Posts

በሲዳማ ዞንና ሃዋሳ ከተማ ከ955 ሺህ በላይ መራጮች ተመዘገቡ

Image
ሃዋሳ ጥር 20/2005 በደቡብ ክልል ሲዳማ ዞንና በሃዋሳ ከተማ በመጪው ሚያዝያ ለሚደረገው የአካባቢ ምርጫ ከ955 ሺህ በላይ መራጮች ተመዘገቡ፡፡ የሲዳማ ዞን ምርጫ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት አስተባባሪ አቶ ብርሃኑ ዱካሞ እንደገለጹት በዞኑ በሚገኙ 21 ወረዳዎችና በሃዋሳና ይርጋለም የከተማ አስተዳደሮች በሚገኙ 1 ሺህ 648 የምርጫ ጣቢያዎች የመራጮች ምዝገባ ያለምንም ችግር በመከናወን ላይ ነው። እስከ ጥር 21 ድረስ በሚቆየው የመራጮችና የዕጩዎች ምዝገባ ከ1 ሚሊዮን 282 ሺህ በላይ መራጮች ይመዘገባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል። ከታህሳስ 22 ጀምሮ በመከናወን ላይ ባለው የመራጮችና የዕጩዎች ምዝገባ ለመራጭነት ከተመዘገቡት መካከል 446 ሺህ 699 ሴቶች መሆናቸውን ጠቁመዋል። በመጪው ሚያዝያ ወር በሚደረገው የአካባቢና የማሟያ ምርጫ ላይ በመራጭነት ለመሳተፍ የመራጮች ምዝገባ በመጪው ማክሰኞ ከመጠናቀቁ በፊት ህብረተሰቡ በመመዝገብ የመራጭነት ማረጋገጫ ካርዱን መያዝ እንዳለበት አስተባባሪው አሳስበዋል። በሃዋሳ ከተማ ሚሊኒየም ቀበሌና ዋጋኔ ዋጮ ቀበሌ ለመራጭነት በመመዝገብ ላይ ከሚገኙት መካከል ወይዘሮ በላይነሽ ደምሴና አቶ ታከለ ተሾመ በሰጡት አስተያየት ያገኙትን ዲሞክራሲያዊ መብት በመጠቀም የተሻለ ለውጥ በማምጣት ይሰራልናል ብለው ያመኑትን ዕጩ ለመምረጥ የመራጭነት ማረጋገጫ ካርድ ወስደዋል። http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=4931&K=1

በሃዋሳ ከተማ ከ7 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጭ የተገነባው የነዳጅ ማደያ አገልግሎት ጀመረ፡፡

Image
ሃዋሳ ጥር 20/2005 የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በማሳካት የኢንዱስትሪውን ልማት ለማፋጠን በሚደረገው ጥረት የልማታዊ ባላሃብቶች ተሳትፎ ከፍተኛ ድርሻ እንዳለዉ የደቡብ ክልል ምክር ቤት ምክትል አፈ ገባኤ አስታወቁ ፡፡ በሃዋሳ ከተማ ከሰባት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጭ የተገነባው ዳሎል ኦይል የነዳጅ ማደያ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡ ምክትል አፌ-ጉባኤ አቶ ማሞ ጎዴቦ ማደያውን መርቀው ስከፍቱ እንደተናገሩት ባለፉት ሁለት አስርት አመታት በግብርና፣ በከተማ ልማት፣ በኢንዱስትሪ፣ በመልካም አስተዳደር እንዲሁም በሌሎችመስኮች በክልሉ አመርቂ ውጤቶች ተመዝግበዋል፡፡ በየደረጃው ለተመዘገቡ ለውጦች መንግስታዊ አደረጃጀቶች፣ መላው ህብረተሰብ፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና የግል ባለሃብቶች በጋራ ያበረከቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው ብለዋል ። በተለይ ይላሉ አቶ ማሞ ሁሉም ዜጋ በሀገሪቱ ውስጥ በሚከናወኑ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ውስጥ የድርሻቸውን እንዲወጡ መንግስት ያስቀመጣቸው ውጤታማ ፖሊሲዎችና ስትራቴጅዎች ለተመዘገበው ስኬት ቁልፍ ድርሻ አበርክተዋል፡፡ በዚህም በክልሉ ከ1986 ወዲህ ከ68 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ከአምስት ሺህ የሚበልጡ ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወስደው ወደ ስራ መሰማራታቸውንና ከአንድ ሚሊዮን ለሚበልጡ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ ዕድል መፍጠራቸው ተናግረዋል፡፡ የሃዋሳ ከተማ ባለፉት ጥቅት አመታት ፈጣን ዕድገት እያስመዘገቡ ካሉ የሀገራችን ከተሞች አንዷ መሆኗን የጠቆሙት አቶ ማሞ የግል ባለሃብቶች ከከተማው ዕድገት ጋር የሚጣጣም የልማት አቅርቦት እንዲኖር ከመንግስት ጎን በመሆን እያበረከቱት ያለው አስተዋጽኦ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አስገንዝበዋል ። የዳሎል ኦይል አክሲዮን ማህበር

የሲዳማ ባህል እና ኣዲስ ኣመትን የተመለከተ በዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል የተዘጋጀ ዶክሜንትር

Image
Sidama's Culture and New Year

ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ከጌታ መንገድና ከኢህአዴግ መንገድ አንዱን መምረጥ ይኖርባቸዋል!

