Posts

ብሄራዊ የስነ- ህዝብ ምክር ቤት ሊቋቋም ነው

Image
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 17፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) በያዝነው ዓመት የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር 84 ነጥብ 3 ሚሊዮን ገደማ መድረሱን ማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ያደረገው ሳይንሳዊ ግምት ያመለክታል። የሃገሪቱ ፖሊሲ የህዝብ ቁጥርን መቀነስ ላይ ከማተኮር ይልቅ ፥ ያለውን የህዝብ ቁጥር ከሃገሪቱ የልማት አቅምና የኢኮኖሚ ክፍፍል ጋር ማጣጣም ላይ አተኩሮ የሚሰራ ነው። ኢትዮጵያም የህዝብ ቁጥሩን ዕድገት ከኢኮኖሚ ዕድገቷ ጋር ለማመጣጠን እንዲያስችላት ፥ ከዛሬ 18 ዓመት በፊት የስነ-ህዝብ ፖሊሲ ቀርጻ ወደ ትግበራ ብትገባም ፥ እስካሁን ተግባራዊ አልተደረገም። ይህንኑ የስነ-ህዝብ ጉዳይ የሚያስተባብረውን የብሄራዊ ስነ-ህዝብ ምክር ቤት ለማማቋም ፥ ባለፈው አመት ረቂቅ ደንብ በማዘጋጀት ለሚኒስትሮች ምክር ቤት መቅረቡን ፤ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ተጠባባቂ የስነ-ህዝብ ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ መኮንን ናና ተናግረዋል። እሳቸው እንዳሉት የሚቋቋመው ምክር ቤት ይበልጥ ውጤታማ ይሆን ዘንድ ፥ እንደገና ሰፋ ያለ ጥናት ተደርጎበት ፤ በዚህ አመት መጨረሻ ወይም በሚቀጥለው አመት መጀመሪያ ላይ ፥ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ይቀርባል። ረቂቁ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቦ አስኪጸድቅ ድረስም ፥ የማስተባበሩን ሒደት ለማከናወን ሃገር አቀፍ ግብረ ሃይል በያዝነው ወር ውስጥ በማቋቋም ፥ ምክር ቤቱ እስኪመሰረት ግብረ ሃይሉ የማስተባበሩን ስራ እያከናወነ ይቆያል ብለዋል አቶ መኮንን። ሃገሪቱ ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት ባለሁለት አሃዝ የኢኮኖሚ ዕድገት ብታስመዘግብም ፥ ካላት የህዝብ ብዛት ጋር መመጣጠን ባለመቻሉ አጠቃላይ የምርት መጠኗ 412 አሜሪካን ዶላር ላይ እንዲወሰን አስገድዷታል። የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ መረጃ እንደሚያመለክተው ደግሞ ፥ በሃገሪ

የሲኣን ምስረታ በኣል እና ኣዲስ ኣመራር

ከማህበራዊ መረብ ላይ የተገኘ  SLM (Sidama liberation movement) is transformed! Today is the day of transformation for SLM and/or Sidama As many sons, daughters and friends of Sidama have been writing and speaking in several medias, occasions, and moments the oppression, terrorism, and agony caused by the tyrant rulers of the past governments including the present one is immeasurable. Since the hands of occupiers had touched the land of Sidama, the people has been fighting and saying no to forceful occupation. Even after the consolidation of the power of the tyrants the people of Sidama hasn’t kept silent. Injustices and lack of good governance and basic human rights violations has been the concern of the entire Sidama. Today I am writing not to mention the injustices and immoral acts of the government.  I would like to take this opportunity to write little about today’s organized resistance response of our people. Of course our people had resisted the occupiers in an organized way incl

