ሁለተኛ ጨዋታ መብራት ሃይል ሙገር ሲሚንቶን 3 ለ 0 በማሸነፍ ፥ ደረጃውን ወደ አራተኛ አሻሽሏል። ፕሪሚየር ሊጉን ሃዋሳ ከነማ በ22 ነጥብ ሲመራ ፥ ደደቢት በ21 እንዲሁም ቅዱስ ጊዮርጊስ በ19 ነጥቦች ተከታዮቹን ደረጃዎች ይዘዋል። ኢትዮጵያ ውሃ ስፖርት ደግሞ ከ10 ጨዋታዎች ባገኘው አንድ ነጥብ የደረጃውን ግርጌ ይዞ ይገኛል። የፕሪሚየር ሊጉ 11ኛ ሳምንት በመጭው ረቡዕ እና ሃሙስ ተካሂዶ ፥ በብሄራዊ ቡድኑ የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ዝግጅት ምክንያት ለ3 ሳምንታት ይቋረጣል።