Image
የኢትዮጵያ ሕዝብ ጨረቃን ከሰማይ አውርዱልን እያለ አይደለም። የኢትዮጵያ ሕዝብ እያለ ያለው ግልጽነትን፣ ቀጥተኝነትን፣ ቅንነትንና ሀቀኝነትን አውርዱልን ነው። ዴሞክራሲን አውርዱልን ነው። ቁሳዊ ልማት ብቻውን አይበቃም፣ ሰብአዊና መንፈሳዊ ልማትንም አውርዱልን ነው። ዶ/ር ኃይሉ አርአያ የጌታ ኢየሱስ መንገድ ስል የክርስትና ሃይማኖት ዕምነት ቀኖናውን (ዶግማውን) ሳይሆን ክርስቶስ በዚህ ምድር ላይ ሲያስተምር ያሳየውን የቀናነት፣ የሃቀኝነት፣ የግልጽነት፣ የፍትሓዊነት፣ የእኩልነት፣ የአንድነት፣ የነፃነት፣ የዴሞክራሲያዊነት፣ የመተሳሰብ፣ የመፈቃቀር፣የመከባበር፣ የመተማመን... መንገድ ማለቴ ነው። ይህ መንገድ የክርስትና ሃይማኖት ብቻ ሳይሆን የእስልምና እንዲሁም የሌሎች የዓለም ታላላቅ ሃይማኖቶች መንገድ ነው። በዚህ መንገድ በሚመራ ህብረተሰብ ውስጥ በዕውቀት (በችሎታ) ማነስ ወይም በተራ ስህተት ወይም በስንፍና ካልሆነ በስተቀር ሆን ተብሎ፣ ታስቦና ታቅዶ በተንኮል በሚፈጸም ቂም በቀል፣ ግፍና በደል አገርና ሕዝብ አይጎዱም። የኢትዮጵያ ሕዝብ በዚህ መንገድ ቢመራ ከድህነትና ከኋላ ቀርነት የመላቀቅ፣ በዴሞክራሲያዊና ፍትሐዊ ሥርዓት የመመራትና በነፃነት፣ በሠላምና በአንድነት የክብር ኑሮ የመኖር ተስፋው እየራቀ ሳይሆን እየቀረበና እየለመለመ ይመጣል። የሚያሳዝነው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚመራው በዚህ መንገድ ሳይሆን በኢህአዴግ መንገድ ነው። የኢህአዴግ መንገድ ደግሞ በአብዛኛው ከላይ ከተገለጸው መንገድ የተለየ ነው። በእኔ እምነት የኢህአዴግ መንገድ ቀናነት፣ ግልጽነትና ሀቀኝነት የሚጎድለው መንገድ ነው። ከታሪካቸው እንደተረዳሁት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከልብ አማኝ ክርስቲያን ና

የተቃዋሚዎች በምርጫው መሳተፍና አለመሳተፍ ትርፍም ኪሣራም እንደሌለው ኢህአዴግ ገለፀ

Image
ከሁለት ወራት በኋላ ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው የአዲስ አበባ አስተዳደርና የአካባቢ ምርጫ ላይ የተቃዋሚ ፓርቲዎች መሣተፍና አለመሳተፍ ለኢህአዴግ ትርፍም ኪሳራም እንደሌለውና የሚያጐድለው ነገርም እንደማይኖር ኢህአዴግ ገለፀ፡፡ የኢህአዴግ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሬድዋን ሰይድ ትናንት በፅ/ቤቱ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተናገሩት፤ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በአብዛኛው በአካባቢ ምርጫ ተሳትፈው አያውቁም፡፡ በአካባቢ ምርጫ የሚገኝ ሥልጣን በአብዛኛው ለታይታና ለወሬ የማይመች እና ሥራ ላይ ትኩረት ያደረገ በመሆኑ ተቃዋሚ ፓርቲዎቹ ፓርላማ መግባትን የመዋደቂያ ነጥብ አድርገው ሲንቀሣቀሱ ይታያሉ ብለዋል፡፡ የፓርቲዎቹ በምርጫው ላይ መሣተፍና አለመሳተፍ ትርፍም ኪሣራም የለውም ያሉት አቶ ሬድዋን፤ ለሥርዓቱ ግን መሣተፋቸው ጠቃሚ ይሆን እንደነበርና በምርጫው ውስጥ መሣተፋቸው ራሳቸውን ለማየትና ለመማር እንዲችሉ ያደርጋቸው እንደነበር ተናግረዋል፡፡ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች አንዳንዶቹ አንድ ግለሰብ በአራት ማህተም የሚያንቀሣቅሣቸውና በህይወት በሌሉ፣ የመጀመሪያውን ማህተም ባልመለሱ ሰዎች የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች እንደ ፓርቲ ተቆጥረው ምርጫ ውስጥ ገቡ አልገቡ ሊያሰኝ እንደማይችል ገልፀዋል። ብዙዎቹ ፓርቲዎች አባልም፣ ፅ/ቤትም እንደሌላቸው የተናገሩት ኃላፊው፤ እነዚህ ፓርቲዎች በምርጫው ቢሣተፉ ምንም እንደማይጠቅሙ ጠቁመው፤ ቀድሞውኑ የሚያንቀሣቅሱት ዓላማ ስለሌላቸው፤ ባይሣተፉ ደግሞ ምንም እንደማያጐሉ ምክንያቱም ቀድሞውኑ ያልነበሩ ስለሆነ ሲሉ ተናግረዋል፡፡ በምርጫው ውስጥ የብዙ ፓርቲዎች መሣተፍ የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት መገለጫ አይደለም ወይ በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄም፤ ምርጫው በ29 ፓርቲዎች መካከል የሚ