ተቃዋሚዎች ከኢህአዴግ ጋር ድርድር እንፈልጋለን አሉ

Image
በመጪው ግንቦት ወር በሚካሄደው የአካባቢና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ላይ ከመወያየታችን በፊት በምርጫው ዲሞክራሲያዊነትና ነፃ መሆን ላይ ልንወያይ ይገባል በሚል ለምርጫ ቦርድ በደብዳቤ ጥያቄ ያቀረቡ 34 ተቃዋሚ ፓርቲዎች፤ የምርጫ ምልክት ውሰዱ መባሉን ተቃወሙ፡፡ በምርጫ ቦርዱ ላይ እምነት ስለሌለን ከኢህአዴግ ጋር ያለቅድመ ሁኔታ ድርድር እንፈልጋለን ብለዋል - ተቃዋሚ ፓርቲዎቹ፡፡የኢህአዴግ ጽ/ቤት ቢሮ ኃላፊና በጠ/ሚኒስትሩ የህዝብ አደረጃጀት አማካሪ አቶ ሬድዋን ሁሴን በበኩላቸው፤ የምርጫ ስነምግባር ደንቡን ካልፈረሙ ፓርቲዎች ጋር አንደራደርም ብለዋል፡፡  ፓርቲዎች የምርጫ ምልክታቸውን እስከፊታችን ሰኞ እንዲወስዱ ምርጫ ቦርድ ያስታወቀ ሲሆን ተቃዋሚዎች በበኩላቸው፤ ለቦርዱ ደብዳቤ በማስገባት ምላሽ እየጠበቁ ባሉበት ሰዓት የምርጫ ምልክት ውሰዱ መባላቸው አግባብ እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡ ተቃዋሚዎች ላቀረቡት ጥያቄ ምርጫ ቦርድ “ምላሽ የሚሰጠው ተገቢ ጥያቄዎችን ሲያቀርቡ ነው” ሲል ለአዲስ አድማስ መግለፁ ይታወሳል፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎቹ በቦርዱ ላይ እምነት እንደሌላቸው በመግለፅ፡- ከኢህአዴግ ጋር ውይይት እንደሚፈልጉና ከዛ በፊት የምርጫ ምልክት እንደማይወስዱ አስታውቀዋል፡፡ የመድረክ የስራ አስፈፃሚ አባልና የ34ቱ ፓርቲዎች ጊዜያዊ ኮሚቴ ዋና ሰብሳቢ አቶ አስራት ጣሴ ለአዲስ አድማስ ሲያስረዱ፤ “ከዚህ ቀደም የተደረጉ ምርጫዎች ችግር የነበረባቸው በመሆናቸው ከጊዜ ሰሌዳው በፊት በምርጫው ፍትሃዊነትና ዲሞክራሲያዊነት ላይ ውይይት እንዲደረግ ፒትሽን ተፈራርመን ለቦርዱ አስገብተን፣ ለሱ ምላሽ ሳይሰጥ ምልክት ውሰዱ መባሉ ተገቢ አይደለም” ብለዋል የምርጫ ቦርዱ ተአማኒነትና ተቀባይነት ጥያቄ ውስጥ ነው ያሉት አቶ አስራት ጣሴ፤ ከኢህአዴግ

የሲዳማ ኣርነት ንቅናቄ 35 ኣምስተኛውን የምስረታ በዓል በደማቅ ሁኔታ ኣከበረ፤ ኣዳዲስ የድርጅት ኣመራር መርጧል

የሲዳማ ኣርነት ንቅናቄ 35 ኣምስተኛውን የምስረታ በዓል በደማቅ ሁኔታ ኣከበረ፤ ኣዳዲስ የድርጅት ኣመራር መርጧል በዛሬው እለት በሃዋሳ ከተማ በዳግም ጂሚናዥዬም በተካሄደው የምስረታ  ሰነስርኣት ላይ የሲዳማ ኣርነት ንቅናቄ  35 ኣመት የምስረታ በኣል በተለያዩ  ዝግጅቶች ኣክብሯል። በርካታ የድርጅቱ ደጋፊዎች በተገኙበት በተካሄደው በዚህ ስነስርኣት ላይ ለሲዳማ ህዝብ ነጻነት ለተሰው ሰማዕታት የህልና ጸሎት የተደረገ  ሲሆን ድርጅቱን በቀጣይነት የምመሩ ኣመራሮች ተመርጠዋል። በኣጠቃላይ 15 ኣባላት ያሉት በኣብዛኛው ወጣቶችን የሆነና የዩኒቨርሲቲ ተማርዎችን ያቀፈ የድርጅት ኣመራር የተመረጠ ሲሆን ኣንጋፋ የሲዳማ ታጋዮችን በኣመራርነት ተካተዋል። በኣመራርነት ከተመረጡት መካከል ካላ ዋቃዮ፤ ዶክተር ኣለማዬሁ፤ እና ካላ ካሳ ኣዲሶ  ይገኙበታል። ክቡራን ኣንባቢያን  ዝርዝር ዜናውን እንደደረሰን እናቀርባለን

በሲዳማ ዞን ሎካ አባያ ወረዳ በየደረጃው ከ26 ሚሊዮን ብር በላይ ለማሠራጨት ግብ ጥሎ እየሠራ መሆኑን የወረዳው ኦሞ ማክሮ ፋይናንስ ንዑስ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

በሲዳማ ዞን ሎካ አባያ ወረዳ በየደረጃው ከ26 ሚሊዮን ብር በላይ ለማሠራጨት ግብ ጥሎ እየሠራ መሆኑን የወረዳው ኦሞ ማክሮ ፋይናንስ ንዑስ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡ የንዑስ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ደሳለኝ ሀይለኢየሱስ እንደገለፁት መንግስት የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል በነደፈው ስትራቴጂ መሠረት በተያዘው በጀት ዓመት 1ዐ ሚሊዮን ብር ብድር ለማሰራጨት እና 18 ሚሊዮን ብር ከቁጠባ ለመሰብሰብ አቅዶ እየሰራ ነው፡፡ ንዑስ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ ከንግድና ኢንዱስትሪ ጽህፈት ቤት ጋር በመተባበር ከተለያዩ ዩንቨርስቲዎችና ኮሌጆ  ለተመረቁ  ተማሪዎችን ከ5 መቶ ሺህ ብር በላይ የብድር አገልግሎት ለመስጠት ማቀዱን ገልፀዋል፡፡ በተያዘው እሩብ በጀት ዓመት 3 ሚሊዮን 6 መቶ ሺህ ብር ብድር ማሰራጨቱንና መቶ ሺህ ብር ቁጠባ መሰብሰብ መቻሉን ጠቁመው 6 ሺህ 8 መቶ የሚሆኑ የህብረተሰቡ ክፍሎች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆናቸውን ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል ሲል ሪፖርተር አካሉ ጥላሁን ከበንሳ ቅርንጫፍ ጣቢያ ዘግቧል፡፡